የደም ግሉኮስ ማመጣጠኛ ፓኬት (ታብሌት/ፓውደር)

$228.95
  • A powerful combination of our Complete Multi-Vitamin Mineral Tablets, Bone Support Powder and Ultimate Omegas 3-6-9 Plus and Blood Glucose Support
  • Containing over 60 Plant Derived Minerals, 16 Vitamins, 12 Amino Acids, 3 Essential Fatty Acids plus extra Chromium and specific botanicals to support healthy blood sugar levels
  • Highly absorbable forms of nutrients and necessary co-factors
  • Rich in antioxidants (vitamins A, C and E) protecting against free radical damage
Size Guide
$228.95
Add to Wish List

ገለፃ

የደም ግሉኮስ ማመጣጠኛ ፓኬት (ታብሌት/ፓውደር)፤ በዘመን አመጣሹ የእርሻ ቴክኖሎጂ ምክንያት ከምግቦቻችን ላይ እየጠፉ የመጡትን በጣም ጠቃሚ እና አስፈላጊ ቪታሚኖችንና ማዕድናትን፣ አሚኖ አሲዶችንና ጠቃሚ ፋቲ አሲዶችን ለመተካት ታልመው የተዘጋጁ ናቸው። የዚህ ውጤታማ ቀመር ድብልቅ ከ 90 በላይ ጠቃሚ ቪታሚኖችን፣ አሚኖ አሲዶችን እና ተፈጥሯዊ ምግቦችን ይዟል፣ ለበለጠ የአጥንት ጥንካሬ ካልሲየምቪታሚን ዲ3 እና ማግኒዚየምን አካቷል፣ ከእነዚህ በተጨማሪም የእኛን ልዩ የኦሜጋ ዘይት ቅይጥ እና የደም ግሉኮስ ማመጣጠኛ ጋር ተጣምሮ የቀረበ ነው፤ ይኸውም በአንቲኦክሲደንት የበለፀገ ሲሆን ሰውነታችሁ የ21ኛው ክፍለ-ዘመን ጭንቀት እና ውጥረት እንዲዋጋ ለመርዳት ታልሞ የተዘጋጀ ነው።

የዚህ ፓኬት ይዘት፤

የደንከሊያ የተሟላ የተለያዩ ቪታሚን ማዕድን ታብሌት

ጥቅሞቹ

ከፍተኛ መጠን ያለው የ ፓይቶኒውትረንት  ቅይጥ፣ ከዕፅዋትን የተቀመሙ ግብዓቶች እና ከፍተኛ አንቲኦክሲደንት የያዘ ነው።

ቪታሚን ቢ አይነቶችን በሙሉ የያዘ - የጉልበት መጠናችሁን ከፍ በማድረግ፣ የድካም ስሜቱን እና ድካምን ይቀንሳል

ቪታሚን ቢ1ቢ2ቢ6 እና ቢ12 - የድካምን ስሜትን እና ድካምን በመቀነስ አስተዋፅዖ ያደርጋል

ቪታሚን ሲ - የበሽታ ተከላካይ ስርዓት ስራውን በአግባቡ እንዲሰራ ጠቃሚ የሆነ

ከፍተኛ ጥራት ያላቸው ግብዓቶች፤ የባክቴሪያ ቅይጥንም ያካተቱ ይኸውም ግብዓቶች በከፍተኛ ሁኔታ እንዲሰርጉ የሚያደርግ

ፍሪ ራዲካልስ ከሚደርስብን ጉዳት የሚከላከሉ ጠቃሚ የሆኑ አንቲ ኦክሲደንቶች  ቪታሚን ኤ እና የያዙ። ፍሪ ራዲካልስ የማይሰክኑ ሞለኪውሎች  ሲሆኑ በሰውነታችን ውስጥ የሚገኙ ህዋሳትን የሚጎዱ እና የጤና ችግር የሚያስከትሉ እና ያለዕድሜ የሚያስረጁ ናቸው።

ፎሊክ አሲድ  ለቀይ የደም ህዋሳት ጤናማ ተግባር አስተዋፅዖ ያለው ነው

ከሚከተሉት ነገሮች ነፃ የሆነ፡ ግሉተን፣ ስንዴ፣ የወተት ተዋፅዖ፣ አኩሪ አተር፣ እርሾ፣ ሰው ሰራሽ ማቆያዎች እና ማጣፈጫዎች ነፃ የሆነ።

የደንከሊያ ዩልቲሜት ኦሜጋ 3-6-9 ፕላስ

ጥቅሞቹ

ኦሜጋ 3-6-9 ከአሳ፣ ከፍላክስሲድ እና ከ ቦራዥ ዘይት በጥንቃቄ የተቀመሩ ቅይጦች ናቸው። ሰውነታችን እነዚህን አስፈላጊ ፋቲ አሲዶች ማመንጨት አይችልም፤ እናም ለተለያዩ የሰውነታችን ስራዎች ወሳኝ ከመሆናቸው አንፃር ከምንመገባቸው ምግቦች እና/ወይም በተጨማሪነት ከምንወስዳቸው ነገሮች ማግኘት አለብን።

ኦሜጋ 3 የሚሰራው ከ EPA(ኤኮሳፐንታኖይክ አሲድ) እና DHA (ዶኮሳሄክሳኖይክ አሲድ) ነው። ይህ ፋቲ አሲድ የሰውነት መቆጣጥን ለመቀነስ እና አጠቃላይ የስሜት ሁኔታን ለማሻሻል ይረዳል። የሚገኘውም ዘይታማ አሳዎች ከሆኑት ሳርዲንማክረል እና ሳልሞን ውስጥ ነው። እንዲሁም ደግሞ አሳዎች በተፈጥሯቸው ወደ EPA እና DHA የሚለውጡትን ALA (አልፋ-ሊኖልኒክ አሲድ) ያካተተ ነው። ሰውነታችን ይህን ተግባር በአነስተኛ መጠን ብቻ ነው መለወጥ የሚችለው።

ኦሜጋ 6 በተለያዩ ዘይቶች፣ የአትክልት-ዘር እና ለውዝ ውስጥ ይገኛል። የሚሰራውም ከሊኖልኒክ አሲድ እና ጋማ-ሊኖልኒክ አሲድ ነው።

ኦሜጋ 9 በተለያዩ አይነት ምግቦች ውስጥ የሚገኝ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥም በአትክልት-ዘር፣ በለውዝ እና በተለያዩ የአትክልት እና የፍሬ ዘይቶች ውስጥ ይገኛል።

ኦሜጋ 3-6-9 በውስጣቸው ያለው የፋቲ አሲድ ምጣኔ የተስተካከለ እንዲሆን በከፍተኛ ጥንቃቄ የተቀመሩ ናቸው። ምርቶቻችን ከፍተኛ ምጣኔ ያላቸው የ ኦሜጋ 3 ዘይቶችን፣ ከ አሳ እና ከ ፍላክስ ፣ የ ኦሜጋ 6ን ደግሞ ከ ቦራዥ እና ፍላክስ ዘይቶች እንዲሁም ኦሜጋ 9ን ደግሞ በ ኦሊክ አሲድ መልኩ ከ ፍላክስ ዘይት የሚያቀርቡ ናቸው።

የደንከሊያ የ ኦሜጋ 3-6-9 የላቁ የ ኦሜጋ ምርቶች የሚታሸጉት በ ናይትሮጀኒክ  አየር በተሞላ ክፍል ውስጥ ነው፣ ይኸውም ዝቃጭ ቅንጣቶችን የሚያስከትል ኦክሲዴሽን እንዳይፈጠር ለመከላከል ነው።

ከሚከተሉት ነገሮች ነፃ የሆነ፡ ግሉተን፣ ስንዴ፣ የወተት ተዋፅዖ፣ አኩሪ አተር፣ እርሾ፣ ሰው ሰራሽ ማቆያዎች እና ማጣፈጫዎች ነፃ የሆነ።

የደንከሊያ የአጥንት ማጠንከሪያ ፓውደር

የደንከሊያ የአጥንት ማጠንከሪያ ፓውደር የአጥንት ጤናዎን የሚደግፉ 7 ዋና ዋና ንጥረ ነገሮችን እንዲያገኙ በጥንቃቄ የተቀመረ ነው። ዕድሜያችን በጨመረ ቁጥር፣ የአጥንታችንን ጤንነት መጠበቅ ይበልጥ ጠቃሚ እየሆነ ይሄዳል ምክንያቱም እንደወጣትነታችን ጊዜ አጥንታችን ራሱን አያድስም። ይኸውም ለኦስቲኦፖሮሲስ ይዳርገናል - በተለይ ደግሞ ደም-በቆረጡ (የወር-አበባ ማየት ባቆሙ) ሴቶች ላይ ይህ ነገር እየተለመደ መጥቷል።

አጥንት ህይወት ያለው ህብረ-ህዋስ ሲሆን ጤናማ አጥንትን እንደገና ለመገንባት ከሰውነታችን ጋር በተመጋጋቢ ግንኙነት የተመረኮዘ ነው - አሮጌው አጥንት በ ኦስቲኦክላስትስ አማካኝነት ይሰባበራል እና ደግሞ አዲስ አጥንት በ ኦስቲኦብላስትስ አማካኝነት ይገነባል። በዚህ ሂደት ውስጥ አለመመጣጠን ሊኖር ይችላል፣ የአጥንት መገንባት (መፈጠር) ወይም የአጥንት መጥፋት (መ’ዋጥ) ሊከሰት ይችላል።

ዕድሜያችን ወደ ሰላሳዎቹ አጋማሽ ሲደርስ፣ ከሚገነባው አጥንት የበለጠ የምናጣው አጥንት እየበዛ ይሄዳል። ስለሆነም ወደዚያ የዕድሜ ደረጃ ከመድረሳችን በፊት የተመጣጠነ የአጥንት መጠን መኖሩ አስፈላጊ ነው። አመጋገባችን እና የአኗኗር ዘይቤያችን፣ እንዲሁም ዘረ-መላችን በአጥንት ጤና ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ ያሳርፋሉ።

የደንከሊያ የአጥንት ማጠንከሪያ ፓውደር ልዩ ቅይጦችን የያዘ ሲሆን እነዚህም አሚኖ አሲድ ቸላትስሲትራትስ  እና ማላትስ  ሲሆኑ እነዚህ ማዕድናት በሁሉም የዕድሜ ክልል ውስጥ ለሚገኙት፣ የምግብ መፈጨት ችግር ላለባቸውም በቀላሉ የሚሰርጉ ናቸው።

ካልሲየም ከተገኙት ሁሉ በተትረፈረፈ መልኩ የሚገኝ መሆኑ የታወቀ ነው፣ ሆኖም ግን በሚገባ መስረግ እንዲችል፣ እንደ ቪታሚን ዲ እና MSM ያሉ ሌሎች ግብዓቶች ያስፈልጉታል። የአጥንት ማጠንከሪያ ፖውደራችን ሙሉ ለሙሉ እንዲሰርግ በላቁ ባለሙያዎች የተቀመረ ነው።

  • የላቀ የካልሲየም ድብልቅ፣ ለአጥንት ጤና አስፈላጊ ከሆኑ ንጥረ ነገሮች ጋር
  • አጥንትን ለማጠንከር ወሳኝ የሆኑ ማዕድናትን እና ቪታሚኖችን የሚያቀርብ
  • የአጥንት ማጠንከሪያ ንጥረ-ነገሮችን በተመጣጠነ ደረጃ ማግኘታችሁን የሚያረጋግጥ
  • ካልሲየም - አጥንትን ለመጠገን
  • ካልሲየም - ሴት ልጅ ደም-ከቆረጠች በኋላ ለሚደርስባት የአጥንት የማዕድን ዴንሲቲ(እፍግታ) ማሽቆልቆልን የሚቀንስ። ዝቅተኛ የሆነ የአጥንት ማዕድን እፍግታ፣ ለ ኦስቲኦፖሮቲክ የአጥንት መሰንጠቅ መንስዔ ነው።
  • ቪታሚን ዲ3ዚንክ እና ማግኒዚየም - ለአጥንት እና ለጡንቻዎች ጤና አስተዋፅዖ አላቸው።
  • ኮፐር - ለአገናኝ ህብረ-ህዋሳት ጤና አስተዋፅዖ አለው
  • ማንጋኒዝ - ለአገናኝ ህብረ-ህዋሳት መፈጠር እና አጥንትን ለመጠገን አስተዋፅዖ አለው
  • MSM(ኤም. ኤስ. ኤም) - በሰውነት ውስጥ ለተለያዩ ዋና ዋና ተግባራት አስፈላጊ የሆነውን ሰልፈር ያቀርብልናል

ከሚከተሉት ነገሮች ነፃ የሆነ፡ ግሉተን፣ ስንዴ፣ የወተት ተዋፅዖ፣ አኩሪ አተር፣ እርሾ ነፃ የሆነ።

የደም ጉሉኮስ ማመጣጠኛ

የደም ውስጥ ግሉኮስ ማመጣጠኛ፣ በከፍተኛ ሁኔታ የላቀ የክሮሚየም ድብልቅ ሲሆን፣ በዕፅዋት ቀማሚዎች ዘንድ ከፍተኛ ቦታ ከሚሰጣቸው እንደ ቀረፋ፣ ጂምነማ ቅጠል፣ የሆምጣጣ የሀባብ ፍሬ እና ጃምቦላን  ፍሬ ጋር አብሮ የሚቀመም ነው። የክሮሚየም ቅንጣቶች የኢንሱሊን  መነቃቃትን የሚጨምሩ እና የሜታቦሊዝም  ሂደትን የሚያስተካክሉ ጠቃሚ ማዕድናት ናቸው። እንዲሁም የፕሮቲን፣ የካርቦሀይድሬት እና የሊፒድ ሜታቦሊዝምን ይደግፋሉ።

ዋና ግብዓቶች

ጂምነማ  ቅጠል የተቀመመ

ጂምነማ ሲልቨስትሪ  አዩርቬዲክ  ህክምና ውስጥ ለብዙ ክፍለ-ዘመናት የስኳር ህመምን ለማከም ሲጠቀሙበት የኖረ ነው። የጂምነማ  የ ሂንዲ ቋንቋ ስም “የስኳር ማጥፊያ” ነው።

ከሆምጣጣ የህንድ ሀባብ የተቀመሙ

ሆምጣጣ ሀባብ ታዋቂነቱ በህንድ ሲሆን፣ ለረዥም ጊዜ የተለያዩ ህመሞችን ለማከም ሲጠቀሙበት የኖሩ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ ታይፕ 2 የስኳር ህመም አንዱ ነው።

ጃምቦላን  ፍሬ የተቀመሙ

ጃሙም  በህንድ ሀገር የሚገኝ ዕፅ ሲሆን የስኳር ህመም መንስዔዎችን ለመቅረፍ የሚያስችል እንደሆነ ይታሰባል። በውስጡም ፋይበር፣ ስብ (ፋት)፣ ፕሮቲን፣ የተለያዩ ቪታሚኖችን እና ማዕድናትን ይዟል። የጃሙም  ፍሬዎች፤ ወደ ሰውነታችን ስርዓት ውስጥ የሚለቀቀውን የስኳር መጠን በማዘግየት፣ በሰውነታችን ውስጥ የሚገኘውን የኢንሱሊን መጠን የሚጨምሩ ጃምቦሊን እና ጃምቦሲን የተባሉ ይዘቶች ያሏቸው ናቸው።

ከሚከተሉት ነገሮች ነፃ የሆነ፡ ግሉተን፣ ስንዴ፣ የወተት ተዋፅዖ፣ አኩሪ አተር፣ እርሾ፣ ሰው ሰራሽ ማቆያዎች እና ማጣፈጫዎች ነፃ የሆነ።

የተሟላ የተለያዩ ቪታሚኖች ማዕድን  ታብሌት - በየቀኑ ከምግብ ጋር ወይም ከምግብ በኋላ 4 ታብሌት መውሰድ፣ ወይም የጤና አማካሪዎ በሚያዝዝዎ መሰረት መውሰድ::

ዩልቲሜት ኦሜጋ 3-6-9 ፕላስ - በየቀኑ ከምግብ ጋር 3 እንክብሎችን እንድትወስዱ ይመከራል፣ ወይም የጤና አማካሪዎ በሚያዝዝዎ መሰረት መውሰድ።

የተሟላ የአጥንት ማጠንከሪያ ፓውደር - 1 ጎድጓዳ ማንኪያ ከ 250 ሚሊ ውሀ ወይም ጭማቂ(ጁስ) ጋር ቀላቅላችሁ ከምግብ ጋር ወይም ከምግብ በኋላ መውሰድ፣ ወይም የጤና አማካሪዎ በሚያዝዎ መሰረት መውሰድ።

የደም ጉሉኮስ ማመጣጠኛ - በየቀኑ ከምግብ በፊት 2 እንክብሎችን መውሰድ፣ ወይም የጤና አማካሪዎ በሚያዝዝዎ መሰረት መውሰድ።

ሁሉም እቃ ፀሀይ በቀጥታ በማያገኘው መልኩ በቀዝቃዛ እና ደረቅ ቦታ ይቀመጥ።

ይህን ምርት በፍሪጅ ውስጥ ማስቀመጥ አያስፈልግም።

Have Questions?Ask An Expert
The cookie settings on this website are set to 'allow all cookies' to give you the very best experience. Please click Accept Cookies to continue to use the site.
የደም ግሉኮስ ማመጣጠኛ ፓኬት (ታብሌት/ፓውደር)
You have successfully subscribed!