የመካነ-ቅርስ ቁፋሮዎች፣ የማሳጅ ቴራፒ ላለፉት አምስት ሺህ አመታት ምናልባትም ከዚያ በላይ ለሆኑ ጊዜያት ሁሉ ውጥረትን ለማቅለል እና ህመምን ለማስታገስ አገልግሎት ላይ እንደዋለ አሳይተዋል። ማሳጅ ውጥረትን ከሰውነት ለማስወገድ በጣም ጠቃሚ ከሆኑት ነገሮች ውስጥ እንደሆነ በሚገባ እናምናለን። ውጥረትን እና ጭንቀትን ለማቅለል እና ለማስወገድ እንዲረዳችሁ የምንጠቀመው የማሳጅ ቴክኒክ ራይኖር ይባላል። ይህ ቴክኒክ የዮጋ አተነፋፈስ ቴክኒኮችን ከምስራቃዊያን ልምዶች እንደ ሺያትሱ፣ ሎሚ ሎሚ፣ አዩርቨዲክ እና ከታይ ማሳጅ ጋር የሚያቀናጅ ነው።

የእኛ የማሳጅ ቴክኒክ ጡንቻዎችን እና የአጥንት ስርዓትን ብቻ የሚያክም አይደለም፣ በተጨማሪነት በሰውነታችን ውስጥ የሚገኘውን የኢነርጂ ስርዓትን ጭምር እንጂ። ሊወገዱ የሚችሉ ውጥረቶች የሚመጡት ከስሜት እና ከጭንቀት ጋር በተገናኙ ጉዳዮች የሚመጡ እንደሆኑ ይታወቃል። የራይኖር ማሳጅ፣ ተፅዕኖ ካሳረፉበት የምስራቃዊያን አሻራዎቹ ጋር፣ የሰውነት ሚዛንን ያዛቡ የተሸማቀቁ ጡንቻዎችን እና አጥንትን ያፋለሱትን ክፍሎች ይፈልጋል። የማሳጅ ቴክኒካችን የተዛቡትን በማስተካከል፣ እያንዳንዱ የሰውነት አካላችን ወደ መዝናናት ስሜት እንዲመጣ ይረዳል። 

የማሳጅ ቴራፒ ዋጋ

የ ራይኖር የመግቢያ ማሳጅ £40 ሲሆን የህብለ-ሠረሰር ጤና UK ሐኪም በሆኑት ዶክተር ሮበርት ተያያዥ የሆነ የህብለ-ሠረሠር ጤና ምርመራ ይደረግላችኋል።

ይህም በ15 ደቂቃ የማማከር፣ የጤና መጠይቅ መሙላት እና መተንተንን የሚጨምር እና በ45 ደቂቃ የማሳጅ ቴራፒ አገልግሎት የተከፋፈለ ነው።

ለአዲስ ደንበኞች የ2 ሰዓት የመግቢያ አገልግሎት £95

የመጀመሪያ ማዕረግ የራይኖር ማሳጅ በተመጣጣኝ ክፍያ የማማከር እና የማሳጅ ቴራፒ አገልግሎትን ያካተተ ነው።

አንድ ሰዓት ለቋሚ ደንበኛ £50

ሁሉም የማሳጅ አገልግሎቶች በቀጠሮ ብቻ የሚስተናገዱ ናቸው፣ እባክዎ እኛን ለማግኘት ይህን ይጫኑ እኛም በተቻለ ፍጥነት መልስ የምንሰጣችሁ ይሆናል። እንደ አማራጭም መደወል ትችላላችሁ።

The cookie settings on this website are set to 'allow all cookies' to give you the very best experience. Please click Accept Cookies to continue to use the site.
You have successfully subscribed!