ፖሊሲያችን እስከ 30 ቀናት ይጠብቃል። ግዢ ፈፅማችሁ 30 ቀናት ካለፋችሁ ግን፣ የገንዘብ ተመላሽም ሆነ ለውጥ አናደርግላችሁም።

የገንዘብ ተመላሽ ለመጠየቅ ብቁ ለመሆን፣ እቃው ያልተጠቀማችሁበት እና በተቀበላችሁት ተመሳሳይ ይዞታ መሆን አለበት። እንዲሁም ደግሞ በትክክለኛው ማሸጊያ መሆን አለበት።

የዕቃ ተመላሻችሁን ለመፈፀም፣ ግዣችሁን የሚያረጋግጥ ሰነድ ወይም ሪሲት የምንጠይቅ ይሆናል።፡

እባካችሁ የገዛችሁትን እቃ መልሳችሁ ወደ አምራቹ  አትላኩት።

ከፊል የሆነ የገንዘብ ተመላሽ የሚሰጥባቸው የተወሰኑ ሁኔታዎች አሉ፤ (የሚቻል ከሆነ)

በትክክለኛው ማሸጊያ ያልሆነ፣ ከእኛ ስህተት ባልሆነ ምክንያት የተጎዳ ወይም የጎደለ ማንኛውም እቃ።

ተልኮላችሁ 30 ቀናት ካለፉት በኋላ የተመለሰ ማንኛውም እቃ


የገንዘብ ተመላሽ (የሚቻል ከሆነ)

የመለሳችሁትን እቃ ከተቀበልን እና ከገመገምን በኋላ፣ የመለሳችሁትን እቃ መቀበላችንን ለማሳወቅ የኢሜይል መልዕክት የምንልክላችሁ ይሆናል። እንዲሁም የገንዘብ ተመላሽ ጥያቄያችሁን መቀበላችንን ወይም አለመቀበላችንን የምናሳውቃችሁ ይሆናል።

ተቀባይነት ካገኛችሁ፣ የገንዘብ ተመላሽ ጥያቄያችሁን ወዲያው የምናስጀምር ሲሆን፣ በተወሰኑ ቀናት ውስጥ ወደ ክሬዲት ካርዳችሁ ወይም መጀመሪያ በከፈላችሁበት አማራጭ አውቶማቲክ በሆነ መልኩ ገቢ የሚደረግላችሁ ይሆናል።

የዘገየ ወይም የጠፋ የገንዘብ ተመላሽ (የሚቻል ከሆነ)

የገንዘብ ተመላሹን እስካሁን ካላገኛችሁ፣ በመጀመሪያ የባንክ አካውንታችሁን ደግማችሁ “ቼክ” አድርጉ።

በመቀጠል የክሬዲት ካርድ ኩባንያውን አግኙት፣ የገንዘብ ተመላሹ በይፋ እስኪለጠፍ ድረስ የተወሰነ ጊዜ ሊወስድ ይችላል። ከዚያም ከባንኮች ጋር ተገናኙ። በአብዛኛው የገንዘብ ተመላሽ እስኪለጠፍ ድረስ ሂደቶቹ የተወሰነ ጊዜ ይወስዳሉ። ይህንን ሁሉ አድርጋችሁ የገንዘብ ተመላሻችሁን ካላገኛችሁ ግን፣ እባክዎ በ info@denkelia.com ያግኙን። 

በለውጥ የተወሰዱ እቃዎች (የሚቻል ከሆነ)

መደበኛ ዋጋ ላላቸው እቃዎች ብቻ ነው የገንዘብ ተመላሽ የሚደረግ፣ እንዳለመታደል ሆኖ በለውጥ የተወሰዱ እቃወች የገንዘብ ተመላሽ አይደረግባቸውም።

ለውጥ (የሚቻል ከሆነ)

እቃወቹን የምንቀይርላችሁ የማይሰሩ ወይም ጉዳት የደረሰባቸው ከሆኑ ብቻ ነው። በተመሳሳይ እቃ መለወጥ ከፈለጋችሁ፣ በ info@denkelia.com የኢሜይል መልዕክት ላኩልን እንዲሁም የገዛችሁትን እቃ በሚከተለው አድራሻ ላኩ The Distribution Solution, Unit 26, Kilwee Business Park, Upper Dunmurry Ln, Belfast, BT17 0HD. ለደንበኞቻችን 100% የእርካታ ዋስትና የምንሰጥ ሲሆን፤ በምርታችን ደስተኛ ካልሆኑ፣ እባክዎ ያግኙን እና ጥያቄዎን በቅደም ተከተል የምናስተናግድልዎ ይሆናል። በከፊል ወይም በሙሉ የገንዘብ ተመላሽ ልናደርግልዎ እና/ወይም ሌላ ምትክ ልንሰጥዎ እንችላለን።

ስጦታዎች

እቃው የስጦታ ምልክት ተደርጎበት የተገዛ እና በቀጥታ ወደ እናንተ የተላከ ከሆነ፣ የገንዘብ ተመላሽ ስታደርጉ የስጦታ-“ክሬዲት” የምትሰጡ ይሆናል። የመለሳችሁትን እቃ እንደተቀበልን፣ የስጦታ የምስክር-ወረቀት የምንልክላችሁ ይሆናል።

እቃው በተገዛበት ወቅት የስጦታ ምልክት ያልተደረገበት ከሆነ፣ ወይም ስጦታ ሰጪው እቃውን ወደራሱ ካስላከ በኋላ ለእናንተ ከሰጣችሁ፣ የገንዘብ ተመላሽ የምናደርገው ስጦታ ለሰጣችሁ አካል ሲሆን እቃውን ስለመመለሳችሁም በዚያው የሚያውቅ ይሆናል።   

መላኪያ

እቃውን ለመመለስ፣ በሚከተለው አድራሻ መላክ አለባችሁ፤ The Distribution Solution, Unit 26, Kilwee Business Park, Upper Dunmurry Ln, Belfast, BT17 0HD.

እቃውን መልሳችሁ ስትልኩ የመላኪያ ዋጋውን የመክፈል ኃላፊነቱ የእናንተው ነው። የመላኪያ ክፍያዎች ተመላሽ አይደረጉም። የገንዘብ ተመላሽ ከተቀበላችሁ፣ ድጋሚ የተላከበት ዋጋ ከተመላሽ ገንዘቡ ላይ ይቀነሳል።

እንደምትኖሩበት አካባቢ፣ የተለወጠላችሁ እቃ እስኪደርሳችሁ ድረስ የቆይታ ጊዜው ከቦታ ቦታ ሊለያይ ይችላል።

ከ £50 በላይ ዋጋ ያላቸው እቃወችን ስታስልኩ፣ የመከታተያ ቁጥር የሚሰጡ የመላኪያ አገልግሎቶችን መጠቀምን ወይም የመልዕክት ዋስትና መግዛትን ግምት ውስጥ ማስገባት አለባችሁ። እናንተ መልሳችሁ የላካችሁትንን እቃ እንደምንቀበል፣ እኛ ዋስትና አንሰጥም።

The cookie settings on this website are set to 'allow all cookies' to give you the very best experience. Please click Accept Cookies to continue to use the site.
You have successfully subscribed!