ወደ ፀጥታ ማፈግፈግ
በሰሜናዊ ኬኒያ ወደሚገኘው ማሪች ፓስ ፊልድ የጥናት ማዕከል፣ ፀጥታን ለማግኘት ማፈግፈጋችንን ስናበስራችሁ በታላቅ ደስታ ነው። ይህ አካባቢ በዘመናዊው ዓለም ያልተነካ ሲሆን፣ ማዕከሉ የተገነባው የአካባቢውን የኢኮቱሪዝም እሴት ከግምት ውስጥ በማስገባት ነው።
እጅግ ፀጥታ በሰፈነበት ቦታ ይዝናኑ፤ ራስዎን ከዲጂታል እና ከፈጣን ምግቦች ሱስ ለማላቀቅ ወይም ከድብርት ለመውጣት በጣም ትክክለኛው ስፍራ ነው። ተፈጥሯዊው የቁጥቋጦ አካባቢ የባህርይ ችግሮችን ለማዳን፤ ኦቲዝምን ወይም የዕድገት መዛባትን፣ ሱስ እና አጠቃላይ የጤና ችግርን ለማከም ተመራጭ ስፍራ ነው።
ማዕከሉ የአካባቢውን ህይወት እና መልክዓ-ምድር ሙሉ ለሙሉ እንድትላመዱ፣ የቁጥቋጦ ውስጥ ጉዞ፣ የአዕዋፋት እይታ፣ የወንዝ ዳርቻ ጉዞ፣ የተራራ መውጣት፣ የሳፋሪ ጉብኝት እና የአካባቢውን ባህላዊ ዳንስ እና እንቅስቃሴዎች ያላምዳችኋል።