ሰላም፣ ስሜ ሰናይት ይባላል የስነ-ምግብ ባለሙያ እና የጤና አሰልጣኝ ስሆን ክብደትን ለመቆጣጠር እና የአዕምሮ-ጤና/ሱሶች እንዲሁም ለተሟላ አካላዊ ጤና የሚሆኑ የስነ-ምግብ ዕቅዶችን በመፍጠር የካበተ ሙያ አለኝ። እንዲሁም ደግሞ የኦቲዝም እና የዕድገት መዛባት ያለባቸውን ልጆች በማሰልጠን ከፍተኛ ልምድ አለኝ። የእኔ ሚና፣ አንድ ግለሰብ የአኗኗር ዘየውን እና የስነ-ምግብ ዕቅዱን እንዴት ማቀናጀት እንደሚችል ድጋፍ እና መመሪያ መስጠት ሲሆን ደንበኞቼ፤ የጤና፣ የአካል ብቃት እና የተስተካከል ቁመና እንዲኖራቸው ያለሙትን ግብ እንዲያሳኩ መርዳት ነው። 



{formbuilder:23775}

ሰናይት


የስነ-ምግብ ባለሞያ፣ የጤና አሰልጣኝ፣ “ቢኤስሲ”



እኔ ያለኝ አቀራረብ ትኩረት የሚያደርገው፤ የአኗኗር ዘየን በሁሉም አቅጣጫ በመመርመር የችግሩን መንስዔ በመለየት፣ ችግሩን መቅረፍ የሚያስችሉ መረጃን መሰረት ያደረጉ ዘዴወችን ማቅረብ ነው።  እኔ ለምግብ እና ለስነ-ምግብ ልዩ ፍቅር ያደረብኝ ገና በልጅነቴ ነበር። የመጀመሪያ ዲፕሎማየን በምግብ-ሳይንስ እና በስነ-ምግብ በ1992 የተቀበልኩ ሲሆን የ “ቢኤስሲ” ዲግሪየን ደግሞ በስነ-ምግብ በ2012 አጠናቅቄያለሁ።

ለስነ-ምግብ አፅንዖት እንድሰጥ እና መልካም አካላዊ ጤንነትን እና አዕምሯዊ ጤናን ለመጠበቅ አስፈላጊ መሆኑን ይበልጥ የተገነዘብኩት፣ አሁን ላይ ያደጉትን ሶስት ልጆቼን ከወለድኩ በኋላ ለብዙ አመታት ባጋጠመኝ የእንሽርሽሪት-መዳከም ምክንያት ለሁለት ወራት ሆስፒታል ከተኛሁ በኋላ ነው። ከዚያም ዋና መንስዔውን ሳይሆን ህመሜን ብቻ የሚያስታግሱ በጣም ብዙ የታዘዙልኝን መድሀኒቶች ከወሰድኩ በኋላ፣  በሰውነቴ ውስጥ ምን እየተካሄደ ነው? እና ለምን? ብየ ራሴን በራሴው መመርመር ጀመርኩ።

በ መልካም ስነ-ምግብ ላይ ትኩረት በማድረግ፣ እንዲሁም ከዕፅዋት የተገኙ ማዕድናትን፣ ቪታሚኖችን፣ አሚኖ አሲድ፣ ጠቃሚ ፋቲ አሲድ በመጠቀም፣ አካላዊ እንቅስቃሴ እና ስነ-ልቦናዊ ጤናን በመጠበቅ፣ ጤናየን ሙሉ-ለሙሉ መልሼ ማግኘት ችያለሁ። አሁን የኔ ዓላማ፣ ተመሳሳይ ምልክት ያለባቸው ሌሎች ሰዎችን ጤናቸውን የሚያውከውን ዋናውን ጉዳይ በመለየት እንዲቆጣጠሩት መርዳት ነው።

እኔ ከተለያዩ ግለሰቦች ጋር የሰራሁ ሲሆን፣ በተለይም የኦቲዝም እና የእድገት መዛባት፣ ኤ.ዲ.ኤች.ዲ፣ የተለያየ የጤና ችግር፣ የበሽታ ተከላካይ መዛባት፣ ህመም እና ሌሎች ሱሶች ካለባቸው ሰወች ጋር ሰርቻለሁ። ሰዎች ያለባቸውን እክል በመቆጣጠር ጤናማ የአኗኗር ዘየን እንዲከተሉ እና ያለሙትን ግብ እንዲያሟሉ በተሳካ ሁኔታ ድጋፍ አድርጊያለሁ።

የደንከሊያን ፍልስፍና እና ምርቶች ሙሉ ለሙሉ እቀበላለሁ፣ ምርቶቹን በመጠቀሜ ስለ ምርቶቹ ውጤታማነት እና የማዳን ጥቅም በራሴ እና በዓመታት ውስጥ በረዳኋቸው ሰዎች ስም መናገር እችላለሁ።

እርስዎንም ጤናዎን የሚያውኩ ዋና መንስዔዎችን እንዲለዩ ለመርዳት የአንድ-ጊዜ የ30 ደቂቃ የማማከር አገልግሎት በነፃ እሰጥዎታለሁ። ፍላጎቱ ካለዎት፣ እባክዎ የመገናኛ ቅፁን ይሙሉ፤ እርስዎን ወደ ጤናማነት በሚያደርጉት ጉዞ መርዳቴ/መምራቴ ለእኔ ታላቅ ደስታ ነው።


The cookie settings on this website are set to 'allow all cookies' to give you the very best experience. Please click Accept Cookies to continue to use the site.
You have successfully subscribed!