የአገልግሎት ውል
የገዛችኋቸውን ነገሮች መግለጫ ከመጠቀማችሁ በፊት ማንበብ አለባችሁ፣ አንዳንድ ጊዜ በዚህ ድረ-ገፅ ላይ የሚቀርቡ መረጃዎች እና በጠርሙሱ/ጣሳው/ማሸጊያ-ሳጥኑ ወዘት. . . ላይ የተለጠፉት መረጃዎች በተወሰነ መልኩ ሊለያዩ ይችላሉ።
የገዛችሁትን መመለስ
ፖሊሲያችን ለ30 ቀናት የሚጠብቅ ሲሆን፣ ግዢ ፈፅማችሁ 30 ቀናት ካለፋችሁ ግን፣ የገንዘብ ተመላሽም ሆነ ለውጥ አናደርግላችሁም።
የገንዘብ ተመላሽ ለመጠየቅ ብቁ ለመሆን፣ እቃው ያልተጠቀማችሁበት እና በተቀበላችሁት ተመሳሳይ ይዞታ መሆን አለበት። እንዲሁም ደግሞ በትክክለኛው ማሸጊያ መሆን አለበት።
የዕቃ ተመላሻችሁን ለመፈፀም፣ ግዣችሁን የሚያረጋግጥ ሰነድ ወይም ሪሲት የምንጠይቅ ይሆናል።
እባካችሁ የገዛችሁትን እቃ መልሳችሁ ወደ አምራቹ አትላኩት።
ከፊል የሆነ የገንዘብ ተመላሽ የሚሰጥባቸው የተወሰኑ ሁኔታዎች አሉ፤ (የሚቻል ከሆነ)
በትክክለኛው ማሸጊያ ያልሆነ፣ ከእኛ ስህተት ባልሆነ ምክንያት የተጎዳ ወይም የጎደለ ማንኛውም እቃ።
ተልኮላችሁ 30 ቀናት ካለፉ በኋላ የተመለሰ ማንኛውም እቃ
አውሮፖ ከሆናችሁ እባካችሁ የአውሮፓ የዕቃ ተመላሽ መረጃን ተመልከቱ
አውሮፖ ውስጥ ሆነው አዝዘው፣ ደንበኛው ባለመገኘቱ ምክንያት ወደ መጋዘን የተመለሱ እቃዎች
ከ10 ኪሎ-ግራም በታች ለሆኑ ወደ አውሮፓ ለሚላኩ ትዕዛዞች የ FedEx ን ፈጣን አለም-አቀፍ መላኪያ የምንጠቀም ሲሆን፣ በተለምዶ ከ1-2 ቀን ውስጥ ያደርሳል። FedEx ዕቃውን ለማድረስ ይሞክራል፣ ግን ተቀባይ ከሌለ ደጃፋችሁ ላይ ካርድ በማስቀመጥ በአካባቢው በሚገኘው መጋዘን ውስጥ ያስቀምጣል። እንደአጠቃላይ በአካባቢው በሚገኘው መጋዘን የሚያስቀምጠው ለ 3 ቀናት ሲሆን ደንበኛው ከFedEx ጋር በመነጋገር እንደገና የሚላክበትን ሁኔታ ማመቻቸት አለበት። በተመሳሳይ ሁኔታ አድራሻውን ለማግኘት አስቸጋሪ ከሆነ፣ ወይም ደንበኛው ረዘም ላለ ጊዜ ወደሌላ ቦታ ከተጓዘ፣ ደንበኛው ወደ ሌላ አድራሻ እንደገና ማስላክ ይጠበቅበታል። የገዛችሁት ዕቃ ወደ እኛ ተዛውሮ የሚመጣ ከሆነ፣ እና ደንበኛው የሚስማማውን መፍትሄ ፈልጎ ከላይ በተጠቀሰው መሰረት አስፈላጊዎን እርምጃ ካልወሰደ እና እቃው ወደ UK መጋዘናችን ተመልሶ ከተቀበልነው £60 የመመለሻ ክፍያ የሚከፍል ይሆናል። በተጨማሪም ደግሞ ደንበኛው እንደገና እንዲላክለት ከፈለገ የመላኪያ ሂሳብ ይከፍላል።
የገንዘብ ተመላሽ (የሚቻል ከሆነ)
የመለሳችሁትን እቃ ከተቀበልን እና ከገመገምን በኋላ፣ የመለሳችሁትን እቃ መቀበላችንን ለማሳወቅ የኢሜይል መልዕክት የምንልክላችሁ ይሆናል። እንዲሁም የገንዘብ ተመላሽ ጥያቄያችሁን መቀበላችንን ወይም አለመቀበላችንን የምናሳውቃችሁ ይሆናል።
ተቀባይነት ካገኛችሁ፣ የገንዘብ ተመላሽ ጥያቄያችሁን ወዲያው የምናስጀምር ሲሆን፣ በተወሰኑ ቀናት ውስጥ ወደ ክሬዲት ካርዳችሁ ወይም መጀመሪያ በከፈላችሁበት አማራጭ አውቶማቲክ በሆነ መልኩ ገቢ የሚደረግላችሁ ይሆናል።
የዘገየ ወይም የጠፋ የገንዘብ ተመላሽ (የሚቻል ከሆነ)
የገንዘብ ተመላሹን እስካሁን ካላገኛችሁ፣ በመጀመሪያ የባንክ አካውንታችሁን ደግማችሁ “ቼክ” አድርጉ።
በመቀጠል ከክሬዲት ካርድ ኩባንያውን አግኙት፣ የገንዘብ ተመላሹ በይፋ እስኪለጠፍ ድረስ የተወሰነ ጊዜ ሊወስድ ይችላል።
ከዚያም ከባንኮች ጋር ተገናኙ። በአብዛኛው የገንዘብ ተመላሽ እስኪለጠፍ ድረስ ሂደቶቹ የተወሰነ ጊዜ ይወስዳሉ።
ይህንን ሁሉ አድርጋችሁ የገንዘብ ተመላሻችሁን ካላገኛችሁ ግን፣ እባክዎ በ info@denkelia.com ያግኙን።
በለውጥ የተወሰዱ እቃዎች (የሚቻል ከሆነ)
መደበኛ ዋጋ ላላቸው እቃዎች ብቻ ነው የገንዘብ ተመላሽ የሚደረግ፣ እንዳለመታደል ሆኖ በለውጥ የተወሰዱ እቃወች የገንዘብ ተመላሽ አይደረግባቸውም።
ለውጥ (የሚቻል ከሆነ)
እቃወቹን የምንቀይርላችሁ የማይሰሩ ወይም ጉዳት የደረሰባቸው ከሆኑ ብቻ ነው። በተመሳሳይ እቃ መለወጥ ከፈለጋችሁ፣ በ info@denkelia.com የኢሜይል መልዕክት ላኩልን እንዲሁም የገዛችሁትን እቃ በሚከተለው አድራሻ ላኩ The Distribution Solution, Unit 26, Kilwee Business Park, Upper Dunmurry Ln, Belfast, BT17 0HD.
ስጦታዎች
እቃው የስጦታ ምልክት ተደርጎበት የተገዛ እና በቀጥታ ወደ እናንተ የተላከ ከሆነ፣ የገንዘብ ተመላሽ ስታደርጉ የስጦታ-“ክሬዲት” የምትሰጡ ይሆናል። የመለሳችሁትን እቃ እንደተቀበልን፣ የስጦታ የምስክር-ወረቀት የምንልክላችሁ ይሆናል።
እቃው በተገዛበት ወቅት የስጦታ ምልክት ያልተደረገበት ከሆነ፣ ወይም ስጦታ ሰጪው እቃውን ወደራሱ ካስላከ በኋላ ለእናንተ ከሰጣችሁ፣ የገንዘብ ተመላሽ የምናደርገው ስጦታ ለሰጣችሁ አካል ሲሆን እቃውን ስለመመለሳችሁም በዚያው የሚያውቅ ይሆናል።
መላኪያ
እቃውን ለመመለስ፣ በሚከተለው አድራሻ መላክ አለባችሁ፤ The Distribution Solution, Unit 26, Kilwee Business Park, Upper Dunmurry Ln, Belfast, BT17 0HD.
እቃውን መልሳችሁ ስትልኩ የመላኪያ ዋጋውን የመክፈል ኃላፊነቱ የእናንተው ነው። የመላኪያ ክፍያዎች ተመላሽ አይደረጉም። የገንዘብ ተመላሽ ከተቀበላችሁ፣ ድጋሚ የተላከበት ዋጋ ከተመላሽ ገንዘቡ ላይ ይቀነሳል።
እንደምትኖሩበት አካባቢ፣ የተለወጠላችሁ እቃ እስኪደርሳችሁ ድረስ የቆይታ ጊዜው ከቦታ ቦታ ሊለያይ ይችላል።
ከ £50 በላይ ዋጋ ያላቸው እቃወችን ስታስልኩ፣ የመከታተያ ቁጥር የሚሰጡ የመላኪያ አገልግሎቶችን መጠቀምን ወይም የመልዕክት ዋስትና መግዛትን ግምት ውስጥ ማስገባት አለባችሁ። እናንተ መልሳችሁ የላካችሁትንን እቃ እንደምንቀበል፣ እኛ ዋስትና አንሰጥም።
መሰረዝ - የግዢ ትዕዛዝ መሰረዝ
ዕቃችሁ በተቀበላችሁ በ 30(ሰላሳ) የስራ ቀናት ውስጥ ሀሳባችሁን ልትቀይሩ እና የግዢ ትዕዛዛችሁን ልትሰርዙ ትችላላችሁ። ትዕዛዛችሁን ለመሰረዝ ከፈለጋችሁ፣ እኛ የገዛችሁበትን ሙሉ ዋጋ ተመላሽ እናደርግላችኋለን።
ማሳሰቢያ፤ የግዢ ትዕዛዛችሁን ለማቋረጥ ከፈለጋችሁ ዕቃውን መመለስ የሚጠበቅባችሁ ሲሆን ዕቃው ሙሉ ለሙሉ እንደ አዲስነቱ መሆን አለበት። ደንከሊያ የስነ-ምግብ ምርቶች ኤል.ቲ.ዲ የመልሶ መላኪያ ዋጋውን (ወደ እኛ መልሳችሁ የላካችሁበትን ዋጋ) ተመላሽ አያደርግም እንዲሁም የገዛችሁትን እቃ ወደ እኛ መልሳችሁ መላክ ካልቻላችሁ፣ እኛ መጥተን የምንወስድበትን ዋጋ እናስከፍላችኋለን።