ደንከሊያ ከህብለ-ሰረሰር ጤና UK ጋር በቅርበት ይሰራል፣ ይኸውም የ25 አመት የህክምና ልምድ ያለው ሲሆን ከጨቅላ ህፃናት እስከ በ90ዎቹ የዕድሜ ክልል ያሉትን ሁሉ ይረዳል።

ለጤና መታወክ እና ህመም መንስዔ ከሆኑት ውስጥ ዋናው የዲስክ መንሸራተት ነው። እዚህ ጋር አከርካሪ አጥንታችን ሲፋለስ ህመም፣ ውጥረት ወይም በነርቮች ላይ ጉዳት ያስከትላል። የዲሽክ መንሸራተት በተለያዩ ምክንያቶች ይከሰታል - በአካላዊ፣ በዘረ-መል፣ በኬሚካል (በብክለት፣ . . ) እንዲሁም በስሜታዊነት ሊከሰት ይችላል።

የዲስክ መንሸራተት ምልክቶች የተለያዩ ናቸው። እዚህ ጋር የተወሰኑት ተጠቅሰዋል - የጀርባ ህመም፣ የአንገት ህመም፣ ድብርት፣ ከባድ ቁርጠት፣ አስም፣ ጉልበት ማጣት፣ ክብደትን አለመቆጣጠር እና ጡንቻዎችን እና ኦርጋኖችን አለመቆጣጠር ናቸው።

ከህብለ-ሰረሰር ጤና UK ጋር በመሆነ፣ በሚከተሉት ነገሮች ላይ እናምናለን፤

  • የሰውነታችን ተፍጥሯዊ ሁኔታ ያልተዛባ ጤንነት ያለው ነው

  • አካላችን በራሱ-የሚያገግም እና የራሱን-ሚዛን የሚጠብቅ ነው

  • ስርዓተ ነርቭ በመላው አካላችን ያለውን ተግባር የሚቆጣጠር ነው

  • በስርዓተ-ነርቭ ላይ ጣልቃ ሊገቡ የሚችሉ ነገሮች አካላዊ፣ ኬሚካላዊ ወይም ስሜታዊ ውጥረቶች ሊሆኑ ይችላሉ

  • ህብለ-ሰረሰር፣ የነርቭ ስርዓትን የሚያስጠልል እና የሚጠብቅ ነው

  • ይህ በአከርካሪ አጥንት መፋለስ ችግር ሊገጥመው ይችላል፣ እርሱም የዲስክ-መንሸራተት ተብሎ ይጠራል

  • አካላችን ነርቭ ጣልቃ ካልገባበት በአግባቡ ይሰራል

  • የህብለ-ሰረሰር UK ስፔሻሊስቶች ዓላማም ይህንን የዲስክ-መንሸራተት ችግር ማዳን ነው

  • ይኸውም ወደ ሙሉ ጤናማነት እንድትሸጋገሩ ይረዳል

የህብለ ሰረሰር ጤና UK ልዩ የሆነ የህብለ-ሰረሰር ማስተካከያ የሚጠቀም ሲሆን፣ በሚያስፈልጋችሁ ልክ በከፍተኛ ሁኔታ ልዩ የሆኑ ቴኪኒኮችን ተፈጥሯዊ በሆነ መልኩ የሚያቀናጅ ነው። ይህ የሚጀምረው በዘመናዊ የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች በመታገዝ የነርቭ ስርዓት ላይ ጣልቃ የገባውን (የአከርካሪ አጥንት የዲሽክ መንሸራተት ተብሎ ይጠራል) ለማስተካከል መጠነኛ ግፊት በማሳደር ነው። የእኛ ዓላማ የችግሩን መንስዔ በማስተካከል እንድትድኑ እና አካላዊ እንቅስቃሴያችሁን እንድታገኙ መርዳት ነው።

እባክዎ የUK ህብለ-ሰረሰር ጤናን በ 07889486989 https://spinalhealthuk.com/ ያግኙን

The cookie settings on this website are set to 'allow all cookies' to give you the very best experience. Please click Accept Cookies to continue to use the site.
You have successfully subscribed!