የቅድመ-ታሪክን መልክዓ-ምድር አስቡት እስኪ፣ ጥርት ያለ፣ በማዕድናት የበለፀገ፣ ያልተበከሉ ዕፅዋቶች የሞሉበት… የደንከሊያ ከ ዕፅዋት የተገኙ የማዕድናት የሚመጡበት ምንጭም ይህ ነው። እነዚህ በ ዩታህ የሚገኙት ጥንታዊ ክምችቶች በዓለም ውስጥ በ ሁሚክ ሼል ከበለፀጉ አካባቢዎች ውስጥ ተጠቃሽ ናቸው። እናም ይህ በማዕድን የበለፀገ ቅርፍተ-መሬት ከዕፅዋት የተገኙ ማዕድናትን የሚያስገኝልን ሲሆን ከ 90-95% በውስጡ አስርጎ የመያዝ አቅም ያለው ነው፤  ይኸውም ኢንኦርጋኒክ ከሆኑ (ኢ-ተፈጥሯዊ) “ሰፕልመንት” እና ከሌሎች ማዕድናት አንፃር በጣም፣ በጣም የሚበልጥ ነው። ከዕፅዋት የተገኙ ማዕድናት ኔጋቲቭ ቻርጅ ያላቸው ሲሆኑ፣ ሰውነታችንን በማፅዳት ሂደት ውስጥ አውቶማቲክ በሆነ መልኩ ይረዱታል። ይህ የኔጋቲቭ ቻርጅ ሰውነታችን ንጥረ ነገሮችን በቀላሉ እንዲያጓጉዝ የሚያበረታታ እና የ “ባዮአቬሌቢሊቲ” ን የሚጨምር ነው። እነዚህ የቅድመ-ታሪክ ዕፅዋት ከ 75 ሚሊዮን ዓመታት በፊት የነበሩ ሲሆን አሁን ላይ ያለውን “የሰፕልመንቴሽን” ገፅታ በመቀየር ደንከሊያ ግቡን እንዲያሳካ አስችለዋል።


ስለ ማዕድን ማውጫው ገለፃ

የደንከሊያ ከዕፅዋት የተገኙ ማዕድናት የሚገኙት በዩናይትድ ስቴትስ የማዕድን ዋና ከተማ በሆነችው በ ዩታህ ሲሆን በጥንቃቄ ወጥተው በምርት ሂደት ውስጥ አልፈው የሚመጡ ናቸው። ምንጫችንም ከ 75 እስከ 150 ሚሊዮን አመታት በፊት የነበሩ የቅድመ-ታሪክ ዕፅዋትን አከማችቶ የያዘ የሁሚክ ሼል ስፍራ ሲሆን፣ አሁን ላይ ይህ ውድ ሀብት ተቀምጦ የሚገኘው ወደ ገፀ-ምድር አቅራቢያ ስለሆነ እጅግ ጥራት ባላቸው ከ ዕፅዋት የተገኙ ማዕድናት ሊያንበሸብሸን ዝግጁ ነው። 

ውሀ እና የ UV ጨረሮች ከእነዚህ ክምችቶች ውስጥ ጥሩ፤ጥሩውን መለየት ይስችላሉ። ይሁን እንጂ፣ የእኛ ምንጮች በጥንት ጊዜ ጥቅጥቅ ደን በነበሩ ነገሮች የተሸፈኑ ናቸው። ይኸውም ደግሞ በስስ የጀሶ ንጣፍ ተሸፍኖ፣ ንጥረ-ነገሮችን ይከላከላል። እኛ ህይወት ጠጋኝ የሆነውን ከዕፅዋት የተገኘ ማዕድን የምናወጣበት የመሬት ንጣፍ ከፍተኛ ግፊት የማይደረግበት ስለሆነ ወደ ቅሪትነት ወይም ብስባሽነት አይለወጥም እናም በቀላሉ መውጣት የሚችል ነው።


አራት ዋና ዋና የዕፅዋት ቡድኖች

የእኛ ከዕፅዋት የተገኙ ማዕድናት ምንጭ የሆነው ቦታ ጥንት ጥቅጥቅ ደን የነበረ ሲሆን በጥንት ጊዜ በ ፈርን፣ አንጂዮስፐርምስ (ለምሳሌ፣ ማግኖሊስ)፣ ሲያካድስ እና ኮኒፈርስ የተሞላ ስፍራ ነበር። በጊዜው፣ እነዚህ አስደናቂ ዕፅዋት የበቀሉበት አፈር በማዕድናት የበለፀገ ነበረ እነዚህም ወደ ኦርጋኒክ ኮሎይዳልስ ተለውጠዋል፣ ከ 75 ሚሊየን ዓመታት በኋላም፣ የደንከሊያ ከዕፅዋት የተገኙ ማዕድናት መሰረት ሆነዋል።

እነዚህ ዕፅዋትም በአፈር ውስጥ ከሚገኙ ከ80+ በላይ “ሜታሊክ” ማዕድናት ቢያንስ 60ዎቹን በውስጣቸው እንደያዙ ይታመናል። ብሮንቶሳውረስ የተባለው የዳይኖሰር ዝርያም በቀን በአማካኝ እስከ 880 ፖውንድ ዕፅዋትን እየነጨ ይመገብ ነበር፣ ዛፎችም በየአመቱ በአማካኝ እስከ 25 “ፊት” ያድጉ ነበር።

የሁሚክ ሼሉ በጥንቃቄ ከጥንታዊ ማረፊያ ስፍራው ከተነሳ በኋላ፣ በ “ስቴራላይስድ” የምግብ ጥራት ደረጃ ባላቸው ግዙፍ ታንከሮች ውስጥ ከተፈጥሯዊ የምንጭ ውሀ ጋር ይከማቻል። እዚህ ጋር ነው የ “ኦስሞሲስ” ሂደት የሚካሄደው፣ ንጥረ ነገሮችም ዝግ-በዝግ ከሼሉ ይወጣሉ። የዚህ ሂደት የመጨረሻ ውጤትም የዕፅዋት የ“ኮሎይዳል” ማዕድን “ሰፕልመንት” የሚያስገኝልን ሲሆን በሊትር 38 ግራም ያለው ከዕፅዋት የተገኙ ማዕድናት ይኖሩታል።  አንድ ሊትር የሚሆን የዚህን ውድ ነገር ለማምረት 78 ፖውንድ ሁሚክ ሼል የሚወስድ ሲሆን፣ ይህም 1034 ፖውንድ የቅድመ-ታሪክ አታክልት እንደሚሆን ይታመናል። 


ሰውነታችን ማዕድናትን የሚያገኝበት 3 መንገዶች አሉት፤



ሜታሊክ ማዕድናት

  • መገኛቸው - የባህር-ጠለል፣ አለት እና አፈር

  • በውሀ የማይሟሙ (ሀይድሮፒክ) ስለሆኑም ለመሟሟት አስቸጋሪ ናቸው

  • ፖዘቲቭ ኤሌክትሪክ ቻርጅ

  • የስርገት “የመመጠጥ” መጠኑ ከ 8% ያነሰ

  • በሱፐርማርኬቶች ውስጥ በመደበኝነት የሚሸት “ሰፕልመንት”


ቸልትድ ማዕድናት

  • በአሚኖ አሲድ ወይም በፕሮቲን የተሸፈነ ሜታሊክ ማዕድን

  • ለደካማ የሜታሊክ ማዕድን ስርገት በ1970ቹ መጨረሻ እንደመፍትሄ የተመረተ

  • የስርገት መጠኑ ከ 50% በላይ


ከዕፅዋት የተገኙ ማዕድናት

  • ኔጋቲቭ ኤሌክትሪክ ቻርጅ

  • በቀላሉ የሚሟሟ (ሀይድሮፊሊክ)

  • ከሜታሊክ ማዕድናት አንፃር ከ 200- 2000 ጊዜ ያነሰ

  • በቀላሉ የሚሟሟ - አንዳንድ ማዕድናት .0000001 ማይክሮን ብቻ ናቸው

  • የስርገት መጠኑ ከ 90 - 95% ነው


ከዕፅዋት የሚገኝ



የደንከሊያ ከዕፅዋት የተገኙ ማዕድናት መገኛ ምንጭም፣ በምድረ-ገፅ ላይ ከ75 ሚሊዮን ዓመታት በፊት በቅለው የነበሩና በማዕድን ከበለፀጉ የቅድመ-ታሪክ ጥቅጥቅ ደኖች ነው። ለሚሊዮን ዓመታት  ከዓለም ተደብቀው የኖሩት የሁሚክ ሼሎች እነዚህን የዕፅዋቶች ቅንጣት በውስጣቸው የያዙ ሲሆን ከምድረ-ገፅ በጥንቃቄ የሚወጡ ሲሆን፣ ከሌሎች የማዕድን ምንጮች እንደ- ደረቅ የባህር-ጠለል ቅንጣቶች ወይም “ቤንቶናይት  ክሌይ” አንፃር እጅግ በጣም የተሻሉ በሚያደርግ የምርት ሂደት ውስጥ ያልፋሉ።


ፈሳሽ የኮሎይዳል ፎርም


ዕፅዋቶች በተፈጥሮ ከመሬት የሚመጧቸው ማዕድናት ወደ “ኮሎይድስ” የሚለወጡ ሲሆን በከፍተኛ ሁኔታ የሚሰርጉ እና “ባዮአቬሌብል” የሆኑ ናቸው።


“ባዮአቬሌብሊቲ” እና “ዲቶክሲፊኬሽን” ን መጨመር


ከዕፅዋት የተገኙት ማዕድናት ያላቸው ኔጋቲቭ ኤሌክትሪካል ቻርጅ፣ የሰውነትን የ “ዲቶክሲፊኬሽን” ሂደት የሚጨምሩ ብቻ ሳይሆኑ ሰውነታችን ንጥረ-ነገሮችን እንዲያጓጉዝ በመርዳት “ባዮአቬሌብሊቲን” ይጨምራሉ።


ጥርት ያለ እና ተፈጥሯዊ

ከዕፅዋት የተገኙ ማዕድናትን ከሁሚክ ሼል ውስጥ የማውጣት ሂደቱ ተጀምሮ-እስኪጠናቀቅ ድረስ በጥንቃቄ ክትትል የሚደረግበት ነው። ማዕድኑ ከወጣ በኋላ፣ በ “ስቴራላይዝድ” የምግብ ጥራት ደረጃ ባለው ግዙፍ ኮንቴነር ውስጥ ከተፈጥሯዊ የምንጭ ውሀ ጋር ይከማቻል፣ ማዕድናቱን ለይቶ የማውጣት ሂደት የሚጀምረውም እዚህ ጋር ነው። ውጤቱም ጥራት ያለው፣ ተፈጥሯዊ ከዕፅዋት የተገኘ ማዕድን ሲሆን ምንም አይነት ሰው-ሰራሽ ንጥረ ነገር ወይም (“ፕሪዘርቫቲቭ”፣ “አዲቲቭስ”፣ “ፍላቮሪንግ”) አይደረግበትም።

The cookie settings on this website are set to 'allow all cookies' to give you the very best experience. Please click Accept Cookies to continue to use the site.
You have successfully subscribed!