ደንከሊያ የ “ሜክ ዋተር ፒውር” አጋር በመሆኑ ኩራት ይሰማዋል፣ የዚህ ኩባንያ የውሀ ማጣሪያዎች እንደ ተፈጥሮ የውሀ ዑደት ተመሳሳይ በሆነ መንገድ የተጣራ ውሀን የሚያመርት ነው።  “ሜክ ዋተር ፒውር” የውሀ ማጣሪያ ወደየቤታችሁ የሚመጣውን የቧንቧ ውሀ ሳይቀር ወደተጣራ ውሀ የሚቀይር ነው፤ ይኸውም ወደ ትነት እስኪቀየር ድረስ በማፍላት ከማንኛውም አይነት ኬሚካሎች፤ እንደ ክሎሪን እና ፍሎራይድ፣ “ሄቪ ሜታልስ” እንደ “ኮፐር” እና “ሊድ”፣ ብክለቶች፣ መርዛማ እና ሌሎች ቅንጣቶች ነፃ የሚያደርግ ነው። ትነቱን ወደ ተጣራ ውሀ በማጤዝ ንፁህ ውሀ የሚሆን ሲሆን ከቀዘቀዘ በኋላ እና በደንከሊያ ከዕፅዋት የተገኙ ማዕድናት ከበለፀገ በኋላ ለመጠጥነት ዝግጁ ይሆናል።

ለቤትዎ የሚሆኑ የውሀ ማጣሪያዎች

የቤት የውሀ ማጣሪያዎች ውጤታማ የውሀ ማጣራት ሂደት እንዳላቸው ይታወቃል። “ሜክ ዋተር ፒውር”ም በውሀ ማጣሪያ መሳሪያዎቹ ከየትኞቹንም የውሀ ማጣሪያ ስርዓቶች እና ስልቶች በጣም የላቀ ነው። የቤት ውስጥ የውሀ ማጣሪያዎቹ፣ ውሀን ለማጣራት የሚያስፈልጓችሁን ነገሮች በሙሉ የያዙ ናቸው፣ ዉሀው የሚጠራቀምበት የጠርሙስ ዕቃ ያለው ሲሆን እናንተው ከዕፅዋት በተገኙት ማዕድናት ታበልፅጉታላችሁ።

ዛሬዉኑ ያግኙን እና በቧንቧ ውሀ እንዲሁም ደግሞ በታሸጉ ውሀዎች ላይ ሳይቀር ከሚገኙ መጥፎ ኬሚካሎች እና ተፈጥሯዊ ያልሆኑ ማዕድናት ቤተሰብዎን ይጠብቁ! ከእኛ ጋር በመቀላቀል ራሳችሁ እንዴት ውሀችሁን የተጣራ ንፁህ ማድረግ እንደሚችሉ ይማሩ እንዲሁም ደግሞ ከዕፅዋት በተገኙት ማዕድናት ውሀውን በማበልፀግ በምድር ላይ ምርጥ የሚባለውን ውሀ መጠጣት ያለውን ጥቅም አጋሩን።

የውሀ ማጣሪያችሁን ለመግዛት ይህን ይጫኑ. . .


የውሀ ማጣሪያ የጤና ጥቅሙ እና አጠቃቀሙ

የውሀ ማጣሪያ ለመግዛት ፈልገው፣ ነገር ግን ስለ ጤና ጥቅሞቹ ወይም አጠቃቀሙ በደንብ እርግጠኛ አልሆኑም? አንዳንድ ሰዎች በጥዜት የተጣራ ውሀ ማለት በ “ስቲም አይረን” የሚጨመረው ይመስላቸዋል እናም ሙሉ ለሙሉ ተሳስተዋል ማለት አይቻልም። ኖርማል የቧንቧ ውሀን በ 50/50 ምጣኔ መደባለቅ የ “ስቲም አይረን”ን ዕድሜ በከፍተኛ ሁኔታ ሊያረዝም ይችላል። በጥዜት የተጣራ ውሀ፣ ተፈጥሯዊ ካልሆኑ ማዕድናት እና ቅንጣቶች ነፃ ሲሆን፣ ለመጠጥነት፣ ለማብሰያ እና ለፅዳት ተመራጭ ነው።

ኩልል ካለው ጣዕም በተጨማሪ፣ የተለያዩ የጤና ጥቅሞችን ታገኛላችሁ እንደምሳሌ የቆዳ ልስላሴ፣ ከፍተኛ ጉልበት፣ የተሻለ አዕምሮ እና የአንጎል ኃይል እንዲሁም ጤነኛ የሰውነት ክፍሎች “ኦርጋን” እና አካላዊ እንቅስቃሴን ታገኛላችሁ። የሰውነታችን 70% ያህሉ የተገነባው ከውሀ ነው፣ ስለሆነም በቀን ውስጥ ቢያንስ ስምንት ብርጭቆ እጅግ በጣም የተጣራ ውሀ በመጠጣት፣ በራሳችን ላይ ከፍተኛ የጤና ለውጥ ብንመለከት ሊያስገርመን አይችልም።

በጥዜት የተጣራን ውሀ መጠቀም ዘርፈ ብዙ ጥቅሞች አሉት። ስለሆነም የቤት ውስጥ የውሀ ማጣሪያ መግዛት ከፍተኛ ጥቅም አለው። በቋሚነት የተጣራ ውሀ ስለምታገኙ የ መስታወት ማፅጃ መግዛትም በፍፁም አያስፈልጋችሁም። በመስታወት ላይ ሳይፀዱ የሚቀሩ ነገሮች ለምን እንደሚያጋጥሟችሁ አስባችሁ ታውላችሁ? ምክንያቱም በቧንቧ ውሀ ውስጥ ከሚገኙ ቅንጣቶች እና መርዛማ ነገሮች የሚተርፉ ናቸው። የ መስታወት እቃወችን ለማፅዳት የተጣራን ውሀ የምትጠቅሙ ከሆነ ግን በአስደናቂ መልኩ ፅዱ እንደሚሆኑ ታስተውላላችሁ።

የተጣራ ውሀ በመዋኛ መነፀሮች ላይ የሚገኙ አስቀያሚ ቆሻሻወችን ለማስወገድ ተመራጭ ነው። በቀላሉ በጥዜት በተጣራ ውሀ ውስጥ መነፀራችሁን ዘፍዝፋችሁት አድራችሁ ጠዋት ላይ ልክ እንደአዲስ ሆኖ ታገኙታላችሁ። እንዲሁም ደግሞ፣ በቤትዎ ውስጥ ለምትጠቀሙት “ስቲም” በሙሉ የተጣራን ውሀ ተጠቀሙ። የልብስ ካውያዎችም በልብሳችሁ ላይ ምልክት መተዋቸውን ያቆማሉ፣ የ “ስቲም” መወልወያዎችም በአስደናቂ መልኩ ያፀዳሉ፤ ከሁሉም በላይ ደግሞ ውስጣቸው ላይ የ “ላይም” ክምችት ስለማይፈጥሩ ረዥም ዕድሜ ይኖራቸዋል።

ጥራትን ከተመጣጣኝ ዋጋ ጋር የያዙ የጥዜት የውሀ ማጣሪያዎችን ፈልጋችሁ ከሆነ፣ ሌላ ፍለጋ ሳትደክሙ በአውሮፓ ቀዳሚ የጥዜት የውሀ ማጣሪያ አቅራቢ ከሆነው “ሜክ ዋተር ፒውር” ከማይዝግ ብረት የተሰሩ የተለያዩ አይነት የውሀ ማጣሪያዎችን ታገኛላችሁ።

የውሀ ማጣሪያችሁን ለመግዛት ይህን ይጫኑ. . .

The cookie settings on this website are set to 'allow all cookies' to give you the very best experience. Please click Accept Cookies to continue to use the site.
You have successfully subscribed!