ሰናይት፣ የስነ-ምግብ ባለሙያ እና የጤና አሰልጣኝ ስትሆን በተለይ ደግሞ ክብደትን ለመቆጣጠር፣ ለአዕምሮ ጤና እንዲሁም የተሟላ አካላዊ ጤናን የሚጠብቁ የስነ-ምግብ ዕቅዶችን የምታዘጋጅ ባለሙያ ናት። የእርሷ ሚና፣ አንድ ግለሰብ የአኗኗር ዘየውን እና የስነ-ምግብ ዕቅዱን እንዴት ማቀናጀት እንደሚችል ድጋፍ እና መመሪያ በመስጠት ደንበኞቿ፤ የጤና፣ የአካል ብቃት እና የተስተካከል ቁመና እንዲኖራቸው ያለሙትን ግብ እንዲያሳኩ መርዳት ነው። 

በተጨማሪም ሰናይት የ ኦቲዝም እና የዕድገት መዛባት ካለባቸው ልጆች ጋር ጥልቅ ግንኙነት ያላት ሲሆን እንደ አማካሪ እና እንደ አሰልጣኝ በመሆን ትረዳቸዋለች። ሰናይት ከደንበኞቿ ጋር ስትሰራ ዘርፈ-ብዙ ዕይታ ያላት ሲሆን፣ የደንበኞቿን የአኗኗር ዘየ በሁሉም አቅጣጫ በመመርመር የችግሩን መንስዔ በመለየት፣ ችግሩን ለመቅረፍ መረጃን መሰረት ያደረጉ ዘዴወችን ትጠቀማለች። 

ሰናይት ለምግብ እና ለስነ-ምግብ ልዩ ፍቅር ያደረባት ገና በልጅነቷ ሲሆን የመጀመሪያ ዲፕሎማዋን በምግብ-ሳይንስ እና በስነ-ምግብ በ1992 ተቀብላለች እንዲሁም ደግሞ የ “ቢኤስሲ” ዲግሪዋን በስነ-ምግብ ከሂርፎርድሻየር ዩኒቨርሲቲ  በ2012 ተቀብላለች።

ሰናይት በደካማ እንሽርሽሪት ምክንያት ለረዥም አመታት ስትሰቃይ ኖራለች ይኸውም ሶስት ልጆቿ ከተወለዱ በኋላ ለ2 ወራት ሆስፒታል ገብታ እንድድትታከም አድርጓታል፣ ከዚያ በኋላም የተሟላ አካላዊ እና አዕምሯዊ ጤናን ለማግኘትና ለመጠበቅ ስነ-ምግብን እንደ መሳሪያ መመልከት ጀመረች።

በመልካም ስነ-ምግብ ላይ ትኩረት በማድረግ፣ እንዲሁም ከዕፅዋት የተገኙ ማዕድናትን፣ ቪታሚኖችን፣ አሚኖ አሲድ፣ ጠቃሚ ፋቲ አሲድ በመጠቀም፣ አካላዊ እንቅስቃሴ እና ስነ-ልቦናዊ ጤናን በመጠበቅ፣ ሰናይት ጤናዋን ሙሉ-ለሙሉ መልሳ ማግኘት ችላለች። በዚህ ምክንያትም፣ የእርሷ ዓላማ፣ ተመሳሳይ ምልክት ያለባቸው ሌሎች ሰዎችን ጤናቸውን የሚያውከውን ዋናውን ጉዳይ በመለየት መፍትሄ መፈለግ ነው። ሌሎች ሰዎችንም ያለባቸውን እክል ቀርፈው ጤናማ የአኗኗር ዘየ እንዲኖሩ እና ግባቸውን እንዲያሟሉ በተሳካ ሁኔታ መርዳት ችላለች።

The cookie settings on this website are set to 'allow all cookies' to give you the very best experience. Please click Accept Cookies to continue to use the site.
You have successfully subscribed!