የደንከሊያ የሱስ ማጥፊያ ፓኬት (ታብሌት/ፈሳሽ)

$670.95
This comprehensive pack has been expertly designed to deal with underlying digestive issues that can lead to a malabsorption of nutrients, further exacerbating the addiction to unwanted substances such as alcohol, drugs and junk food. Alongside the digestive programme are an array of specifically designed products targeted at giving the body the nutritional support needed to relieve unwanted addictions.
Size Guide
$670.95
Add to Wish List

ገለፃ

የደንከሊያ የሱስ ማጥፊያ ፓኬት ጤናማ ለመሆን እና ጤናን ለማስቀጠል የሚያስችሉ ጠቃሚ የሆኑ የንጥረ-ነገሮች ድብልቅ ይዟል፣ እንዲሁም ሱስ ለማጥፋት የሚረዳ ይዘት አለው። ይኸውም፤ በዘመን አመጣሹ የእርሻ ቴክኖሎጂ ምክንያት ከምግቦቻችን ላይ እየጠፉ የመጡትን በጣም ጠቃሚ እና አስፈላጊ ቪታሚኖችን እና ማዕድናትን፣ አሚኖ አሲዶችን እና ጠቃሚ ፋቲ አሲዶችን ለመተካት ታልመው የተዘጋጁ ናቸው።

ይህ የተሟላ ፓኬት የንጥረ ነገሮች አለመስረግ መንስዔ የሆነውን ይባስ ብሎም አላስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን እንደ አልኮል፣ አደንዛዥ ዕፅ እና ጤናን የሚጎዱ ምግቦች ሱሰኛ የሚያደርገን የእንሽርሽሪት ሂደት መዛባትን ለማስተካከል በመፍትሄነት በልዩ ባለሙያዎቻችን የተቀመረ ነው።  የእንሽርሽሪት ስርዓትን ከማስተካከል በተጨማሪ ሰውነታችንን ካላስፈላጊ ሱሶች ለማላቀቅ የሚያስፈልጉ የተለያዩ ንጥረ-ነገሮችን እንዲሰጠን ታልመው የተዘጋጁ ምርቶች ናቸው።


የዚህ ፓኬት ይዘት፤

የደንከሊያ የተሟሉ የተለያዩ ቪታሚን ማዕድናት ታብሌት

ጥቅሞቹ

ከፍተኛ መጠን ያለው የ ፓይቶኒውትረንት  ቅይጥ፣ ከዕፅዋትን የተቀመሙ ግብዓቶች እና ከፍተኛ አንቲኦክሲደንት የያዘ ነው።

የቪታሚን ቢ አይነቶችን በሙሉ የያዘ - የጉልበት መጠናችሁን ከፍ በማድረግ፣ የድካም ስሜቱን እና ድካምን ይቀንሳል

ቪታሚን ቢ1፣ ቢ2፣ ቢ6 እና ቢ12 - የድካምን ስሜትን እና ድካምን በመቀነስ አስተዋፅዖ ያደርጋል

ቪታሚን ሲ - የበሽታ ተከላካይ ስርዓት ስራውን በአግባቡ እንዲሰራ ጠቃሚ የሆነ

ከፍተኛ ጥራት ያላቸው ግብዓቶች፤ የባክቴሪያ ቅይጥንም ያካተቱ ይኸውም ግብዓቶች በከፍተኛ ሁኔታ እንዲሰርጉ የሚያደርግ

ፍሪ ራዲካልስ ከሚደርስብን ጉዳት የሚከላከሉ ጠቃሚ የሆኑ አንቲ ኦክሲደንቶች  ቪታሚን ኤ፣ ሲ እና ኢ የያዙ። ፍሪ ራዲካልስ የማይሰክኑ ሞለኪውሎች  ሲሆኑ በሰውነታችን ውስጥ የሚገኙ ህዋሳትን የሚጎዱ እና የጤና ችግር የሚያስከትሉ እና ያለዕድሜ የሚያስረጁ ናቸው።

ፎሊክ አሲድ  ለቀይ የደም ህዋሳት ጤናማ ተግባር አስተዋፅዖ ያለው ነው


የደንከሊያ የአጥንት ማጠንከሪያ ፈሳሽ

የደንከሊያ የአጥንት ማጠንከሪያ ፈሳሽ የአጥንት ጤናዎን የሚደግፉ 7 ዋና ዋና ንጥረ ነገሮችን እንዲያገኙ በጥንቃቄ የተቀመረ ነው። ዕድሜያችን በጨመረ ቁጥር፣ የአጥንታችንን ጤንነት መጠበቅ ይበልጥ ጠቃሚ እየሆነ ይሄዳል ምክንያቱም እንደወጣትነታችን ጊዜ አጥንታችን ራሱን አያድስም። ይኸውም ለ ኦስቲኦፖሮሲስ ይዳርገናል - በተለይ ደግሞ ደም-በቆረጡ (የወር-አበባ ማየት ባቆሙ) ሴቶች ላይ ይህ ነገር እየተለመደ መጥቷል።

አጥንት ህይወት ያለው ህብረ-ህዋስ ሲሆን ጤናማ አጥንትን እንደገና ለመገንባት ከሰውነታችን ጋር በተመጋጋቢ ግንኙነት የተመረኮዘ ነው - አሮጌው አጥንት በ ኦስቲኦክላስትስ አማካኝነት ይሰባበራል እና ደግሞ አዲስ አጥንት በ ኦስቲኦብላስትስ አማካኝነት ይገነባል። በዚህ ሂደት ውስጥ አለመመጣጠን ሊኖር ይችላል፣ የአጥንት መገንባት (መፈጠር) ወይም የአጥንት መጥፋት (መ’ዋጥ) ሊከሰት ይችላል።

ዕድሜያችን ወደ ሰላሳዎቹ አጋማሽ ሲደርስ፣ ከሚገነባው አጥንት የበለጠ የምናጣው አጥንት እየበዛ ይሄዳል። ስለሆነም ወደዚያ የዕድሜ ደረጃ ከመድረሳችን በፊት የተመጣጠነ የአጥንት መጠን መኖሩ አስፈላጊ ነው። አመጋገባችን እና የአኗኗር ዘይቤያችን፣ እንዲሁም ዘረ-መላችን በአጥንት ጤና ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ ያሳርፋሉ።

የደንከሊያ የአጥንት ማጠንከሪያ ፈሳሽ ልዩ ቅይጦችን የያዘ ሲሆን እነዚህም አሚኖ አሲድ ቸላትስ ሲትራትስ  እና ማላትስ  ሲሆኑ እነዚህ ማዕድናት በሁሉም የዕድሜ ክልል ውስጥ ለሚገኙት፣ የምግብ መፈጨት ችግር ላለባቸውም በቀላሉ የሚሰርጉ ናቸው።

ካልሲየም ከተገኙት ሁሉ በተትረፈረፈ መልኩ የሚገኝ መሆኑ የታወቀ ነው፣ ሆኖም ግን በሚገባ መስረግ እንዲችል፣ እንደ ቪታሚን ዲ እና MSM ያሉ ሌሎች ግብዓቶች ያስፈልጉታል። የአጥንት ማጠንከሪያ ፈሳሻችን ሙሉ ለሙሉ እንዲሰርግ በላቁ ባለሙያዎች የተቀመረ ነው።

  • የላቀ የካልሲየም ድብልቅ፣ ለአጥንት ጤና አስፈላጊ የሆኑ ንጥረ ነገሮች ጋር
  • አጥንትን ለማጠንከር ወሳኝ የሆኑ ማዕድናትን እና ቪታሚኖችን የሚያቀርብ
  • የአጥንት ማጠንከሪያ ንጥረ-ነገሮችን በተመጣጠነ ደረጃ ማግኘታችሁን የሚያረጋግጥ
  • ካልሲየም - አጥንትን ለመጠገን
  • ካልሲየም - ሴት ልጅ ደም-ከቆረጠች በኋላ ለሚደርስባት የአጥንት የማዕድን ዴንሲቲ(እፍግታ) ማሽቆልቆልን የሚቀንስ። ዝቅተኛ የሆነ የአጥንት ማዕድን እፍግታ፣ ለ ኦስቲኦፖሮቲክ የአጥንት መሰንጠቅ መንስዔ ነው።
  • ቪታሚን ዲ3፣ ዚንክ እና ማግኒዚየም - ለአጥንት እና ለጡንቻዎች ጤና አስተዋፅዖ አላቸው።
  • ኮፐር - ለአገናኝ ህብረ-ህዋሳት ጤና አስተዋፅዖ አለው
  • ማንጋኒዝ - ለአገናኝ ህብረ-ህዋሳት መፈጠር እና አጥንትን ለመጠገን አስተዋፅዖ አለው
  • MSM(ኤም. ኤስ. ኤም) - በሰውነት ውስጥ ለተለያዩ ዋና ዋና ተግባራት አስፈላጊ የሆነውን ሰልፈር ያቀርብልናል

የደንከሊያ ዩልቲሜት ኦሜጋ 3-6-9 ፕላስ

ጥቅሞቹ

ኦሜጋ 3-6-9 ከአሳ፣ ከፍላክስሲድ እና ከ ቦራዥ ዘይት በጥንቃቄ የተቀመሩ ቅይጦች ናቸው። ሰውነታችን እነዚህን አስፈላጊ ፋቲ አሲዶች ማመንጨት አይችልም፤ እናም ለተለያዩ የሰውነታችን ስራዎች ወሳኝ ከመሆናቸው አንፃር ከምንመገባቸው ምግቦች እና/ወይም በተጨማሪነት ከምንወስዳቸው ነገሮች ማግኘት አለብን።

ኦሜጋ 3 የሚሰራው ከ EPA(ኤኮሳፐንታኖይክ አሲድ) እና DHA (ዶኮሳሄክሳኖይክ አሲድ) ነው። ይህ ፋቲ አሲድ የሰውነት መቆጣጥን ለመቀነስ እና አጠቃላይ የስሜት ሁኔታን ለማሻሻል ይረዳል። የሚገኘውም ዘይታማ አሳዎች ከሆኑት ሳርዲንማክረል እና ሳልሞን ውስጥ ነው። እንዲሁም ደግሞ አሳዎች በተፈጥሯቸው ወደ EPA እና DHA የሚለውጡትን ALA (አልፋ-ሊኖልኒክ አሲድ) ያካተተ ነው። ሰውነታችን ይህን ተግባር በአነስተኛ መጠን ብቻ ነው መለወጥ የሚችለው።

ኦሜጋ 6 በተለያዩ ዘይቶች፣ የአትክልት-ዘር እና ለውዝ ውስጥ ይገኛል። የሚሰራውም ከ ሊኖልኒክ አሲድ እና ጋማ-ሊኖልኒክ አሲድ ነው።

ኦሜጋ 9 በተለያዩ አይነት ምግቦች ውስጥ የሚገኝ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥም በአትክልት-ዘር፣ በለውዝ እና በተለያዩ የአትክልት እና የፍሬ ዘይቶች ውስጥ ይገኛል።

ኦሜጋ 3-6-9 በውስጣቸው ያለው የፋቲ አሲድ ምጣኔ የተስተካከለ እንዲሆን በከፍተኛ ጥንቃቄ የተቀመሩ ናቸው። ምርቶቻችን ከፍተኛ ምጣኔ ያላቸው የ ኦሜጋ 3 ዘይቶችን፣ ከ አሳ እና ከ ፍላክስ ፣ የ ኦሜጋ 6ን ደግሞ ከ ቦራዥ እና ፍላክስ ዘይቶች እንዲሁም ኦሜጋ 9ን ደግሞ በ ኦሊክ አሲድ መልኩ ከ ፍላክስ ዘይት የሚያቀርቡ ናቸው።

የደንከሊያ የ ኦሜጋ 3-6-9 የላቁ የ ኦሜጋ ምርቶች የሚታሸጉት በ ናይትሮጀኒክ  አየር በተሞላ ክፍል ውስጥ ነው፣ ይኸውም ዝቃጭ ቅንጣቶችን የሚያስከትል ኦክሲዴሽን እንዳይፈጠር ለመከላከል ነው።

የሰለኒየም ፕላስ እንክብሎች

ሰለኒየም ፕላስ  እንክብሎች 250 mcg ይስት-ፍሪ(እርሾ-አልባ) የሆነ ሰለኒየም (ኤል-ሰለኖመታይኒን) ያላቸው ሲሆን፣ ይኸውም “ይስት” ለማይስማማቸውም ተጠቃሚዎች ተመራጭ ያደርገዋል።

ሰለኒየም  ጠቃሚ ማዕድን በአፈር ውስጥ የሚገኝ ስለሆነ በአፈሩ ላይ በሚበቅሉት ዕፅዋት አማካኝነት ይገኛል። ይሁን እንጂ፣ የአረም-ማጥፊያ፣ ዝናብ፣ ትነት እንዲሁም የ አፈር አሲዳማነት (PH) በውስጡ ይገኝ የነበረውን መጠን አመናምነውታል።

የደንከሊያ ምርቶች ቅይጥ፤ የሰለኒየምን አንቲኦክሲደንት ጥቅም ይበልጥ ከፍ ለማድረግ፣ ከሌሎች በ ስብ(ፋት) የሚሟሙ ንጥረ-ነገሮች ከሆኑት እንደ ቪታሚን ኢ ጋር ተደማምሮ የተሻሻለ ነው።

ሰለኒየም ጠቃሚ ማዕድን ሲሆን ለተለያዩ የሰውነታችን ተግባሮች ጠቃሚ ነው ይኸውም ዘርን ለመተካት፣ በሽታዎችን እና ፍሪ ራዲካልስ ን ለመከላከል አስፈላጊ ነው።

ቪታሚን ኢ

ህዋሶችን ከ ኦክሲዴቲቭ ውጥረት የሚከላከል ነው።

ከሚከተሉት ነገሮች ነፃ የሆነ፡ ግሉተን፣ ስንዴ፣ የወተት ተዋፅዖ፣ አኩሪ አተር፣ እርሾ፣ ሰው ሰራሽ ማቆያዎች እና ማጣፈጫዎች ነፃ የሆነ።

ፍሎራ ኤድ

የምግብ እንሽርሽሪት የሚካሄድበት የሰውነታችን ክፍል በ ትሪሊዮኖች የሚቆጠሩ ባክቴሪያዎች ያሉበት ክፍል ነው፤ እነዚህም ለጤናማነቱ ድጋፍ የሚያደርጉ ሲሆን፣ እንደ-አጠቃላይ በሽታ የመከላከል አቅማችንን የሚደግፉ ናቸው። እንደ እርጎ፣ ቴምፍ(የኢንዶኔዥያ ምግብ ነው) እና አይብ የመሳሰሉትን የተብላሉ ምግቦች መመገብ ጤናማ ባክቴሪያዎች እንዲበራከቱ ይረዳል። ለገብያ የሚቀርቡት አብዛኞቹ የእርጎ ምርቶች ስኳር የሚጨመርባቸው ስለሆኑ፣ በሆድ እቃችሁ ውስጥ የሚገኙ ጠቃሚ ባክቴሪያዎችን እና መጥፎዎችንም ጭምር የሚመግቡ ናቸው። የምትመገቧቸው ምግቦች የተብላሉ ምግቦችን የማይጨምር ከሆነ፣ ተጨማሪ ምግብ(ሰፕልመንት) መውሰድ ያስፈልጋችኋል። እኛ ከ 3 ነገሮች የቀየጥነው ላክቶባሲለስ አሲዶፊለስ፣ ቢፊዶባክቲሪየም ቢፊዱም፣ እና ቢፊዶባክቲሪየም ኢንፋንቲስ ጠቃሚ ባክቴሪያ ሲሆን የበተፈጥሮ በአንጀት ውስጥ ሊገኝ ይችላል። እያንዳንዷ የምትወስዷቸው እንክብሎች የሆድን አሲድ መቋቋም የሚችሉ እና በታችኛው የምግብ እንሽርሽሪት ክፍል ውስጥ መቀመጥ የሚችሉ ወደ 6 ቢሊዮን ጠቃሚ  ማይክሮ-ኦርጋኒዝምስ  ያላቸው ናቸው ፤ እነዚህም በሆድ እቃችን ውስጥ ያሉትን ጠቃሚ ባክቴሪያዎች በተሻለ መንገድ የሚያበራክቱ ናቸው።

ከሚከተሉት ነገሮች ነፃ የሆነ፡ ግሉተን፣ ስንዴ፣ የወተት ተዋፅዖ፣ አኩሪ አተር፣ እርሾ፣ ሰው ሰራሽ ማቆያዎች እና ማጣፈጫዎች ነፃ የሆነ።

ዩልቲሜት ዲ-ስትረስ

እንደ ሌሎች ሁኔታዎች ሁሉ በዚህ ወከባ በበዛበት ዓለም ውስጥ ጭንቀት ሁሉንም ማህበረሰብ አዳርሷል። ረዘም ላለ ጊዜ የሚያጋጥም ጭንቀት በሰውነታችን ውስጥ ችግር የሚያስከትል እና የበሽታ ተከላካይ ስርዓታችንን የሚያውክ ነው። ዩልቲሜት ዲ-ስትረስ ለጤናማ የጭንቀት ግብረ-መልስ ዑደት የሚሆኑ ጠቃሚ ንጥረ-ነገሮችን ያካተተ ነው። ይህ የላቀ ቀመር ጭንቀትን በተፈጥሯዊ መንገድ ለመቅረፍ የሚያገልግሉ ቪታሚኖች፣ ማዕድናትን እንዲሁም ቦታኒካልስ የያዘ ነው።

ኤች.ጂ.ኤች. ዮዝ ኮምፕሌክስ

ኤች.ጂ.ኤች. ዮዝ ኮምፕሌክስ በገብያ ውስጥ የትም የማይገኝ የእኛ ግኝት ብቻ የሆኑ እና በልዩ ሁኔታ የተቀየጡ አሚኖ አሲዶች፣ ማዕድናት እንዲሁም የባህር ኬልፕ ያሉት ነው። የተቀመረውም “እንደወጣት ረዥም እድሜ እንድትኖሩ” ለመርዳት ነው። የደንከሊያ ኤች.ጂ.ኤች ዮዝ ኮምፕሌክስ ዕድሜያችን በጨመረ ቁጥር የሚለወጡ ተግባራትን የሚደግፍ ነው። ጤናማ የደም ውስጥ የስኳር መጠንን፣ በሽታ ተከላካይን፣ ቆዳችንን፣ እይታችንን፣ የአዕምሮን ተግባር እንዲሁም ወሲባዊ ፍላጎትን የሚደግፍ ነው።

ዩልቲሜት ኢንዛየምስ

ዩልቲሜት ኢንዛየምስ የእንሽርሽሪት ሂደትን እንዲደግፉ የተቀመሩ ናቸው። የእንሽርሽሪት ጤናን እንዲደግፉ ቢቴን HCl፣ Ox ቢሌ እና ሌሎች ጠቃሚ ኢንዛየሞችን ያካተቱ ናቸው። ዩልቲሜት ኢንዛየሞች፤ ሰውነታችን ካርቦሀድሬትን፣ ፕሮቲንን እና ፋትን መሰባበር እና ንጥረ-ነገሮችን ማስረግ እንዲችል የሚረዱ ሲሆን ቆሻሻን በፍጥነት እንዲወጣ ይረዳሉ።

ዩልቲሜት ናይትሊ ኢሴንስ

ዩልቲሜት ናይትሊ ኢሴንስ የተለያዩ የሰውነት ስርዓቶችን የሚደግፉ ጠቃሚ ኢንዛየሞችን የያዘ ሲሆን የልብ ጤና፣ በሽታ የመከላከል አቅማችንን እንዲሁም አጠቃላይ የሆድ እቃችንን ጤና የሚያሻሽሉ ናቸው። ዩልቲሜት ናይትሊ ኢሴንስ፤ የሆርሞን መጠንን፣ የኮሌስትሮል መጠንን፣ እንዲሁም የቆዳችንን ጤና የሚያሻሽሉ ናቸው።

ቪታሚን ዲ3 10,000 IU

የደንከሊያ ቪታሚን ዲ3 10,000 IU (250µg) እንክብሎች ቪታሚን ዲ ን ከ ቪታሚን ኬ1 እና ኬ2 ጋር የያዙ እና ይበልጥ ለሰውንት ተስማሚ በሆነው ዲ3 መልኩ በላቀ ሁኔታ የተቀመሩ እንክብሎች ናቸው። የተስተካከል ጤናን የሚደግፉ ሲሆን፣ “ከፀሀይ ስለሚገኝ ቪታሚን” ጥቅም በብዛት እና በተጠናገረ መልኩ ተገልጿል፣ በተለይ ደግሞ በሽታን ለመከላከል ያለው አስተዋፅዖ ጠቃሚ ነው።

በዓለማችን ላይ ከ7 ቢሊዮን ሰዎች በላይ አነስተኛ የቪታሚን ዲ ያላቸው ሲሆን ቪታሚን ዲ  በ ፋት የሚሟሟ

እና የካልሲየም የስርገት መጠንን የሚጨምር ሲሆን ይኸውም ጤናማ አጥንት እና ጥርስ እንዲኖረን የሚረዳን ነው። የላቁ የቪታሚን ዲ3 ንጥረ-ነገሮች በከፍተኛ ሁኔታ መስረግ የሚችሉ ቪታሚን ዲ ከመሆናቸው ባሻገር የአመጋገብ ዘያችሁን ለመቀየር እና፣ በቀዝቃዛዎቹ የ ዊንተር ወራት የቪታሚን ዲ ሰፕልመንትን መውሰድ የተሻለ ነገር ነው።

ቪታሚን ዲ ያለው አስተዋፅዖ፤

  • ለጤናማ የበሽታ ተከላካይ ስርዓት
  • አጥንትን እና ጥርስን በጤናማ ሁኔታ ለመጠገን
  • ለጤናማ የካልሲየም እና የፎስፈረስ ስርገት
  • በድም ውስጥ የካልሲየም መጠን ጤናማ እንዲሆን አስተዋፅዖ በማድረግ
  • የጡንቻን ተግባር በጤናማ መልኩ ለመጠገን

ቪታሚን ኬ ያለው አስተዋፅዖ፤

  • ለጤናማ የደም መርጋት
  • ጤናማ አጥንትን ለመጠገን

ቪታሚን ዲ እና በቡድን ነው የሚሰሩት

ወደ ካልሲየም ሜታቦሊዝም  ከመጣን፣ ቪታሚን ዲ እና በጋራ ነው የሚሰሩት። ሁለቱም ጠቃሚ ሚና አላቸው።


የተሟላ የተለያዩ ቪታሚኖች ማዕድን  ታብሌት - በየቀኑ ከምግብ ጋር ወይም ከምግብ በኋላ 4 ታብሌት መውሰድ፣ ወይም የጤና አማካሪዎ በሚያዝዝዎ መሰረት መውሰድ::

ዩልቲሜት ኦሜጋ 3-6-9 ፕላስ - በየቀኑ ከምግብ ጋር 6 እንክብሎችን እንድትወስዱ ይመከራል፣ ወይም የጤና አማካሪዎ በሚያዝዝዎ መሰረት መውሰድ።

የተሟላ የአጥንት ማጠንከሪያ ፈሳሽ - በየቀኑ 31 ሚሊ(2 የሻይ ማንኪያ) መውሰድ፣ ወይም የጤና አማካሪዎ በሚያዝዝዎ መሰረት መውሰድ። ለጣዕም ከጭማቂ (ጁስ) ወይም ከውሀ ጋር ቀላቅላችሁ መውሰድ።  ከመጠቀማችሁ በፊት በደንብ መነቅነቅ ያስፈልጋል።

ሰለኒየም ፕላስ  - በየቀኑ ከምግብ በኋላ 3 እንክብሎችን እንድትወስዱ ይመከራል፣ ወይም የጤና አማካሪዎ በሚያዝዝዎ መሰረት መውሰድ።

ፍሎራ ኤድ - በየቀኑ ከምግብ ጋር 3 እንክብሎችን እንድትወስዱ ይመከራል፣ ወይም የጤና አማካሪዎ በሚያዝዝዎ መሰረት መውሰድ።

ኤፍ.ጂ.ኤች ዮዝ ኮምፕሌክስ - በየቀኑ ከምግብ ጋር ወይም ከምግብ በኋላ 6 እንክብሎችን እንድትወስዱ ይመከራል፣ ወይም የጤና አማካሪዎ በሚያዝዝዎ መሰረት መውሰድ።

ዩልቲሜት ዲ-ስትረስ - በየቀኑ ከምግብ ጋር ወይም ከምግብ በኋላ 4 እንክብሎችን እንድትወስዱ ይመከራል፣ ወይም የጤና አማካሪዎ በሚያዝዝዎ መሰረት መውሰድ።

ዩልቲሜት ኢንዛየምስ - ከምግብ በፊት 1 እንክብል መውሰድ፣ ወይም የጤና አማካሪዎ በሚያዝዝዎ መሰረት መውሰድ።

ዩልቲሜት ናይትሊ ኢሴንስ - ምግብ ከመመገባችሁ በፊት 2 እንክሎችን መውሰድ ወይም የጤና አማካሪዎ በሚያዝዝዎ መሰረት መውሰድ።

የተሟላ የተለያዩ ቪታሚኖች ማዕድን ታብሌት - የፀሀይ ብርሃን በቀጥታ በማያገኘው መልኩ በቀዝቃዛ እና ደረቅ ቦታ ያስቀምጡት።

ዩልቲሜት ኦሜጋ 3-6-9  - የፀሀይ ብርሃን በቀጥታ በማያገኘው መልኩ በቀዝቃዛ እና ደረቅ ቦታ ያስቀምጡት።

የተሟላ የአጥንት ማጠንከሪያ ፈሳሽ - የፀሀይ ብርሃን በቀጥታ በማያገኘው መልኩ በቀዝቃዛ እና ደረቅ ቦታ ያስቀምጡት፣ እና ከከፈታችሁት በኋላ በፍሪጅ ውስጥ ይቀመጥ። ምርቱ ከፍተኛ ጥራት ያለው በመሆኑ ለረዥም ጊዜ እንዲሁ ቀጥ አድርጋችሁ ካስቀመጣችሁት ሊጠጥር ይችላል። ይህን ለማስወገድ ከመጠቀማችሁ በፊት በሚገባ ነቅንቁት፣ እንዲሁም በፍሪጅ ውስጥ አጋድማችሁ ያስቀምጡት።

ሰለኒየም ፕላስ - የፀሀይ ብርሃን በቀጥታ በማያገኘው መልኩ በቀዝቃዛ እና ደረቅ ቦታ ያስቀምጡት።

ፍሎራ ኤድ - የፀሀይ ብርሃን በቀጥታ በማያገኘው መልኩ በቀዝቃዛ እና ደረቅ ቦታ ያስቀምጡት።

ኤች.ጂ.ኤች (H.G.H.) ዮዝ ኮምፕሌክስ - የፀሀይ ብርሃን በቀጥታ በማያገኘው መልኩ በቀዝቃዛ እና ደረቅ ቦታ ያስቀምጡት።

ዩልቲሜት ዲ-ስትረስ - የፀሀይ ብርሃን በቀጥታ በማያገኘው መልኩ በቀዝቃዛ እና ደረቅ ቦታ ያስቀምጡት።

ዩልቲሜት ኢንዛየምስ - የፀሀይ ብርሃን በቀጥታ በማያገኘው መልኩ በቀዝቃዛ እና ደረቅ ቦታ ያስቀምጡት።

ዩልቲሜት ናይትሊ ኢሴንስ - የፀሀይ ብርሃን በቀጥታ በማያገኘው መልኩ በቀዝቃዛ እና ደረቅ ቦታ ያስቀምጡት።

ቪታሚን ዲ3 10,000 IU - የፀሀይ ብርሃን በቀጥታ በማያገኘው መልኩ በቀዝቃዛ እና ደረቅ ቦታ ያስቀምጡት።

Have Questions?Ask An Expert
The cookie settings on this website are set to 'allow all cookies' to give you the very best experience. Please click Accept Cookies to continue to use the site.
የደንከሊያ የሱስ ማጥፊያ ፓኬት (ታብሌት/ፈሳሽ)
You have successfully subscribed!