ገለፃ
ይህ የበሽታ ተከላካይ አቅምን የሚያጎለብት ፓኬት (ፓውደር/ፓውደር) ጤናማ ለመሆን እና ጤናን ለማስቀጠል ጠቃሚ የሆኑ የንጥረ ነገሮች ድብልቅ ይዘት ያለው ነው፣ በተጨማሪም የበሽታ ተከላካይን ጤናን የሚደግፍ ይዘት አለው። ይኸውም፤ በዘመን አመጣሹ የእርሻ ቴክኖሎጂ ምክንያት ከምግቦቻችን ላይ እየጠፉ የመጡትን በጣም ጠቃሚ እና አስፈላጊ ቪታሚኖችንና ማዕድናትን፣ አሚኖ አሲዶችን እና ጠቃሚ ፋቲ አሲዶችን ለመተካት ታልመው የተዘጋጁ ናቸው። የዚህ ውጤታማ ቀመር ድብልቅ ከ 90 በላይ ጠቃሚ ቪታሚኖችን፣ አሚኖ አሲዶችን እና ተፈጥሯዊ ምግቦችን ይዟል፤ በተጨማሪም ለበለጠ የአጥንት ጥንካሬ ካልሲየም፣ ቪታሚን ዲ3 እና ማግኒዚየም ከእነዚህ በተጨማሪም በአንቲ ኦክሲደንት የበለፀጉትን የእኛን ልዩ የኦሜጋ ዘይት ቅይጥ የያዘ ሲሆን ሰውነታችሁ የ21ኛው ክፍለ-ዘመን ጭንቀት እና ውጥረት እንዲዋጋ ለመርዳት ታልሞ የተዘጋጀ ነው። ይህ ፓኬት በተጨማሪነት የ ደንከሊያ ረስቨራትሮል ፕላስ ይዘት ያለው ነው፤ ይኸውም ህዋሳችንን የሚጎዱ ፍሪ-ራዲካልስን በብቃት መከላከል የሚችሉ እና በከፍተኛ ደረጃ ባዮአቬሌብል የሆኑ የሶስት አንቲኦክሲደንቶች (ረስቨራትሮል፣ እርድ፣ እና ኩዌርሰቲን) ቅይጦች ነው፤ እንዲሁም ደግሞ የደንከሊያ ሰለኒየም ፕላስ ለአብዛኞቹ የሰውነታችን መሰረታዊ ተግባራት፤ ከመዋለድ እስከ መመረዝን እና ፍሪ-ራዲካልስን እስከመዋጋት ጠቃሚ የሆነ ማዕድን ነው።
የዚህ ፓኬት ይዘት፤
የደንከሊያ የተሟሉ የተለያዩ ቪታሚን ማዕድናት ፓውደር
ጥቅሞቹ
ከፍተኛ መጠን ያለው የ ፓይቶኒውትረንት ቅይጥ፣ ከዕፅዋትን የተቀመሙ ግብዓቶች እና ከፍተኛ አንቲኦክሲደንት የያዘ ነው።
የቪታሚን ቢ አይነቶችን በሙሉ የያዘ - የጉልበት መጠናችሁን ከፍ በማድረግ፣ የድካም ስሜቱን እና ድካምን ይቀንሳል
ቪታሚን ቢ1፣ ቢ2፣ ቢ6 እና ቢ12 - የድካምን ስሜትን እና ድካምን በመቀነስ አስተዋፅዖ ያደርጋል
ቪታሚን ሲ - የበሽታ ተከላካይ ስርዓት ስራውን በአግባቡ እንዲሰራ ጠቃሚ የሆነ
ከፍተኛ ጥራት ያላቸው ግብዓቶች፤ የባክቴሪያ ቅይጥንም ያካተቱ ይኸውም ግብዓቶች በከፍተኛ ሁኔታ እንዲሰርጉ የሚያደርግ
በ ፍሪ ራዲካልስ ከሚደርስብን ጉዳት የሚከላከሉ ጠቃሚ የሆኑ አንቲ ኦክሲደንቶች ቪታሚን ኤ፣ ሲ እና ኢ የያዙ። ፍሪ ራዲካልስ የማይሰክኑ ሞለኪውሎች ሲሆኑ በሰውነታችን ውስጥ የሚገኙ ህዋሳትን የሚጎዱ እና የጤና ችግር የሚያስከትሉ እና ያለዕድሜ የሚያስረጁ ናቸው።
ፎሊክ አሲድ ለቀይ የደም ህዋሳት ጤናማ ተግባር አስተዋፅዖ ያለው ነው
- የደንከሊያ የተሟላ የአጥንት ማጠንከሪያ ፓውደር
ጥቅሞቹ፤
እነዚህ የላቁ የአጥንት ማጠንከሪያ ንጥረ-ነገሮች ልዩ ቅይጦችን የያዙ ሲሆን እነዚህም አሚኖ አሲድ ቸላትስ ፣ ሲትራትስ እና ማላትስ ሲሆኑ እነዚህ ማዕድናት በሁሉም የዕድሜ ክልል ውስጥ ለሚገኙት፣ የምግብ መፈጨት ችግር ላለባቸውም በቀላሉ እንዲሰርጉ የሚረዱ ናቸው። ምንም እንኳ ካልሲየም በአጥንት ውስጥ በብዛት የሚገኝ ቢሆንም፣ ሰውነታችን ጥቅም ላይ ሊያውለው የሚችልበት መንገድ በሌሎች ቁልፍ ንጥረ-ነገሮች የሚወሰን ነው፤ ለምሳሌ ቪታሚን ዲ እና MSM (ኤም.ኤስ.ኤም) ሲሆኑ በልህቀት በተቀመረው ውህዳችን ላይ አብረው ተካትተዋል።
o የላቀ የካልሲየም ድብልቅ፣ ለአጥንት ጤና አስፈላጊ የሆኑ ንጥረ ነገሮች ጋር
o አጥንትን ለማጠንከር ወሳኝ የሆኑ ማዕድናትን እና ቪታሚኖችን የሚያቀርብ
o በተመጣጠነ መልኩ የአጥንት ማጠንከሪያ ንጥረ-ነገሮችን እያገኙ እንደሆኑ ማረጋገጥ ለሚፈልጉ ሰዎች ተመራጭ የሆነ
o ካልሲየም አጥንትን ለመጠገን አስፈላጊ ነው
o ካልሲየም ሴት ልጅ ደም-ከቆረጠች በኋላ ለሚደርስባት የአጥንት ማዕድን እፍግታ ማሽቆልቆልን ለመቀነስ ይረዳል። ዝቅተኛ የሆነ የአጥንት ማዕድን እፍግታ፣ ለ ኦስቲኦፖሮቲክ የአጥንት መሰንጠቅ መንስዔ ነው።
o ቪታሚን ዲ3፣ ዚንክ እና ማግኒዚየም አጥንትን እና ጡንቻዎችን ለመጠገን አስተዋፅዖ አላቸው።
o ኮፐር፤ አገናኝ ህብረ-ህዋሳት ለመጠገን አስተዋፅዖ አለው
o ማንጋኒዝ ለአገናኝ ህብረ-ህዋሳት መፈጠር እና አጥንትን ለመጠገን አስተዋፅዖ አለው
o MSM(ኤም. ኤስ. ኤም) - በሰውነት ውስጥ ለተለያዩ ዋና ዋና ተግባራት አስፈላጊ የሆነውን ሰልፈር ያቀርብልናል
የደንከሊያ ዩልቲሜት ኦሜጋ 3-6-9 ፕላስ
ጥቅሞቹ
ኦሜጋ 3-6-9 ከአሳ፣ ከፍላክስሲድ እና ከ ቦራዥ ዘይት በጥንቃቄ የተቀመሩ ቅይጦች ናቸው። ሰውነታችን እነዚህን አስፈላጊ ፋቲ አሲዶች ማመንጨት አይችልም፤ እናም ለተለያዩ የሰውነታችን ስራዎች ወሳኝ ከመሆናቸው አንፃር ከምንመገባቸው ምግቦች እና/ወይም በተጨማሪነት ከምንወስዳቸው ነገሮች ማግኘት አለብን።
ኦሜጋ 3 የሚሰራው ከ EPA(ኤኮሳፐንታኖይክ አሲድ) እና DHA (ዶኮሳሄክሳኖይክ አሲድ) ነው። ይህ ፋቲ አሲድ የሰውነት መቆጣጥን ለመቀነስ እና አጠቃላይ የስሜት ሁኔታን ለማሻሻል ይረዳል። የሚገኘውም ዘይታማ አሳዎች ከሆኑት ሳርዲን፣ ማክረል እና ሳልሞን ውስጥ ነው። እንዲሁም ደግሞ አሳዎች በተፈጥሯቸው ወደ EPA እና DHA የሚለውጡትን ALA (አልፋ-ሊኖልኒክ አሲድ) ያካተተ ነው። ሰውነታችን ይህን ተግባር በአነስተኛ መጠን ብቻ ነው መለወጥ የሚችለው።
ኦሜጋ 6 በተለያዩ ዘይቶች፣ የአትክልት-ዘር እና ለውዝ ውስጥ ይገኛል። የሚሰራውም ከ ሊኖልኒክ አሲድ እና ጋማ-ሊኖልኒክ አሲድ ነው።
ኦሜጋ 9 በተለያዩ አይነት ምግቦች ውስጥ የሚገኝ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥም በአትክልት-ዘር፣ በለውዝ እና በተለያዩ የአትክልት እና የፍሬ ዘይቶች ውስጥ ይገኛል።
ኦሜጋ 3-6-9 በውስጣቸው ያለው የፋቲ አሲድ ምጣኔ የተስተካከለ እንዲሆን በከፍተኛ ጥንቃቄ የተቀመሩ ናቸው። ምርቶቻችን ከፍተኛ ምጣኔ ያላቸው የ ኦሜጋ 3 ዘይቶችን፣ ከ አሳ እና ከ ፍላክስ ፣ የ ኦሜጋ 6ን ደግሞ ከ ቦራዥ እና ፍላክስ ዘይቶች እንዲሁም ኦሜጋ 9ን ደግሞ በ ኦሊክ አሲድ መልኩ ከ ፍላክስ ዘይት የሚያቀርቡ ናቸው።
የደንከሊያ የኦሜጋ 3-6-9 የላቁ የኦሜጋ ምርቶች የሚታሸጉት በናይትሮጀኒክ አየር በተሞላ ክፍል ውስጥ ነው፣ ይኸውም ዝቃጭ ቅንጣቶችን የሚያስከትል ኦክሲዴሽን እንዳይፈጠር ለመከላከል ነው።
የሰለኒየም ፕላስ እንክብሎች
የሰለኒየም ፕላስ እንክብሎች 250 mcg ይስት-ፍሪ(እርሾ-አልባ) የሆነ ሰለኒየም (ኤል-ሰለኖመታይኒን) ያላቸው ሲሆን፣ ይኸውም “ይስት” ለማይስማማቸውም ተጠቃሚዎች ተመራጭ ያደርገዋል።
የሰለኒየም ጠቃሚ ማዕድን በአፈር ውስጥ የሚገኝ ስለሆነ በአፈሩ ላይ በሚበቅሉት ዕፅዋት አማካኝነት ይገኛል። ይሁን እንጂ፣ የአረም-ማጥፊያ፣ ዝናብ፣ ትነት እንዲሁም የ አፈር አሲዳማነት (PH) በውስጡ ይገኝ የነበረውን መጠን አመናምነውታል።
የደንከሊያ ምርቶች ቅይጥ፤ የሰለኒየምን አንቲኦክሲደንት ጥቅም ይበልጥ ከፍ ለማድረግ፣ ከሌሎች በ ስብ(ፋት) የሚሟሙ ንጥረ-ነገሮች ከሆኑት እንደ ቪታሚን ኢ ጋር ተደማምሮ የተሻሻለ ነው።
ሰለኒየም ጠቃሚ ማዕድን ሲሆን ለተለያዩ የሰውነታችን ተግባሮች ጠቃሚ ነው ይኸውም ዘርን ለመተካት፣ በሽታዎችን እና ፍሪ ራዲካልስ ን ለመከላከል አስፈላጊ ነው።
ቪታሚን ኢ
ህዋሶችን ከ ኦክሲዴቲቭ ውጥረት የሚከላከል ነው።
ከሚከተሉት ነገሮች ነፃ የሆነ፡ ግሉተን፣ ስንዴ፣ የወተት ተዋፅዖ፣ አኩሪ አተር፣ እርሾ፣ ሰው ሰራሽ ማቆያዎች እና ማጣፈጫዎች ነፃ የሆነ።
ረስቨራትሮል ፕላስ እንክብሎች
ረስቨራትሮል፤ የፈረንሳዊያን-ፓራዶክስ (አልኮል እና ስኳራማ ምግቦችን እየተመገቡ ጤናማ ሆነው የሚኖሩበት ተቃርኖ) ምክንያት ከሆኑ ዋና ግብዓቶች ውስጥ አንዱ እንደሆነ ይጠቀሳል። ረስቨራትሮል ለልብ-ስርዓት ጤናማ ተግባር አስተዋፅዖ አለው። እያንዳንዷ የረስቨራትሮል ፕላስ እንክብል - በ64 ብርጭቆ ቀይ ወይን ውስጥ ከሚገኝ ረስቨራትሮል ጋር እኩል ይዘት ያላት ናት። ረስቨራትሮል ፕላስ ተፈጥሯዊ ፖሊፌኖል ሲሆን፣ ይህም ማለት በተፈጥሯዊ የዕፅዋት ምግቦች ውስጥ በተትረፈረፈ መልኩ የሚገኝ ውህድ ነው። የዚህ ተፈጥሯዊ ምንጭ ከሆኑት ውስጥ እንደምሳሌ ለመጥቀስ ቀይ ወይን (የወይን ቆዳ)፣ ለውዝ እና አንዳንድ እፅዋት፣ ለምሳሌ የጃፓኖች ኖትዊድ (ፖሊጎኑም ኩስፒዳቱም)።
የእርድ ስር
ከእርድ ስር የሚቀመም - ይህ ለምግብ ግብዓት የሚሆን ቅመም ብቻ አይደለም፣ ይህ በጣም ደማቅ ቅመም ጤናማ የሚያደርጉ የተለያዩ ባህሪያት ያሉት ነው። የደንከሊያ ከእርድ ስር የሚቀመሙ ንጥረ-ነገሮች ደረጃቸውን የጠበቁ የተመጠነ ይዘት ያላቸው ናቸው፤ ይህም ማለት በእያንዳንዷ እንክብል ውስጥ እኩል ይዘት ያለው ግብዓት እንደምታገኙ የተረጋገጠ ነው።
በእርድ ውስጥ ከሚገኙ ግብዓቶች ውስጥ ኩርኩሚኖይድስ የሚባሉት ጠቃሚ ፍላቮኖይድስ ይካተታሉ እነዚህም ዕፅዋትን መሰረት ያደረጉ አንቲ-ኦክሲደንቶች ናቸው። በሰውነታችን ውስጥ ህዋሳትን የሚጎዱ ፍሪ-ራዲካልስ ን ለመዋጋት ይረዳሉ። ነባር መገኛው በደቡብ ምስራቅ ኤዥያ ሲሆን፣ እርድ በዝንጅብል ቤተሰብ ውስጥ የሚመደብ እና በባህላዊ አዩርቬዲክ ለረዥም ጊዜ ታሪክ ያለው ነው።
ኩዌርሰቲን
ኩዊርሴቲን የዕፅዋት የቀለም ምንጭ (ፍላቮኖይድ) ነው። በተለያዩ ዕፅዋት እና ምግቦች ውስጥ የሚገኝ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥም ቀይ ወይን፣ ሽንኩርት፣ አረንጓዴ ሻይ፣ ፖም፣ ቤሪ፣ ጂንኮ ቢሎባ፣ St. John's wort, American elder, እንዲሁም በሌሎችም ይገኛል። የ “በክዊት” ሻይ ከፍተኛ የኩዊርሴቲን መጠን አለው። ሰዎች ኩዊርሴቲን እንደ መድሃኒትነት ይጠቀሙበታል። ፍላቮኖይዶች ፍሪ ራዲካልስን የማምከን ችሎታ አላቸው፤ ደካማ ሪያክቲቭ ውህዶች እንዲሆኑ በማድረግ ህዋሳንት የመጉዳት ችሎታቸውን ይቀንሱታል። ኩዊርሴቲን በጥልቀት ምርምር እና በሰው ላይ ሙከራ የተካሄደበት ባዮፍላቮኖይድ ሲሆን ሳይንቲስቶችም ለጤና ያለውን ጥቅም አረጋግጠዋል። በቅርብ ጊዜ ከተካሄዱት ጥናቶች አንዱ ለልብ ጤና ያለውን ጥቅም ገልጿል፤ ስለዚህ አስደናቂ ንጥረ-ነገር ይበልጥ ማወቅ ከፈለጋችሁ፣ በቀላሉ ኦንላይን ላይ መመልከት ትችላላችሁ። እንዲሁም ደግሞ ከ አንቲ-ኦክሲደንት ባህሪው በተጨማሪ በ ሂስታሚነስ የምርት እና የልቀት ሂደት ላይ አስተዋፅዖ አለው።
ከሚከተሉት ነገሮች ነፃ የሆነ፡ ግሉተን፣ ስንዴ፣ የወተት ተዋፅዖ፣ አኩሪ አተር፣ እርሾ፣ ሰው ሰራሽ ማቆያዎች እና ማጣፈጫዎች ነፃ የሆነ።