ገለፃ
የደንከሊያ የአጥንት ማጠንከሪያ ፖውደር የአጥንት ጤናዎን የሚደግፉ 7 ዋና ዋና ንጥረ ነገሮችን እንዲያገኙ በጥንቃቄ የተቀመረ ነው። ዕድሜያችን በጨመረ ቁጥር፣ የአጥንታችንን ጤንነት መጠበቅ ይበልጥ ጠቃሚ እየሆነ ይሄዳል ምክንያቱም እንደወጣትነታችን ጊዜ አጥንታችን ራሱን አያድስም። ይኸውም ለ “ኦስቲኦፖሮሲስ” ይዳርገናል - በተለይ ደግሞ ደም በቆረጡ (የወር-አበባ ማየት ባቆሙ) ሴቶች ላይ ይህ ነገር እየተለመደ መጥቷል።
አጥንት ህይወት ያለው ህብረ-ህዋስ ሲሆን ጤናማ አጥንትን እንደገና ለመገንባት ከሰውነታችን ጋር በተመጋጋቢ ግንኙነት የተመረኮዘ ነው - አሮጌው አጥንት በ “ኦስቲኦክላስትስ” አማካኝነት ይሰባበራል እና ደግሞ አዲስ አጥንት በ “ኦስቲኦብላስትስ” አማካኝነት ይገነባል። በዚህ ሂደት ውስጥ አለመመጣጠን ሊኖር ይችላል፣ የአጥንት መገንባት (መፈጠር) ወይም የአጥንት መጥፋት (መ’ዋጥ) ሊከሰት ይችላል።
ዕድሜያችን ወደ ሰላሳዎቹ አጋማሽ ሲደርስ፣ ከሚገነባው አጥንት የበለጠ የምናጣው አጥንት እየበዛ ይሄዳል። ስለሆነም ወደዚያ የዕድሜ ደረጃ ከመድረሳችን በፊት የተመጣጠነ የአጥንት መጠን መኖሩ አስፈላጊ ነው። አመጋገባችን እና የአኗኗር ዘይቤያችን፣ እንዲሁም ዘረ-መላችን በአጥንት ጤና ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ ያሳርፋሉ።
የደንከሊያ የአጥንት ማጠንከሪያ ፖውደር ልዩ ቅይጦችን የያዘ ሲሆን እነዚህም “አሚኖ አሲድ ቸላትስ”፣ “ሲትራትስ” እና “ማላትስ” ሲሆኑ እነዚህ ማዕድናት በሁሉም የዕድሜ ክልል ውስጥ ለሚገኙት፣ የምግብ መፈጨት ችግር ላለባቸውም በቀላሉ የሚሰርጉ ናቸው።
ካልሲየም ከተገኙት ሁሉ በተትረፈረፈ መልኩ የሚገኝ መሆኑ የታወቀ ነው፣ ሆኖም ግን በሚገባ መስረግ እንዲችል፣ እንደ ቪታሚን ዲ እና MSM ያሉ ሌሎች ግብዓቶች ያስፈልጉታል። የአጥንት ማጠንከሪያ ፖውደራችን ሙሉ ለሙሉ እንዲሰርግ በላቁ ባለሙያዎች የተቀመረ ነው።
- የላቀ የካልሲየም ድብልቅ፣ ለአጥንት ጤና አስፈላጊ የሆኑ ንጥረ ነገሮች ጋር
- አጥንትን ለማጠንከር ወሳኝ የሆኑ ማዕድናትን እና ቪታሚኖችን የሚያቀርብ
- የአጥንት ማጠንከሪያ ንጥረ-ነገሮችን በተመጣጠነ ደረጃ ማግኘታችሁን የሚያረጋግጥ
- ካልሲየም - አጥንትን የሚጠግን
- ካልሲየም - ሴት ልጅ ደም-ከቆረጠች በኋላ ለሚደርስባት የአጥንት ማዕድን እፍግታ ማሽቆልቆልን የሚቀንስ። ዝቅተኛ የሆነ የአጥንት ማዕድን እፍግታ፣ ለ ኦስቲኦፖሮቲክ የአጥንት መሰንጠቅ መንስዔ ነው።
- ቪታሚን ዲ3፣ ዚንክ እና ማግኒዚየም - ለአጥንት እና ለጡንቻዎች ጤና አስተዋፅዖ አላቸው።
- ኮፐር - ለአገናኝ ህብረ-ህዋሳት ጤና አስተዋፅዖ አለው
- ማንጋኒዝ - ለአገናኝ ህብረ-ህዋሳት መፈጠር እና አጥንትን ለመጠገን አስተዋፅዖ አለው
- MSM(ኤም. ኤስ. ኤም) - በሰውነት ውስጥ ለተለያዩ ዋና ዋና ተግባራት አስፈላጊ የሆነውን ሰልፈር ያቀርብልናል
ከሚከተሉት ነገሮች ነፃ የሆነ፤ ግሉተን፣ ስንዴ፣ ከወተት ተዋፅዖ፣ እርሾ ነፃ የሆነ