የአጥንት እና የመገጣጠሚያ ማጠንከሪያ ፓኬት (ፈሳሽ/ፓውደር)

$260.95
  • A powerful combination of our Complete Multi-Vitamin Mineral Liquid, Bone Support Powder and Ultimate Omegas 3-6-9 Plus, with added Joint Aid Caps containing glucosamine considered to be the building blocks of bones and cartilage
  • Containing over 60 Plant Derived Minerals, 16 Vitamins, 12 Amino Acids, 3 Essential Fatty Acids. Plus extra Glucosamine.
  • Highly absorbable forms of nutrients and necessary co-factors
  • Rich in antioxidants (vitamins A, C and E) protecting against free radical damage
Size Guide
$260.95

ገለፃ

የአጥንት እና የመገጣጠሚያ ማጠንከሪያ ፓኬት (ፈሳሽ/ፓውደር)፤ ጤናማ ለመሆን እና ጤናን ለማስቀጠል ጠቃሚ የሆኑ የንጥረ ነገሮች ድብልቅ እና ተጨማሪ የአጥንት ማጠንከሪያ ይዘት ያለው ነው። ይኸውም፤ በዘመን አመጣሹ የእርሻ ቴክኖሎጂ ምክንያት ከምግቦቻችን ላይ እየጠፉ የመጡትን በጣም ጠቃሚ እና አስፈላጊ ቪታሚኖችንና ማዕድናትን፣ አሚኖ አሲዶችንና ጠቃሚ ፋቲ አሲዶችን ለመተካት ታልመው የተዘጋጁ ናቸው። የዚህ ውጤታማ ቀመር ድብልቅ ከ 90 በላይ ጠቃሚ ቪታሚኖችን፣ አሚኖ አሲዶችን እና ተፈጥሯዊ ምግቦችን ይዟል፣ ለበለጠ የአጥንት ጥንካሬ ካልሲየምቪታሚን ዲ3 እና ማግኒዚየምን አካቷል፣ ከእነዚህ በተጨማሪም የእኛን ልዩ የኦሜጋ ዘይት ቅይጥ እና የደም ግሉኮስ ማመጣጠኛ ጋር ተጣምሮ የቀረበ ነው፤ ይኸውም በአንቲኦክሲደንት የበለፀገ ሲሆን ሰውነታችሁ የ21ኛው ክፍለ-ዘመን ጭንቀት እና ውጥረት እንዲዋጋ ለመርዳት ታልሞ የተዘጋጀ ነው።

የዚህ ፓኬት ይዘት:

የደንከሊያ የተሟሉ የተለያዩ ቪታሚን ማዕድናት ፈሳሽ

ጥቅሞቹ

ከፍተኛ መጠን ያለው የ ፓይቶኒውትረንት  ቅይጥ፣ ከዕፅዋትን የተቀመሙ ግብዓቶች እና ከፍተኛ አንቲኦክሲደንት የያዘ ነው።

ቪታሚን ቢ አይነቶችን በሙሉ የያዘ - የጉልበት መጠናችሁን ከፍ በማድረግ፣ የድካም ስሜቱን እና ድካምን ይቀንሳል

ቪታሚን ቢ1ቢ2ቢ6 እና ቢ12 - የድካምን ስሜትን እና ድካምን በመቀነስ አስተዋፅዖ ያደርጋል

ቪታሚን ሲ - የበሽታ ተከላካይ ስርዓት ስራውን በአግባቡ እንዲሰራ ጠቃሚ የሆነ

ከፍተኛ ጥራት ያላቸው ግብዓቶች፤ የባክቴሪያ ቅይጥንም ያካተቱ ይኸውም ግብዓቶች በከፍተኛ ሁኔታ እንዲሰርጉ የሚያደርግ

ፍሪ ራዲካልስ ከሚደርስብን ጉዳት የሚከላከሉ ጠቃሚ የሆኑ አንቲ ኦክሲደንቶች  ቪታሚን ኤ እና የያዙ። ፍሪ ራዲካልስ የማይሰክኑ ሞለኪውሎች  ሲሆኑ በሰውነታችን ውስጥ የሚገኙ ህዋሳትን የሚጎዱ እና የጤና ችግር የሚያስከትሉ እና ያለዕድሜ የሚያስረጁ ናቸው።

ፎሊክ አሲድ  ለቀይ የደም ህዋሳት ጤናማ ተግባር አስተዋፅዖ ያለው ነው

ከሚከተሉት ነገሮች ነፃ የሆነ፡ ግሉተን፣ ስንዴ፣ የወተት ተዋፅዖ፣ አኩሪ አተር፣ እርሾ፣ ሰው ሰራሽ ማቆያዎች እና ማጣፈጫዎች ነፃ የሆነ።

የደንከሊያ ዩልቲሜት ኦሜጋ 3-6-9 ፕላስ

ጥቅሞቹ

ኦሜጋ 3-6-9 ከአሳ፣ ከፍላክስሲድ እና ከቦራዥ ዘይት በጥንቃቄ የተቀመሩ ቅይጦች ናቸው። ሰውነታችን እነዚህን አስፈላጊ ፋቲ አሲዶች ማመንጨት አይችልም፤ እናም ለተለያዩ የሰውነታችን ስራዎች ወሳኝ ከመሆናቸው አንፃር ከምንመገባቸው ምግቦች እና/ወይም በተጨማሪነት ከምንወስዳቸው ነገሮች ማግኘት አለብን።

ኦሜጋ 3 የሚሰራው ከ EPA(ኤኮሳፐንታኖይክ አሲድ) እና DHA (ዶኮሳሄክሳኖይክ አሲድ) ነው። ይህ ፋቲ አሲድ የሰውነት መቆጣጥን ለመቀነስ እና አጠቃላይ የስሜት ሁኔታን ለማሻሻል ይረዳል። የሚገኘውም ዘይታማ አሳዎች ከሆኑት ሳርዲንማክረል እና ሳልሞን ውስጥ ነው። እንዲሁም ደግሞ አሳዎች በተፈጥሯቸው ወደ EPA እና DHA የሚለውጡትን ALA (አልፋ-ሊኖልኒክ አሲድ) ያካተተ ነው። ሰውነታችን ይህን ተግባር በአነስተኛ መጠን ብቻ ነው መለወጥ የሚችለው።

ኦሜጋ 6 በተለያዩ ዘይቶች፣ የአትክልት-ዘር እና ለውዝ ውስጥ ይገኛል። የሚሰራውም ከ ሊኖልኒክ አሲድ እና ጋማ-ሊኖልኒክ አሲድ ነው።

ኦሜጋ 9 በተለያዩ አይነት ምግቦች ውስጥ የሚገኝ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥም በአትክልት-ዘር፣ በለውዝ እና በተለያዩ የአትክልት እና የፍሬ ዘይቶች ውስጥ ይገኛል።

ኦሜጋ 3-6-9 በውስጣቸው ያለው የፋቲ አሲድ ምጣኔ የተስተካከለ እንዲሆን በከፍተኛ ጥንቃቄ የተቀመሩ ናቸው። ምርቶቻችን ከፍተኛ ምጣኔ ያላቸው የ ኦሜጋ 3 ዘይቶችን፣ ከ አሳ እና ከ ፍላክስ ፣ የ ኦሜጋ 6ን ደግሞ ከ ቦራዥ እና ፍላክስ ዘይቶች እንዲሁም ኦሜጋ 9ን ደግሞ በ ኦሊክ አሲድ መልኩ ከፍላክስ ዘይት የሚያቀርቡ ናቸው።

የደንከሊያ የ ኦሜጋ 3-6-9 የላቁ የ ኦሜጋ ምርቶች የሚታሸጉት በ ናይትሮጀኒክ  አየር በተሞላ ክፍል ውስጥ ነው፣ ይኸውም ዝቃጭ ቅንጣቶችን የሚያስከትል ኦክሲዴሽን እንዳይፈጠር ለመከላከል ነው።

ከሚከተሉት ነገሮች ነፃ የሆነ፡ ግሉተን፣ ስንዴ፣ የወተት ተዋፅዖ፣ አኩሪ አተር፣ እርሾ፣ ሰው ሰራሽ ማቆያዎች እና ማጣፈጫዎች ነፃ የሆነ።

የደንከሊያ የአጥንት ማጠንከሪያ ፓውደር

የደንከሊያ የአጥንት ማጠንከሪያ ፓውደር የአጥንት ጤናዎን የሚደግፉ 7 ዋና ዋና ንጥረ ነገሮችን እንዲያገኙ በጥንቃቄ የተቀመረ ነው። ዕድሜያችን በጨመረ ቁጥር፣ የአጥንታችንን ጤንነት መጠበቅ ይበልጥ ጠቃሚ እየሆነ ይሄዳል ምክንያቱም እንደወጣትነታችን ጊዜ አጥንታችን ራሱን አያድስም። ይኸውም ለ ኦስቲኦፖሮሲስ ይዳርገናል - በተለይ ደግሞ ደም-በቆረጡ (የወር-አበባ ማየት ባቆሙ) ሴቶች ላይ ይህ ነገር እየተለመደ መጥቷል።

አጥንት ህይወት ያለው ህብረ-ህዋስ ሲሆን ጤናማ አጥንትን እንደገና ለመገንባት ከሰውነታችን ጋር በተመጋጋቢ ግንኙነት የተመረኮዘ ነው - አሮጌው አጥንት በ ኦስቲኦክላስትስ አማካኝነት ይሰባበራል እና ደግሞ አዲስ አጥንት በ ኦስቲኦብላስትስ አማካኝነት ይገነባል። በዚህ ሂደት ውስጥ አለመመጣጠን ሊኖር ይችላል፣ የአጥንት መገንባት (መፈጠር) ወይም የአጥንት መጥፋት (መ’ዋጥ) ሊከሰት ይችላል።

ዕድሜያችን ወደ ሰላሳዎቹ አጋማሽ ሲደርስ፣ ከሚገነባው አጥንት የበለጠ የምናጣው አጥንት እየበዛ ይሄዳል። ስለሆነም ወደዚያ የዕድሜ ደረጃ ከመድረሳችን በፊት የተመጣጠነ የአጥንት መጠን መኖሩ አስፈላጊ ነው። አመጋገባችን እና የአኗኗር ዘይቤያችን፣ እንዲሁም ዘረ-መላችን በአጥንት ጤና ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ ያሳርፋሉ።

የደንከሊያ የአጥንት ማጠንከሪያ ፓውደር ልዩ ቅይጦችን የያዘ ሲሆን እነዚህም አሚኖ አሲድ ቸላትስሲትራትስ  እና ማላትስ  ሲሆኑ እነዚህ ማዕድናት በሁሉም የዕድሜ ክልል ውስጥ ለሚገኙት፣ የምግብ መፈጨት ችግር ላለባቸውም በቀላሉ የሚሰርጉ ናቸው።

ካልሲየም ከተገኙት ሁሉ በተትረፈረፈ መልኩ የሚገኝ መሆኑ የታወቀ ነው፣ ሆኖም ግን በሚገባ መስረግ እንዲችል፣ እንደ ቪታሚን ዲ እና MSM ያሉ ሌሎች ግብዓቶች ያስፈልጉታል። የአጥንት ማጠንከሪያ ፖውደራችን ሙሉ ለሙሉ እንዲሰርግ በብቁ ባለሙያዎች የተቀመረ ነው።

  • የላቀ የካልሲየም ድብልቅ፣ ለአጥንት ጤና አስፈላጊ ከሆኑ ንጥረ ነገሮች ጋር
  • አጥንትን ለማጠንከር ወሳኝ የሆኑ ማዕድናትን እና ቪታሚኖችን የሚያቀርብ
  • የአጥንት ማጠንከሪያ ንጥረ-ነገሮችን በተመጣጠነ ደረጃ ማግኘታችሁን የሚያረጋግጥ
  • ካልሲየም - አጥንትን ለመጠገን
  • ካልሲየም - ሴት ልጅ ደም-ከቆረጠች በኋላ ለሚደርስባት የአጥንት የማዕድን ዴንሲቲ(እፍግታ) ማሽቆልቆልን የሚቀንስ። ዝቅተኛ የሆነ የአጥንት ማዕድን እፍግታ፣ ለ ኦስቲኦፖሮቲክ የአጥንት መሰንጠቅ መንስዔ ነው።
  • ቪታሚን ዲ3ዚንክ እና ማግኒዚየም - ለአጥንት እና ለጡንቻዎች ጤና አስተዋፅዖ አላቸው።
  • ኮፐር - ለአገናኝ ህብረ-ህዋሳት ጤና አስተዋፅዖ አለው
  • ማንጋኒዝ - ለአገናኝ ህብረ-ህዋሳት መፈጠር እና አጥንትን ለመጠገን አስተዋፅዖ አለው
  • MSM(ኤም. ኤስ. ኤም) - በሰውነት ውስጥ ለተለያዩ ዋና ዋና ተግባራት አስፈላጊ የሆነውን ሰልፈር ያቀርብልናል

ከሚከተሉት ነገሮች ነፃ የሆነ፡ ግሉተን፣ ስንዴ፣ የወተት ተዋፅዖ፣ አኩሪ አተር፣ እርሾ ነፃ የሆነ።

የመገጣጠሚያ መደገፊያ እንክብሎች

መገጣጠሚያዎቻችን ከተለያዩ ክፍሎች የሚገነቡ ሲሆን፤ ከእነዚህ ውስጥም ጡንቻ፣ ጅማት፣ ምራን እና ልምአፅም ይካተታሉ እነዚህም በማዕድን መበልፀግ እና ጤናቸው መጠበቅ ያኖርበታል። እኛ በቀላሉ መንቀሳቀስ የምንችለው በጤናማ መገጣጠሚያዎች እና ልምአፅም ምክንያት ነው። የደንከሊያ ቀመርም ልምአፅምን የሚደግፉ እንደ ግሉኮሳማይን ሀይድሮክሎራይድቢፍ ሀይድሮላይሳት እና MSM(ሜታይልሰልፎኔልሚቴን)ን ያካተቱ ዋና ግብዓቶችን ያቀርባሉ።

ልምአፅም የሚገኘው በአጥንት ጫፍ ላይ ሲሆን፣ ከባድ ክብደትን መሸከም የሚችል፣ በአብዛኛው የገንዛ ክብደታችንን የምንሸከምበት፣ ልምጥምጥ እና ጠንካራ ድጋፍ የሚያደርግ ክፍል ነው። ግሉኮሳማይን በተፈጥሮ በአጥንት እና በልምአፅም ውስጥ የሚገኝ ሲሆን የመገጣጠሚያዎች እና የልምአፅም ዋና ገንቢ እንደሆነ ይታመናል። እነዚህ በሙሉ ከቢፍ ሀይድሮላሴት፣ እና MSM የመገጣጠሚያ ድጋፍ መስጫ እንክብሎች ጋር ሲጣመሩ የላቀ ውጤት ይሰጣሉ።

ከሚከተሉት ነገሮች ነፃ የሆነ፡ ግሉተን፣ ስንዴ፣ አኩሪ አተር፣ እርሾ፣ ሰው ሰራሽ ማቆያዎች እና ማጣፈጫዎች ነፃ የሆነ።

የተሟላ የተለያዩ የቪታሚን ማዕድን ፈሳሽ - በየቀኑ 31 ሚሊ(2 የሻይ ማንኪያ) መውሰድ፣ ለጣዕም ከጭማቂ (ጁስ) ወይም ከውሀ ጋር ቀላቅላችሁ መውሰድ፣ ወይም የጤና አማካሪዎ በሚያዝዝዎ መሰረት መውሰድ። ከመጠቀማችሁ በፊት በደንብ መነቅነቅ ያስፈልጋል።

ዩልቲሜት ኦሜጋ 3-6-9 ፕላስ - በየቀኑ ከምግብ ጋር 3 እንክብሎችን እንድትወስዱ ይመከራል፣ ወይም የጤና አማካሪዎ በሚያዝዝዎ መሰረት መውሰድ።

የተሟላ የተለያዩ ቪታሚኖች ማዕድን ፓውደር - 1 ጎድጓዳ ማንኪያ ከ 250 ሚሊ ውሀ ወይም ጭማቂ(ጁስ) ጋር ቀላቅላችሁ ከምግብ ጋር ወይም ከምግብ በኋላ እንድትወስዱ ይመከራል፣ ወይም የጤና አማካሪዎ በሚያዝዎ መሰረት መውሰድ።

የመገጣጠሚያ ማጠንከሪያ እንክብሎች - በየቀኑ ከምግብ ጋር ወይም ከምግብ በኋላ 4 እንክብሎችን መውሰድ፣ ወይም የጤና አማካሪዎ በሚያዝዝዎ መሰረት መውሰድ

የተሟላ የተለያዩ የቪታሚን ማዕድን ፈሳሽ - የፀሀይ ብርሃን በቀጥታ በማያገኘው መልኩ በቀዝቃዛ እና ደረቅ ቦታ ያስቀምጡት። ከከፈታችሁት በኋላ በፍሪጅ አስቀምጡት።

ዩልቲሜት ኦሜጋ 3-6-9  - የፀሀይ ብርሃን በቀጥታ በማያገኘው መልኩ በቀዝቃዛ እና ደረቅ ቦታ ያስቀምጡት።

የተሟላ የአጥንት ማጠንከሪያ ፓውደር -  የፀሀይ ብርሃን በቀጥታ በማያገኘው መልኩ በቀዝቃዛ እና ደረቅ ቦታ ያስቀምጡት።

የመገጣጠሚያ መደገፊያ እንክብሎች - የፀሀይ ብርሃን በቀጥታ በማያገኘው መልኩ በቀዝቃዛ እና ደረቅ ቦታ ያስቀምጡት።

Have Questions?Ask An Expert
The cookie settings on this website are set to 'allow all cookies' to give you the very best experience. Please click Accept Cookies to continue to use the site.
የአጥንት እና የመገጣጠሚያ ማጠንከሪያ ፓኬት (ፈሳሽ/ፓውደር)
You have successfully subscribed!