ለአዕምሮ እና ለልብ ጤና ፓኬት (ታብሌት/ፓውደር)

$273.95
  • A powerful combination of our Complete Multi-Vitamin Mineral Tablets, Bone Support Powder and Ultimate Omegas 3-6-9 Plus, with added Selenium Plus Capsules to help support the immune system and protect cells from oxidative stress
  • Containing over 60 Plant Derived Minerals, 16 Vitamins, 12 Amino Acids, 3 Essential Fatty Acids at its base with added Selenium and EFA to support healthy brain and heart function
  • Highly absorbable forms of nutrients and necessary co-factors
  • Rich in antioxidants (vitamins A, C and E) protecting against free radical damage
Size Guide
$273.95
ገለፃ

ለአዕምሮ እና ለልብ ጤና ፓኬት (ታብሌት/ፓውደር) ጤናማ ለመሆን እና ጤናን ለማስቀጠል ጠቃሚ የሆኑ የንጥረ ነገሮች ድብልቅ እና ተጨማሪ የአጥንት ማጠንከሪያ ይዘት ያለው ነው። ይኸውም፤ በዘመን አመጣሹ የእርሻ ቴክኖሎጂ ምክንያት ከምግቦቻችን ላይ እየጠፉ የመጡትን በጣም ጠቃሚ እና አስፈላጊ ቪታሚኖችንና ማዕድናትን፣ አሚኖ አሲዶችንና ጠቃሚ ፋቲ አሲዶችን ለመተካት ታልመው የተዘጋጁ ናቸው። የዚህ ውጤታማ ቀመር ድብልቅ ከ 90 በላይ ጠቃሚ ቪታሚኖችን፣ አሚኖ አሲዶችን እና ተፈጥሯዊ ምግቦችን ይዟል፣ ለበለጠ የአጥንት ጥንካሬ ካልሲየም፣ ቪታሚን ዲ3 እና ማግኒዚየምን አካቷል፣ ከእነዚህ በተጨማሪም የእኛን ልዩ የኦሜጋ ዘይት ቅይጥ እና የደም ግሉኮስ ማመጣጠኛ ጋር ተጣምሮ የቀረበ ነው፤ ይኸውም በአንቲኦክሲደንት የበለፀገ ሲሆን ሰውነታችሁ የ21ኛው ክፍለ-ዘመን ጭንቀት እና ውጥረት እንዲዋጋ ለመርዳት ታልሞ የተዘጋጀ ነው።

የዚህ ፓኬት ይዘት፤

የደንከሊያ የተሟሉ የተለያዩ ቪታሚን ማዕድናት ታብሌት

ጥቅሞቹ

ከፍተኛ መጠን ያለው የ ፓይቶኒውትረንት  ቅይጥ፣ ከዕፅዋትን የተቀመሙ ግብዓቶች እና ከፍተኛ አንቲኦክሲደንት የያዘ ነው።

የቪታሚን ቢ አይነቶችን በሙሉ የያዘ - የጉልበት መጠናችሁን ከፍ በማድረግ፣ የድካም ስሜቱን እና ድካምን ይቀንሳል

ቪታሚን ቢ1ቢ2ቢ6 እና ቢ12 - የድካምን ስሜትን እና ድካምን በመቀነስ አስተዋፅዖ ያደርጋል

ቪታሚን ሲ - የበሽታ ተከላካይ ስርዓት ስራውን በአግባቡ እንዲሰራ ጠቃሚ የሆነ

ከፍተኛ ጥራት ያላቸው ግብዓቶች፤ የባክቴሪያ ቅይጥንም ያካተቱ ይኸውም ግብዓቶች በከፍተኛ ሁኔታ እንዲሰርጉ የሚያደርግ

ፍሪ ራዲካልስ ከሚደርስብን ጉዳት የሚከላከሉ ጠቃሚ የሆኑ አንቲ ኦክሲደንቶች  ቪታሚን ኤ፣ እና የያዙ። ፍሪ ራዲካልስ የማይሰክኑ ሞለኪውሎች  ሲሆኑ በሰውነታችን ውስጥ የሚገኙ ህዋሳትን የሚጎዱ እና የጤና ችግር የሚያስከትሉ እና ያለዕድሜ የሚያስረጁ ናቸው።

ፎሊክ አሲድ  ለቀይ የደም ህዋሳት ጤናማ ተግባር አስተዋፅዖ ያለው ነው

ከሚከተሉት ነገሮች ነፃ የሆነ፡ ግሉተን፣ ስንዴ፣ የወተት ተዋፅዖ፣ አኩሪ አተር፣ እርሾ፣ ሰው ሰራሽ ማቆያዎች እና ማጣፈጫዎች ነፃ የሆነ።

 የደንከሊያ የአጥንት ማጠንከሪያ ፓውደር

የደንከሊያ የአጥንት ማጠንከሪያ ፓውደር የአጥንት ጤናዎን የሚደግፉ 7 ዋና ዋና ንጥረ ነገሮችን እንዲያገኙ በጥንቃቄ የተቀመረ ነው። ዕድሜያችን በጨመረ ቁጥር፣ የአጥንታችንን ጤንነት መጠበቅ ይበልጥ ጠቃሚ እየሆነ ይሄዳል ምክንያቱም እንደወጣትነታችን ጊዜ አጥንታችን ራሱን አያድስም። ይኸውም ለ ኦስቲኦፖሮሲስ ይዳርገናል - በተለይ ደግሞ ደም-በቆረጡ (የወር-አበባ ማየት ባቆሙ) ሴቶች ላይ ይህ ነገር እየተለመደ መጥቷል።

አጥንት ህይወት ያለው ህብረ-ህዋስ ሲሆን ጤናማ አጥንትን እንደገና ለመገንባት ከሰውነታችን ጋር በተመጋጋቢ ግንኙነት የተመረኮዘ ነው - አሮጌው አጥንት በ ኦስቲኦክላስትስ አማካኝነት ይሰባበራል እና ደግሞ አዲስ አጥንት በ ኦስቲኦብላስትስ አማካኝነት ይገነባል። በዚህ ሂደት ውስጥ አለመመጣጠን ሊኖር ይችላል፣ የአጥንት መገንባት (መፈጠር) ወይም የአጥንት መጥፋት (መ’ዋጥ) ሊከሰት ይችላል።

ዕድሜያችን ወደ ሰላሳዎቹ አጋማሽ ሲደርስ፣ ከሚገነባው አጥንት የበለጠ የምናጣው አጥንት እየበዛ ይሄዳል። ስለሆነም ወደዚያ የዕድሜ ደረጃ ከመድረሳችን በፊት የተመጣጠነ የአጥንት መጠን መኖሩ አስፈላጊ ነው። አመጋገባችን እና የአኗኗር ዘይቤያችን፣ እንዲሁም ዘረ-መላችን በአጥንት ጤና ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ ያሳርፋሉ።

የደንከሊያ የአጥንት ማጠንከሪያ ፓውደር ልዩ ቅይጦችን የያዘ ሲሆን እነዚህም አሚኖ አሲድ ቸላትስሲትራትስ  እና ማላትስ  ሲሆኑ እነዚህ ማዕድናት በሁሉም የዕድሜ ክልል ውስጥ ለሚገኙት፣ የምግብ መፈጨት ችግር ላለባቸውም በቀላሉ የሚሰርጉ ናቸው።

ካልሲየም ከተገኙት ሁሉ በተትረፈረፈ መልኩ የሚገኝ መሆኑ የታወቀ ነው፣ ሆኖም ግን በሚገባ መስረግ እንዲችል፣ እንደ ቪታሚን ዲ እና MSM ያሉ ሌሎች ግብዓቶች ያስፈልጉታል። የአጥንት ማጠንከሪያ ፖውደራችን ሙሉ ለሙሉ እንዲሰርግ በላቁ ባለሙያዎች የተቀመረ ነው።

  • የላቀ የካልሲየም ድብልቅ፣ ለአጥንት ጤና አስፈላጊ ከሆኑ ንጥረ ነገሮች ጋር

    • አጥንትን ለማጠንከር ወሳኝ የሆኑ ማዕድናትን እና ቪታሚኖችን የሚያቀርብ
    • የአጥንት ማጠንከሪያ ንጥረ-ነገሮችን በተመጣጠነ ደረጃ ማግኘታችሁን የሚያረጋግጥ
    • ካልሲየም - አጥንትን ለመጠገን
    • ካልሲየም - ሴት ልጅ ደም-ከቆረጠች በኋላ ለሚደርስባት የአጥንት የማዕድን ዴንሲቲ(እፍግታ) ማሽቆልቆልን የሚቀንስ። ዝቅተኛ የሆነ የአጥንት ማዕድን እፍግታ፣ ለ ኦስቲኦፖሮቲክ የአጥንት መሰንጠቅ መንስዔ ነው።
    • ቪታሚን ዲ3ዚንክ እና ማግኒዚየም - ለአጥንት እና ለጡንቻዎች ጤና አስተዋፅዖ አላቸው።
    • ኮፐር - ለአገናኝ ህብረ-ህዋሳት ጤና አስተዋፅዖ አለው
    • ማንጋኒዝ - ለአገናኝ ህብረ-ህዋሳት መፈጠር እና አጥንትን ለመጠገን አስተዋፅዖ አለው
    • MSM(ኤም. ኤስ. ኤም) - በሰውነት ውስጥ ለተለያዩ ዋና ዋና ተግባራት አስፈላጊ የሆነውን ሰልፈር ያቀርብልናል

ከሚከተሉት ነገሮች ነፃ የሆነ፡ ግሉተን፣ ስንዴ፣ የወተት ተዋፅዖ፣ አኩሪ አተር፣ እርሾ ነፃ የሆነ።

የደንከሊያ ዩልቲሜት ኦሜጋ 3-6-9 ፕላስ

ጥቅሞቹ

ኦሜጋ 3-6-9 ከአሳ፣ ከፍላክስሲድ እና ከ ቦራዥ ዘይት በጥንቃቄ የተቀመሩ ቅይጦች ናቸው። ሰውነታችን እነዚህን አስፈላጊ ፋቲ አሲዶች ማመንጨት አይችልም፤ እናም ለተለያዩ የሰውነታችን ስራዎች ወሳኝ ከመሆናቸው አንፃር ከምንመገባቸው ምግቦች እና/ወይም በተጨማሪነት ከምንወስዳቸው ነገሮች ማግኘት አለብን።

ኦሜጋ 3 የሚሰራው ከ EPA(ኤኮሳፐንታኖይክ አሲድ) እና DHA (ዶኮሳሄክሳኖይክ አሲድ) ነው። ይህ ፋቲ አሲድ የሰውነት መቆጣጥን ለመቀነስ እና አጠቃላይ የስሜት ሁኔታን ለማሻሻል ይረዳል። የሚገኘውም ዘይታማ አሳዎች ከሆኑት ሳርዲንማክረል እና ሳልሞን ውስጥ ነው። እንዲሁም ደግሞ አሳዎች በተፈጥሯቸው ወደ EPA እና DHA የሚለውጡትን ALA (አልፋ-ሊኖልኒክ አሲድ) ያካተተ ነው። ሰውነታችን ይህን ተግባር በአነስተኛ መጠን ብቻ ነው መለወጥ የሚችለው።

ኦሜጋ 6 በተለያዩ ዘይቶች፣ የአትክልት-ዘር እና ለውዝ ውስጥ ይገኛል። የሚሰራውም ከ ሊኖልኒክ አሲድ እና ጋማ-ሊኖልኒክ አሲድ ነው።

ኦሜጋ 9 በተለያዩ አይነት ምግቦች ውስጥ የሚገኝ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥም በአትክልት-ዘር፣ በለውዝ እና በተለያዩ የአትክልት እና የፍሬ ዘይቶች ውስጥ ይገኛል።

ኦሜጋ 3-6-9 በውስጣቸው ያለው የፋቲ አሲድ ምጣኔ የተስተካከለ እንዲሆን በከፍተኛ ጥንቃቄ የተቀመሩ ናቸው። ምርቶቻችን ከፍተኛ ምጣኔ ያላቸው የ ኦሜጋ 3 ዘይቶችን፣ ከ አሳ እና ከ ፍላክስ ፣ የ ኦሜጋ 6ን ደግሞ ከ ቦራዥ እና ፍላክስ ዘይቶች እንዲሁም ኦሜጋ 9ን ደግሞ በ ኦሊክ አሲድ መልኩ ከ ፍላክስ ዘይት የሚያቀርቡ ናቸው።

የደንከሊያ የ ኦሜጋ 3-6-9 የላቁ የ ኦሜጋ ምርቶች የሚታሸጉት በ ናይትሮጀኒክ  አየር በተሞላ ክፍል ውስጥ ነው፣ ይኸውም ዝቃጭ ቅንጣቶችን የሚያስከትል ኦክሲዴሽን እንዳይፈጠር ለመከላከል ነው።

ከሚከተሉት ነገሮች ነፃ የሆነ፡ ግሉተን፣ ስንዴ፣ የወተት ተዋፅዖ፣ አኩሪ አተር፣ እርሾ፣ ሰው ሰራሽ ማቆያዎች እና ማጣፈጫዎች ነፃ የሆነ።

የሰለኒየም ፕላስ እንክብሎች

ሰለኒየም ፕላስ  እንክብሎች 250 mcg ይስት-ፍሪእርሾ-አልባ) የሆነ ሰለኒየም (ኤል-ሰለኖመታይኒን) ያላቸው ሲሆን፣ ይኸውም “ይስት” ለማይስማማቸውም ተጠቃሚዎች ተመራጭ ያደርገዋል።

ሰለኒየም  ጠቃሚ ማዕድን በአፈር ውስጥ የሚገኝ ስለሆነ በአፈሩ ላይ በሚበቅሉት ዕፅዋት አማካኝነት ይገኛል። ይሁን እንጂ፣ የአረም-ማጥፊያ፣ ዝናብ፣ ትነት እንዲሁም የ አፈር አሲዳማነት (PH) በውስጡ ይገኝ የነበረውን መጠን አመናምነውታል።

የደንከሊያ ምርቶች ቅይጥ፤ የሰለኒየምን አንቲኦክሲደንት ጥቅም ይበልጥ ከፍ ለማድረግ፣ ከሌሎች በ ስብ(ፋት) የሚሟሙ ንጥረ-ነገሮች ከሆኑት እንደ ቪታሚን ኢ ጋር ተደማምሮ የተሻሻለ ነው።

ሰለኒየም ጠቃሚ ማዕድን ሲሆን ለተለያዩ የሰውነታችን ተግባሮች ጠቃሚ ነው ይኸውም ዘርን ለመተካት፣ በሽታዎችን እና ፍሪ ራዲካልስ ን ለመከላከል አስፈላጊ ነው።

ቪታሚን ኢ

ህዋሶችን ከ ኦክሲዴቲቭ ውጥረት የሚከላከል ነው።

ከሚከተሉት ነገሮች ነፃ የሆነ፡ ግሉተን፣ ስንዴ፣ የወተት ተዋፅዖ፣ አኩሪ አተር፣ እርሾ፣ ሰው ሰራሽ ማቆያዎች እና ማጣፈጫዎች ነፃ የሆነ።

የተሟላ የተለያዩ ቪታሚኖች ማዕድን  ታብሌት - በየቀኑ ከምግብ ጋር ወይም ከምግብ በኋላ 4 ታብሌት መውሰድ፣ ወይም የጤና አማካሪዎ በሚያዝዝዎ መሰረት መውሰድ::

ዩልቲሜት ኦሜጋ 3-6-9 ፕላስ - በየቀኑ ከምግብ ጋር 6 እንክብሎችን እንድትወስዱ ይመከራል፣ ወይም የጤና አማካሪዎ በሚያዝዝዎ መሰረት መውሰድ።

የተሟላ የአጥንት ማጠንከሪያ ፓውደር - 1 ጎድጓዳ ማንኪያ ከ 250 ሚሊ ውሀ ወይም ጭማቂ(ጁስ) ጋር ቀላቅላችሁ ከምግብ ጋር ወይም ከምግብ በኋላ መውሰድ፣ ወይም የጤና አማካሪዎ በሚያዝዎ መሰረት መውሰድ።

የሰለኒየም ፕላስ እንክብሎች - በየቀኑ ከምግብ በኋላ 3 እንክብሎችን እንድትወስዱ ይመከራል፣ ወይም የጤና አማካሪዎ በሚያዝዝዎ መሰረት መውሰድ።

ሁሉም እቃ ፀሀይ በቀጥታ በማያገኘው መልኩ በቀዝቃዛ እና ደረቅ ቦታ ይቀመጥ።

ይህን ምርት በፍሪጅ ውስጥ ማስቀመጥ አያስፈልግም።

Have Questions?Ask An Expert
The cookie settings on this website are set to 'allow all cookies' to give you the very best experience. Please click Accept Cookies to continue to use the site.
ለአዕምሮ እና ለልብ ጤና ፓኬት (ታብሌት/ፓውደር)
You have successfully subscribed!