ጉድ ኸርብ ለመተንፈሻ ጤና
ገለፃ
ገለፃ
ጉድ ኸርብ ለመተንፈሻ ጤና ከኬሚካል ነፃ በሆነ ሁኔታ ከተፈጥሯዊ ዕፅዋት የተቀመሙ የመተንፈሻ አካላትን ጤናማ የሚያደርጉ ናቸው። የመተንፈሻ ስርዓታችሁ እርስዎን መተንፈስ የሚያስችሏችሁ፤ በሳንባ ውስጥ የሚገኙ ቀዳዳዎችን፣ የደም ቧንቧዎችን እና ጡንቻዎችን ያካተተ ነው። ይህ ለመተንፈሻ ጤና የተቀመመ ቅይጥ ኦርጋኒክ ወይም ከጫካ የተቀጠፉ ዕፆችን የያዘ ሲሆን ለጤናማ ሳንባ እና ደቂቅ ቱቦ እንዲሁም የመተንፈሻ እና የበሽታ ተከላካይ ስርዓታችን የሚደግፉ ቅይጦችን የያዘ ነው።
የ “ሰፕልመንቱ” ይዘት
የእኛ ግኝት ብቻ የሆኑ ከዕፅዋት የተቀመሙ ቅይጦች (የነጭ ሽንኩርት ራስ፣ የ ሙሊን ቅጠል፣ የ ኦትስትራው ዕፅ፣ የ ብለስድ ቲስል ዕፅ፣ የ ኤለካምፓንግ ስር፣ የ ማርሽማለው ስር፣ የ ቡግልዊድ ዕፅ፣ የ ይርባ ሳንታ ዕፅ)።
ከሚከተሉት ነገሮች ነፃ የሆነ፤ ግሉተን፣ ስንዴ፣ የወተት ተዋፅዖ፣ አኩሪ-አተር፣ እርሾ፣ ከሰው ሰራሽ ማቆያ እና ማጣፈጫዎች ነፃ የሆነ።
የአጠቃቀም መምሪያ
በየቀኑ፣ በቀን ሁለት ጊዜ 2 ml(ሚሊ) መውሰድ ወይም የጤና አማካሪዎ በሚያዝዝዎ መሰረት መውሰድ። አነስተኛ መጠን ወዳለው የተጣራ ውሀ መጨመር ይቻላል።
አቀማመጥ
በቀጥታ ፀሀይ በማያገኘው መልኩ በቀዝቃዛ እና በደረቅ ቦታ ያስቀምጡት። ማቀዝቀዣ (ፍሪጅ) ውስጥ ማስቀመጥ አያስፈልግም።