የደም ግሉኮስ ማመጣጠኛ (ፈሳሽ/ፓውደር)

$237.95
  • A powerful combination of our Complete Multi-Vitamin Mineral Liquid, Bone Support Powder and Ultimate Omegas 3-6-9 Plus and Blood Glucose Support
  • Containing over 60 Plant Derived Minerals, 16 Vitamins, 12 Amino Acids, 3 Essential Fatty Acids plus extra Chromium and specific botanicals to support healthy blood sugar levels
  • Highly absorbable forms of nutrients and necessary co-factors
  • Rich in antioxidants (vitamins A, C and E) protecting against free radical damage
  • Specifically formulated to include extra support for healthy blood sugar levels
Size Guide
$237.95
Add to Wish List

ገለፃ

የደም ግሉኮስ ማመጣጠኛ ፓኬት (ፈሳሽ/ፓውደር)፤ በዘመን አመጣሹ የእርሻ ቴክኖሎጂ ምክንያት ከምግቦቻችን ላይ እየጠፉ የመጡትን በጣም ጠቃሚ እና አስፈላጊ ቪታሚኖችንና ማዕድናትን፣ አሚኖ አሲዶችንና ጠቃሚ ፋቲ አሲዶችን ለመተካት ታልመው የተዘጋጁ ናቸው። የዚህ ውጤታማ ቀመር ድብልቅ ከ 90 በላይ ጠቃሚ ቪታሚኖችን፣ አሚኖ አሲዶችን እና ተፈጥሯዊ ምግቦችን ይዟል፣ ለበለጠ የአጥንት ጥንካሬ ካልሲየም፣ ቪታሚን ዲ3 እና ማግኒዚየምን አካቷል፣ ከእነዚህ በተጨማሪም የእኛን ልዩ የኦሜጋ ዘይት ቅይጥ እና የደም ግሉኮስ ማመጣጠኛ ጋር ተጣምሮ የቀረበ ነው፤ ይኸውም በአንቲኦክሲደንት የበለፀገ ሲሆን ሰውነታችሁ የ21ኛው ክፍለ-ዘመን ጭንቀት እና ውጥረት እንዲዋጋ ለመርዳት ታልሞ የተዘጋጀ ነው።

የዚህ ፖኬት ይዘት

የደንከሊያ የተሟላ የተለያዩ ቪታሚን ማዕድን ፈሳሽ

ጥቅሞቹ

ከፍተኛ መጠን ያለው የ ፓይቶኒውትረንት ቅይጥ፣ ከዕፅዋትን የተቀመሙ ግብዓቶች እና ከፍተኛ አንቲኦክሲደንት የያዘ ነው።

የቪታሚን ቢ አይነቶችን በሙሉ የያዘ - የጉልበት መጠናችሁን ከፍ በማድረግ፣ የድካም ስሜቱን እና ድካምን ይቀንሳል

ቪታሚን ቢ1፣ ቢ2፣ ቢ6 እና ቢ12 - የድካምን ስሜትን እና ድካምን በመቀነስ አስተዋፅዖ ያደርጋል

ቪታሚን ሲ - የበሽታ ተከላካይ ስርዓት ስራውን በአግባቡ እንዲሰራ ጠቃሚ የሆነ

ከፍተኛ ጥራት ያላቸው ግብዓቶች፤ የባክቴሪያ ቅይጥንም ያካተቱ ይኸውም ግብዓቶች በከፍተኛ ሁኔታ እንዲሰርጉ የሚያደርግ

ፍሪ-ራዲካልስ ከሚደርስብን ጉዳት የሚከላከሉ ጠቃሚ የሆኑ አንቲ ኦክሲደንቶች ቪታሚን ኤ፣ ሲ እና የያዙ። ፍሪ-ራዲካልስ የማይሰክኑ ሞለኪውሎች ሲሆኑ በሰውነታችን ውስጥ የሚገኙ ህዋሳትን የሚጎዱ እና የጤና ችግር የሚያስከትሉ እና ያለዕድሜ የሚያስረጁ ናቸው።

ፎሊክ አሲድ ለቀይ የደም ህዋሳት ጤናማ ተግባር አስተዋፅዖ ያለው ነው

ከሚከተሉት ነገሮች ነፃ የሆነ፡ ግሉተን፣ ስንዴ፣ የወተት ተዋፅዖ፣ አኩሪ አተር፣ እርሾ፣ ሰው ሰራሽ ማቆያዎች እና ማጣፈጫዎች ነፃ የሆነ።

የደንከሊያ ዩልቲሜት ኦሜጋ 3-6-9 ፕላስ

ጥቅሞቹ

ኦሜጋ 3-6-9 ከአሳ፣ ከፍላክስሲድ እና ከ ቦራዥ ዘይት በጥንቃቄ የተቀመሩ ቅይጦች ናቸው። ሰውነታችን እነዚህን አስፈላጊ ፋቲ አሲዶች ማመንጨት አይችልም፤ እናም ለተለያዩ የሰውነታችን ስራዎች ወሳኝ ከመሆናቸው አንፃር ከምንመገባቸው ምግቦች እና/ወይም በተጨማሪነት ከምንወስዳቸው ነገሮች ማግኘት አለብን።

ኦሜጋ 3 የሚሰራው ከ EPA(ኤኮሳፐንታኖይክ አሲድ) እና DHA (ዶኮሳሄክሳኖይክ አሲድ) ነው። ይህ ፋቲ አሲድ የሰውነት መቆጣጥን ለመቀነስ እና አጠቃላይ የስሜት ሁኔታን ለማሻሻል ይረዳል። የሚገኘውም ዘይታማ አሳዎች ከሆኑት ሳርዲንማክረል እና ሳልሞን ውስጥ ነው። እንዲሁም ደግሞ አሳዎች በተፈጥሯቸው ወደ EPA እና DHA የሚለውጡትን ALA (አልፋ-ሊኖልኒክ አሲድ) ያካተተ ነው። ሰውነታችን ይህን ተግባር በአነስተኛ መጠን ብቻ ነው መለወጥ የሚችለው።

ኦሜጋ 6 በተለያዩ ዘይቶች፣ የአትክልት-ዘር እና ለውዝ ውስጥ ይገኛል። የሚሰራውም ከ ሊኖልኒክ አሲድ እና ጋማ-ሊኖልኒክ አሲድ ነው።

ኦሜጋ 9 በተለያዩ አይነት ምግቦች ውስጥ የሚገኝ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥም በአትክልት-ዘር፣ በለውዝ እና በተለያዩ የአትክልት እና የፍሬ ዘይቶች ውስጥ ይገኛል።

ኦሜጋ 3-6-9 በውስጣቸው ያለው የፋቲ አሲድ ምጣኔ የተስተካከለ እንዲሆን በከፍተኛ ጥንቃቄ የተቀመሩ ናቸው። ምርቶቻችን ከፍተኛ ምጣኔ ያላቸው የ ኦሜጋ 3 ዘይቶችን፣ ከ አሳ እና ከ ፍላክስ ፣ የ ኦሜጋ 6ን ደግሞ ከ ቦራዥ እና ፍላክስ ዘይቶች እንዲሁም ኦሜጋ 9ን ደግሞ በኦሊክ አሲድ መልኩ ከፍላክስ ዘይት የሚያቀርቡ ናቸው።

የደንከሊያ የኦሜጋ 3-6-9 የላቁ የኦሜጋ ምርቶች የሚታሸጉት በናይትሮጀኒክ  አየር በተሞላ ክፍል ውስጥ ነው፣ ይኸውም ዝቃጭ ቅንጣቶችን የሚያስከትል ኦክሲዴሽን እንዳይፈጠር ለመከላከል ነው።

ከሚከተሉት ነገሮች ነፃ የሆነ፡ ግሉተን፣ ስንዴ፣ የወተት ተዋፅዖ፣ አኩሪ አተር፣ እርሾ፣ ሰው ሰራሽ ማቆያዎች እና ማጣፈጫዎች ነፃ የሆነ።

የደንከሊያ የአጥንት ማጠንከሪያ ፈሳሽ

የደንከሊያ የአጥንት ማጠንከሪያ ፈሳሽ የአጥንት ጤናዎን የሚደግፉ 7 ዋና ዋና ንጥረ ነገሮችን እንዲያገኙ በጥንቃቄ የተቀመረ ነው። ዕድሜያችን በጨመረ ቁጥር፣ የአጥንታችንን ጤንነት መጠበቅ ይበልጥ ጠቃሚ እየሆነ ይሄዳል ምክንያቱም እንደወጣትነታችን ጊዜ አጥንታችን ራሱን አያድስም። ይኸውም ለኦስቲኦፖሮሲስ ይዳርገናል - በተለይ ደግሞ ደም-በቆረጡ (የወር-አበባ ማየት ባቆሙ) ሴቶች ላይ ይህ ነገር እየተለመደ መጥቷል።

አጥንት ህይወት ያለው ህብረ-ህዋስ ሲሆን ጤናማ አጥንትን እንደገና ለመገንባት ከሰውነታችን ጋር በተመጋጋቢ ግንኙነት የተመረኮዘ ነው - አሮጌው አጥንት በኦስቲኦክላስትስ አማካኝነት ይሰባበራል እና ደግሞ አዲስ አጥንት በኦስቲኦብላስትስ አማካኝነት ይገነባል። በዚህ ሂደት ውስጥ አለመመጣጠን ሊኖር ይችላል፣ የአጥንት መገንባት (መፈጠር) ወይም የአጥንት መጥፋት (መ’ዋጥ) ሊከሰት ይችላል።

ዕድሜያችን ወደ ሰላሳዎቹ አጋማሽ ሲደርስ፣ ከሚገነባው አጥንት የበለጠ የምናጣው አጥንት እየበዛ ይሄዳል። ስለሆነም ወደዚያ የዕድሜ ደረጃ ከመድረሳችን በፊት የተመጣጠነ የአጥንት መጠን መኖሩ አስፈላጊ ነው። አመጋገባችን እና የአኗኗር ዘይቤያችን፣ እንዲሁም ዘረ-መላችን በአጥንት ጤና ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ ያሳርፋሉ።

የደንከሊያ የአጥንት ማጠንከሪያ ፈሳሽ ልዩ ቅይጦችን የያዘ ሲሆን እነዚህም አሚኖ አሲድ ቸላትስ ሲትራትስ  እና ማላትስ  ሲሆኑ እነዚህ ማዕድናት በሁሉም የዕድሜ ክልል ውስጥ ለሚገኙት፣ የምግብ መፈጨት ችግር ላለባቸውም በቀላሉ የሚሰርጉ ናቸው።

ካልሲየም ከተገኙት ሁሉ በተትረፈረፈ መልኩ የሚገኝ መሆኑ የታወቀ ነው፣ ሆኖም ግን በሚገባ መስረግ እንዲችል፣ እንደ ቪታሚን ዲ እና MSM ያሉ ሌሎች ግብዓቶች ያስፈልጉታል። የአጥንት ማጠንከሪያ ፈሳሻችን ሙሉ ለሙሉ እንዲሰርግ በላቁ ባለሙያዎች የተቀመረ ነው።

  • የላቀ የካልሲየም ድብልቅ፣ ለአጥንት ጤና አስፈላጊ የሆኑ ንጥረ ነገሮች ጋር
  • አጥንትን ለማጠንከር ወሳኝ የሆኑ ማዕድናትን እና ቪታሚኖችን የሚያቀርብ
  • የአጥንት ማጠንከሪያ ንጥረ-ነገሮችን በተመጣጠነ ደረጃ ማግኘታችሁን የሚያረጋግጥ
  • ካልሲየም - አጥንትን ለመጠገን
  • ካልሲየም - ሴት ልጅ ደም-ከቆረጠች በኋላ ለሚደርስባት የአጥንት የማዕድን ዴንሲቲ(እፍግታ) ማሽቆልቆልን የሚቀንስ። ዝቅተኛ የሆነ የአጥንት ማዕድን እፍግታ፣ ለ ኦስቲኦፖሮቲክ የአጥንት መሰንጠቅ መንስዔ ነው።
  • ቪታሚን ዲ3፣ ዚንክ እና ማግኒዚየም - ለአጥንት እና ለጡንቻዎች ጤና አስተዋፅዖ አላቸው።
  • ኮፐር - ለአገናኝ ህብረ-ህዋሳት ጤና አስተዋፅዖ አለው
  • ማንጋኒዝ - ለአገናኝ ህብረ-ህዋሳት መፈጠር እና አጥንትን ለመጠገን አስተዋፅዖ አለው
  • MSM(ኤም. ኤስ. ኤም) - በሰውነት ውስጥ ለተለያዩ ዋና ዋና ተግባራት አስፈላጊ የሆነውን ሰልፈር ያቀርብልናል

ከሚከተሉት ነገሮች ነፃ የሆነ፡ ግሉተን፣ ስንዴ፣ የወተት ተዋፅዖ፣ አኩሪ አተር፣ እርሾ ነፃ የሆነ።

የደም ጉሉኮስ ማመጣጠኛ

የደም ውስጥ ግሉኮስ ማመጣጠኛ፣ በከፍተኛ ሁኔታ የላቀ የ ክሮሚየም ድብልቅ ሲሆን፣ በዕፅዋት ቀማሚዎች ዘንድ ከፍተኛ ቦታ ከሚሰጣቸው እንደ ቀረፋ፣ ጂምነማ ቅጠል፣ የሆምጣጣ የሀባብ ፍሬ እና ጃምቦላን  ፍሬ ጋር አብሮ የሚቀመም ነው። የክሮሚየም ቅንጣቶች የ ኢንሱሊን  መነቃቃትን የሚጨምሩ እና የ ሜታቦሊዝም  ሂደትን የሚያስተካክሉ ጠቃሚ ማዕድናት ናቸው። እንዲሁም የፕሮቲን፣ የካርቦሀይድሬት እና የ ሊፒድ ሜታቦሊዝምን ይደግፋሉ።

ዋና ግብዓቶች

ጂምነማ  ቅጠል የተቀመመ

ጂምነማ ሲልቨስትሪ  አዩርቬዲክ  ህክምና ውስጥ ለብዙ ክፍለ-ዘመናት የስኳር ህመምን ለማከም ሲጠቀሙበት የኖረ ነው። የ ጂምነማ  የ ሂንዲ ቋንቋ ስም “የስኳር ማጥፊያ” ነው።

ከሆምጣጣ የህንድ ሀባብ የተቀመሙ

ሆምጣጣ ሀባብ ታዋቂነቱ በህንድ ሲሆን፣ ለረዥም ጊዜ የተለያዩ ህመሞችን ለማከም ሲጠቀሙበት የኖሩ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ ታይፕ 2 የስኳር ህመም አንዱ ነው።

ጃምቦላን  ፍሬ የተቀመሙ

ጃሙም  በህንድ ሀገር የሚገኝ ዕፅ ሲሆን የስኳር ህመም መንስዔዎችን ለመቅረፍ የሚያስችል እንደሆነ ይታሰባል። በውስጡም ፋይበር፣ ስብ (ፋት)፣ ፕሮቲን፣ የተለያዩ ቪታሚኖችን እና ማዕድናትን ይዟል። የጃሙም  ፍሬዎች፤ ወደ ሰውነታችን ስርዓት ውስጥ የሚለቀቀውን የስኳር መጠን በማዘግየት፣ በሰውነታችን ውስጥ የሚገኘውን የኢንሱሊን መጠን የሚጨምሩ ጃምቦሊን እና ጃምቦሲን የተባሉ ይዘቶች ያሏቸው ናቸው።

ከሚከተሉት ነገሮች ነፃ የሆነ፡ ግሉተን፣ ስንዴ፣ የወተት ተዋፅዖ፣ አኩሪ አተር፣ እርሾ፣ ሰው ሰራሽ ማቆያዎች እና ማጣፈጫዎች ነፃ የሆነ።

የተሟላ የተለያዩ ቪታሚኖች ማዕድን ፈሳሽ - በየቀኑ 31 ሚሊ(2 የሻይ ማንኪያ) መውሰድ፣ ለጣዕም ከጭማቂ (ጁስ) ወይም ከውሀ ጋር ቀላቅላችሁ መውሰድ፣ ወይም የጤና አማካሪዎ በሚያዝዝዎ መሰረት መውሰድ። ከመጠቀማችሁ በፊት በደንብ መነቅነቅ ያስፈልጋል።

ዩልቲሜት ኦሜጋ 3-6-9 ፕላስ - በየቀኑ ከምግብ ጋር 3 እንክብሎችን እንድትወስዱ ይመከራል፣ ወይም የጤና አማካሪዎ በሚያዝዝዎ መሰረት መውሰድ።

የተሟላ የአጥንት ማጠንከሪያ ፓውደር - 1 ጎድጓዳ ማንኪያ ከ 250 ሚሊ ውሀ ወይም ጭማቂ(ጁስ) ጋር ቀላቅላችሁ ከምግብ ጋር ወይም ከምግብ በኋላ መውሰድ፣ ወይም የጤና አማካሪዎ በሚያዝዎ መሰረት መውሰድ።

የደም ጉሉኮስ ማመጣጠኛ - በየቀኑ ከምግብ በፊት 2 እንክብሎችን መውሰድ፣ ወይም የጤና አማካሪዎ በሚያዝዝዎ መሰረት መውሰድ።

የተሟላ የተለያዩ ቪታሚኖች ማዕድን ፈሳሽ - የፀሀይ ብርሃን በቀጥታ በማያገኘው መልኩ በቀዝቃዛ እና ደረቅ ቦታ ያስቀምጡት። ከከፈታችሁት በኋላ በፍሪጅ ያስቀምጡት።

ዩልቲሜት ኦሜጋ 3-6-9 ፕላስ - የፀሀይ ብርሃን በቀጥታ በማያገኘው መልኩ በቀዝቃዛ እና ደረቅ ቦታ ያስቀምጡት።

የተሟላ የአጥንት ማጠንከሪያ ፓውደር- የፀሀይ ብርሃን በቀጥታ በማያገኘው መልኩ በቀዝቃዛ እና ደረቅ ቦታ ያስቀምጡት።

የደም ጉሉኮስ ማመጣጠኛ - የፀሀይ ብርሃን በቀጥታ በማያገኘው መልኩ በቀዝቃዛ እና ደረቅ ቦታ ያስቀምጡት።

Have Questions?Ask An Expert
The cookie settings on this website are set to 'allow all cookies' to give you the very best experience. Please click Accept Cookies to continue to use the site.
የደም ግሉኮስ ማመጣጠኛ (ፈሳሽ/ፓውደር)
You have successfully subscribed!