የአዕምሮ እና የልብ ጤና ፓኬት (ፓውደር/ፓውደር)

$296.95
  • A powerful combination of our Complete Multi-Vitamin Mineral Powder, Bone Support powder and Ultimate Omegas 3-6-9 Plus, with added Selenium Plus Capsules to help support the immune system and protect cells from oxidative stress
  • Containing over 60 Plant Derived Minerals, 16 Vitamins, 12 Amino Acids, 3 Essential Fatty Acids at its base with added Selenium and EFA to support healthy brain and heart function
  • Highly absorbable forms of nutrients and necessary co-factors
  • Rich in antioxidants (vitamins A, C and E) protecting against free radical damage
Size Guide
$296.95
ገለፃ

አዕምሮን እና ልብን የሚረዱ እጅግ በጣም የተለያዩ ንጥረ-ነገሮችን እና የላቀ ዘመናዊ ህይወት መኖር ለሚፈልጉ ተመራጭ የሆነ። የዘመናችን ዘመናዊ የአስተራረስ ዘዴ ለም የሆነውን የአፈር ክፍል ከሚገባው በላይ ደጋግሞ የሚጠቀም በመሆኑ ምክንያት ለጤና አስፈላጊ የሆኑት፤ ጠቃሚ ቪታሚኖች፣ ማዕድናት፣ አሚኖ አሲድስ እንዲሁም ጠቃሚ ፋቲ አሲዶች ከምግቦቻችን ላይ በመጥፋት ላይ ይገኛሉ። የዚህ ፓኬት ይዘትም፤ የተሟላ የተለያዩ ቪታሚን ማዕድናት ፓውደር፣ 2 x ፕሪሚየም የኦሜጋ ዘይት ቅይጥ፣ የአጥንት ማጠንከሪያ ፓውደር፣ እንዲሁም የሰለኒየም ፕላስ ውጤታም ድብልቆችን የያዘ ሲሆን። ከ90 በላይ ጠቃሚ ቪታሚኖች፣ ማዕድናት፣ አሚኖ አሲድስ፣ እና ጠቃሚ ፋቲ አሲዶች እንዲሁም በተጨማሪ ካልሲየም፣ ቪታሚን ዲ3 እና ማግኒዚየም እና በሽታ የመከላከል አቅምን ከኦክሲዴቲቭ ውጥረት የሚከላከል ተጨማሪ ሰለኒየም  የያዘ ነው።  ይህ ዕለታዊ 90 ፓኬት ፕላስ ፓውደር በንጥረ-ነገሮች የላቀ እንዲሁም በአንቲኦክሲደንትስ የበለፀገ እና ሰውነታችን የዘመናዊ ህይወትን ጭንቀት እና ውጥረት መዋጋት መቋቋም እንዲችል የሚረዱ ከ 115 በላይ ፍራፍሬ እና አትክልቶች ጋር በልዩ ሁኔታ የተቀመሩ እና በተጨማሪነት ከአጥንት ማጠንከሪያ ጋር የቀረቡ ናቸው።

የዚህ ፓኬት ይዘት፤

1 x የደነከሊያ የተሟሉ የተለያዩ ቪታሚን ማዕድናት ፓውደር

ጥቅሞቹ

ከፍተኛ መጠን ያለው የ ፓይቶኒውትረንት  ቅይጥ፣ ከዕፅዋትን የተቀመሙ ግብዓቶች እና ከፍተኛ አንቲኦክሲደንት ያለው ሲሆን 115 አይነት አትክልት እና ፍራፍሬን ያካተተ ነው።

    የቪታሚን ቢ አይነቶችን በሙሉ የያዘ - ዕለታዊ የጉልበት መጠናችሁን ከፍ በማድረግ፣ የድካም ስሜትን እና ድካምን ይቀንሳል

      ቪታሚን ቢ1ቢ2ቢ6 እና ቢ12 - የድካምን ስሜትን እና ድካምን በመቀነስ አስተዋፅዖ ያደርጋል

        ቪታሚን ሲ - የበሽታ ተከላካይ ስርዓት ስራውን በአግባቡ እንዲሰራ ጠቃሚ የሆነ

        ከፍተኛ ጥራት ያላቸው ግብዓቶች፤ የባክቴሪያ ቅይጥንም ያካተቱ ይኸውም ግብዓቶች በከፍተኛ ሁኔታ እንዲሰርጉ የሚያደርግ

        በ ፍሪ ራዲካልስ ከሚደርስብን ጉዳት የሚከላከሉ ጠቃሚ የሆኑ አንቲ ኦክሲደንቶች  ቪታሚን ኤ፣ ሲ እና ኢ የያዙ። ፍሪ ራዲካልስ የማይሰክኑ ሞለኪውሎች  ሲሆኑ በሰውነታችን ውስጥ የሚገኙ ህዋሳትን የሚጎዱ እና የጤና ችግር የሚያስከትሉ እና ያለዕድሜ የሚያስረጁ ናቸው።

        ፎሊክ አሲድ  ለቀይ የደም ህዋሳት ጤናማ ተግባር አስተዋፅዖ ያለው ነው

        2 x ደንከሊያ ዩልቲሜት ኦሜጋ 3-6-9 ፕላስ

        ጥቅሞቹ፤

        • ዩልቲሜት ኦሜጋስ 3-6-9 ከአሳ፣ ከፍላክስሲድ እና ከቦራዥ ዘይት የተገኙ የኦሜጋ 3፣ 6፣ እና 9 ፋቲ አሲዶች ልዩ ቅይጥ ነው። እነዚህ ጠቃሚ ፋትስ ለተለያዩ አካላዊ ተግባራት አስፈላጊ ሲሆኑ ሰውነታችን እነዚህን ፋትስ በራሱ ማመንጨት ስለማይችል የምግባችን አካል መሆን አለባቸው።
        • ኦሜጋ 3 EPA(ኤኮሳፐንታኖይክ አሲድ) እና DHA (ዶኮሳሄክሳኖይክ አሲድ) ያሉት ነው። በአብዛኛው የሚገኘው ዘይታማ አሳዎች በሆኑት ሳርዲንማክረል እና ሳልሞን ውስጥ ነው። እንዲሁም ደግሞ አሳዎች በተፈጥሯቸው ጠቃሚ ወደሆነው EPA እና DHA መለወጥ የሚችሉትን ALA (አልፋ-ሊኖልኒክ አሲድ) ያካተተ ነው፣ ነገር ግን ሰውነታችን አነስተኛ መጠን ብቻ ነው መለወጥ የሚችለው።
        • ኦሜጋ 6 የሚሰራውም ከ ሊኖልኒክ አሲድ እና ጋማ-ሊኖልኒክ አሲድ ነው፤ የሚገኘውም በተለያዩ ዘይቶች እና ለውዝ ውስጥ ነው።
        • ኦሜጋ 9፤ በተፈጥሮ የኦሊክ አሲድ ያለባቸው ምግቦች እንደ ለውዝ እና ዘይት ውስጥ ሊገኝ ይችላል።
        • በእነዚህ ፋቲ አሲዶች መካከል ያለው የሬሾ መጠን በጣም ጠቃሚ ነው፣ በተለይ ደግሞ በኦሜጋ 3 እና በኦሜጋ 6 መካከል ያለው። ኦሜጋ 3-6-9፣ በቀን 3ቴ በሚወሰድ ዶዝ፣ ከአሳ እና ከፍላክስ ከፍተኛ የኦሜጋ 3 ዘይት ሬሾ የሚሰጥ ሲሆን፣ እና ደግሞ ከቦራዥ እና ፍላክስ ዘይት ከፍተኛ ጥራት ያለው የኦሜጋ 6ን የምናገኝ ይሆናል፣ ይኸውም ከኦሊክ አሲድ እንዲሁም ከፍላክስ ዘይት በሚገኝ ኦሜጋ 9ኝ የሚመጣጠን ይሆናል።
        • የአሳ ዘይት ለኦክሲዴሽን ተጋላጭ ነው፤ ይኸውም በምርቱ ላይ ዝቃጭ ቅንጣቶችን ያስከትላሉ። የእኛ የላቁ ዩልቲሜት ኦሜጋ ንጥረ-ነገሮች በናይትሮጂን በተሞላ አየር ክፍል ውስጥ ስለሚሞሉ ጥራቱ እና ደህንነቱ የተጠበቀ ነው።

        1 x የደንከሊያ የተሟላ የአጥንት ማጠንከሪያ ፓውደር

        ጥቅሞቹ፤

        እነዚህ የላቁ የአጥንት ማጠንከሪያ ንጥረ-ነገሮች ልዩ ቅይጦችን የያዙ ሲሆን እነዚህም አሚኖ አሲድ ቸላትስ ሲትራትስ  እና ማላትስ  ሲሆኑ እነዚህ ማዕድናት በሁሉም የዕድሜ ክልል ውስጥ ለሚገኙት፣ የምግብ መፈጨት ችግር ላለባቸውም በቀላሉ እንዲሰርጉ የሚረዱ ናቸው። ምንም እንኳ ካልሲየም በአጥንት ውስጥ በብዛት የሚገኝ ቢሆንም፣ ሰውነታችን ጥቅም ላይ ሊያውለው የሚችልበት መንገድ በሌሎች ቁልፍ ንጥረ-ነገሮች የሚወሰን ነው፤ ለምሳሌ ቪታሚን ዲ እና MSM (ኤም.ኤስ.ኤም) ሲሆኑ በልህቀት በተቀመረው ውህዳችን ላይ አብረው ተካትተዋል።

        o  የላቀ የካልሲየም ድብልቅ፣ ለአጥንት ጤና አስፈላጊ የሆኑ ንጥረ ነገሮች ጋር

        o  አጥንትን ለማጠንከር ወሳኝ የሆኑ ማዕድናትን እና ቪታሚኖችን የሚያቀርብ

        o  በተመጣጠነ መልኩ የአጥንት ማጠንከሪያ ንጥረ-ነገሮችን እያገኙ እንደሆኑ ማረጋገጥ ለሚፈልጉ ሰዎች ተመራጭ የሆነ

        o  ካልሲየም አጥንትን ለመጠገን አስፈላጊ ነው

        o  ካልሲየም ሴት ልጅ ደም-ከቆረጠች በኋላ ለሚደርስባት የአጥንት ማዕድን እፍግታ ማሽቆልቆልን ለመቀነስ ይረዳል። ዝቅተኛ የሆነ የአጥንት ማዕድን እፍግታ፣ ለ ኦስቲኦፖሮቲክ የአጥንት መሰንጠቅ መንስዔ ነው።

        o  ቪታሚን ዲ3፣ ዚንክ እና ማግኒዚየም አጥንትን እና ጡንቻዎችን ለመጠገን አስተዋፅዖ አላቸው።

        o  ኮፐር፤ አገናኝ ህብረ-ህዋሳት ለመጠገን አስተዋፅዖ አለው

        o  ማንጋኒዝ ለአገናኝ ህብረ-ህዋሳት መፈጠር እና አጥንትን ለመጠገን አስተዋፅዖ አለው

        o  MSM(ኤም. ኤስ. ኤም) - በሰውነት ውስጥ ለተለያዩ ዋና ዋና ተግባራት አስፈላጊ የሆነውን ሰልፈር ያቀርብልናል

        1 x ሰለኒየም ፕላስ

        ሰለኒየም ፕላስ እንክብሎች 250 mcg የሰለኒየም ይዘት ያላቸው ሲሆን፣ በተፈጥሮ በአፈር ውስጥ የሚገኝ ጠቃሚ ማዕድን ነው። በሽታ የመከላከል አቅምን የሚያጎለብት እና ህዋሳትን በፍሪ-ራዲካልስ አማካኝነት ከሚመጣ ኦክሲዴቲቭ ውጥረት የሚከላከል ጠቃሚ ማዕድን ነው። ፍሪ ራዲካልስ የማይሰክኑ ሞለኪውሎች  ሲሆኑ በሰውነታችን ውስጥ የሚገኙ ህዋሳትን የሚጎዱ እና የጤና ችግር የሚያስከትሉ እና ያለዕድሜ የሚያስረጁ ናቸው።

        የእኛ ልዩ የሆነው ቅይጥ የሰለኒየምን አንቲኦክሲደንት ጥቅም ይበልጥ ከፍ ለማድረግ፣ ከሌሎች በ ስብ(ፋት) የሚሟሙ ንጥረ-ነገሮች ከሆኑት እንደ ቪታሚን ኢ ጋር ተደማምሮ የተሻሻለ ነው።

        ይህ በእኛ የተቀመረው ልዩ ቅይጥ ይስት አልባ የሆነውን ሰለኒየም(ኤል-ሰለኖመታይኒን) ተጠቅመን የፈጠርነው ሲሆን፣ ይስት ለማይስማማቸውም ተጠቃሚዎች ተመራጭ ያደርገዋል።

        ሰለኒየም መጠናችሁን የተስተካከለ ማድረግ ለፀጉር እና ጥፍር ጤና ጠቃሚ ሲሆን፣ እንዲሁም ደግሞ አጠቃላይ ሜታቦሊዝምን ይደግፋል።

        ቪታሚን ኢ፤

        • ህዋሳትን ከኦክሲዴቲቭ ውጥረት የሚከላከል

        ሰለኒየም፤

        • ለኖርማል ስፐርማቶጀነሲስ
        • ፀጉርን ለመጠገን
        • ጥፍርን ለመጠገን
        • የበሽታ ተከላካይ ስርዓት
        • ለኖርማል የታይሮይድ ዕጢ ተግባር
        • ህዋሳትን ከኦክሲዴቲቭ ውጥረት የሚከላከል

        ከሚከተሉት ነገሮች ነፃ የሆነ፡ ግሉተን፣ ስንዴ፣ የወተት ተዋፅዖ፣ አኩሪ አተር፣ እርሾ፣ ሰው ሰራሽ ማቆያዎች እና ማጣፈጫዎች ነፃ የሆነ።

        የተሟላ የተለያዩ ቪታሚኖች ማዕድን ፓውደር - 1 ጎድጓዳ ማንኪያ ከ 250 ሚሊ ውሀ ወይም ጭማቂ(ጁስ) ጋር ቀላቅላችሁ ከምግብ ጋር ወይም ከምግብ በኋላ እንድትወስዱ ይመከራል፣ ወይም የጤና አማካሪዎ በሚያዝዎ መሰረት መውሰድ።

        ዩልቲሜት ኦሜጋ 3-6-9 ፕላስ - በየቀኑ ከምግብ ጋር 6 እንክብሎችን እንድትወስዱ ይመከራል፣ ወይም የጤና አማካሪዎ በሚያዝዝዎ መሰረት መውሰድ።

        የተሟላ የአጥንት ማጠንከሪያ ፓውደር - 1 ጎድጓዳ ማንኪያ ከ 250 ሚሊ ውሀ ወይም ጭማቂ(ጁስ) ጋር ቀላቅላችሁ ከምግብ ጋር ወይም ከምግብ በኋላ መውሰድ፣ ወይም የጤና አማካሪዎ በሚያዝዎ መሰረት መውሰድ።

        ሰለኒየም ፕላስ እንክብሎች - በየቀኑ ከምግብ በኋላ 3 እንክብሎችን እንድትወስዱ ይመከራል፣ ወይም የጤና አማካሪዎ በሚያዝዝዎ መሰረት መውሰድ።

        ሁሉም እቃ ፀሀይ በቀጥታ በማያገኘው መልኩ በቀዝቃዛ እና ደረቅ ቦታ ይቀመጥ።

        ይህን ምርት በፍሪጅ ውስጥ ማስቀመጥ አያስፈልግም።

        Have Questions?Ask An Expert
        The cookie settings on this website are set to 'allow all cookies' to give you the very best experience. Please click Accept Cookies to continue to use the site.
        የአዕምሮ እና የልብ ጤና ፓኬት (ፓውደር/ፓውደር)
        You have successfully subscribed!