የደንከሊያ ዩልቲሜት የእንሽርሽሪት ፓኬት (ታብሌት/ፈሳሽ)

$379.95
This pack contains the powerful combination of our comprehensive Complete Multi Vitamin Mineral Tablets, Premium Omega Oil Blend, Bone Support Liquid, Flora Aid, Ultimate Enzymes, and Nightly Essense. It contains over 90 key vitamins, minerals, amino acids, and essential fatty acids as well as extra Calcium, Vitamin D3 and magnesium and extra selenium to help support the immune system from oxidative stress.
Size Guide
$379.95

ገለፃ

የእንሽርሽሪት ስርዓትን የሚደግፉና እጅግ በጣም የተለያዩ ንጥረ-ነገሮች የተጨመሩበት እና የላቀ ዘመናዊ ህይወት መኖር ለሚፈልጉ ተመራጭ የሆነ። የዘመናችን ዘመናዊ የአስተራረስ ዘዴ ለም የሆነውን የአፈር ክፍል ከሚገባው በላይ ደጋግሞ የሚጠቀም በመሆኑ ምክንያት ለጤና አስፈላጊ የሆኑት፤ ጠቃሚ ቪታሚኖች፣ ማዕድናት፣ አሚኖ አሲድስ እንዲሁም ጠቃሚ ፋቲ አሲዶች ከምግቦቻችን ላይ በመጥፋት ላይ ይገኛሉ። የዚህ ፓኬት ይዘትም፤ የተሟላ የተለያዩ ቪታሚን ማዕድናት ታብሌት፣ ፕሪሚየም የኦሜጋ ዘይት ቅይጥ፣ የአጥንት ማጠንከሪያ ፈሳሽ፣ ፍሎራ ኤድ፣ ዩልቲሜት ኢንዛየምስ፣ እና ናይትሊ ኢሴንስ የያዘ ነው። ከ90 በላይ ጠቃሚ ቪታሚኖች፣ ማዕድናት፣ አሚኖ አሲድስ፣ እና ጠቃሚ ፋቲ አሲዶች እንዲሁም በተጨማሪ ካልሲየም፣ ቪታሚን ዲ3 እና ማግኒዚየም እና በሽታ የመከላከል አቅምን ከኦክሲዴቲቭ ውጥረት የሚከላከል ተጨማሪ ሰለኒየም  የያዘ ነው።  ይህ የእንሽርሽሪት ስርዓትን የሚደግፍ ፓኬት (ታብሌት/ፈሳሽ)  በአንቲኦክሲደንትስ የበለፀገ እና ሰውነታችን የዘመናዊ ህይወትን ጭንቀት እና ውጥረት መዋጋት መቋቋም እንዲችል የሚረዱ ከ 115 በላይ ፍራፍሬ እና አትክልቶች ጋር በልዩ ሁኔታ የተቀመሩ እና በተጨማሪነት እንሽርሽሪትን ከሚደግፉ ጋር አብረው የቀረቡ ናቸው።

የዚህ ፓኬት ይዘት:

1 x የደነከሊያ የተሟሉ የተለያዩ ቪታሚን ማዕድናት ታብሌት

ጥቅሞቹ

ከፍተኛ መጠን ያለው የ ፓይቶኒውትረንት  ቅይጥ፣ ከዕፅዋትን የተቀመሙ ግብዓቶች እና ከፍተኛ አንቲኦክሲደንት የያዘ ነው።

ቪታሚን ቢ አይነቶችን በሙሉ የያዘ - ዕለታዊ የጉልበት መጠናችሁን ከፍ በማድረግ፣ የድካም ስሜትን እና ድካምን ይቀንሳል

ቪታሚን ቢ1፣ ቢ2፣ ቢ6 እና ቢ12 - የድካምን ስሜትን እና ድካምን በመቀነስ አስተዋፅዖ ያደርጋል

ቪታሚን ሲ - የበሽታ ተከላካይ ስርዓት ስራውን በአግባቡ እንዲሰራ ጠቃሚ የሆነ

ከፍተኛ ጥራት ያላቸው ግብዓቶች፤ የባክቴሪያ ቅይጥንም ያካተቱ ይኸውም ግብዓቶች በከፍተኛ ሁኔታ እንዲሰርጉ የሚያደርግ

ፍሪ ራዲካልስ ከሚደርስብን ጉዳት የሚከላከሉ ጠቃሚ የሆኑ አንቲ ኦክሲደንቶች  ቪታሚን ኤ፣ እና የያዙ። ፍሪ ራዲካልስ የማይሰክኑ ሞለኪውሎች  ሲሆኑ በሰውነታችን ውስጥ የሚገኙ ህዋሳትን የሚጎዱ እና የጤና ችግር የሚያስከትሉ እና ያለዕድሜ የሚያስረጁ ናቸው።

    ፎሊክ አሲድ  ለቀይ የደም ህዋሳት ጤናማ ተግባር አስተዋፅዖ ያለው ነው

    1 x ደንከሊያ ዩልቲሜት ኦሜጋ 3-6-9 ፕላስ

    ጥቅሞቹ

    • ዩልቲሜት ኦሜጋስ 3-6-9 ከአሳ፣ ከፍላክስሲድ እና ከቦራዥ ዘይት የተገኙ የኦሜጋ 3፣ 6፣ እና 9 ፋቲ አሲዶች ልዩ ቅይጥ ነው። እነዚህ ጠቃሚ ፋትስ ለተለያዩ አካላዊ ተግባራት አስፈላጊ ሲሆኑ ሰውነታችን እነዚህን ፋትስ በራሱ ማመንጨት ስለማይችል የምግባችን አካል መሆን አለባቸው።
    • ኦሜጋ 3 EPA(ኤኮሳፐንታኖይክ አሲድ) እና DHA (ዶኮሳሄክሳኖይክ አሲድ) ያሉት ነው። በአብዛኛው የሚገኘው ዘይታማ አሳዎች በሆኑት ሳርዲንማክረል እና ሳልሞን ውስጥ ነው። እንዲሁም ደግሞ አሳዎች በተፈጥሯቸው ጠቃሚ ወደሆነው EPA እና DHA መለወጥ የሚችሉትን ALA (አልፋ-ሊኖልኒክ አሲድ) ያካተተ ነው፣ ነገር ግን ሰውነታችን አነስተኛ መጠን ብቻ ነው መለወጥ የሚችለው።
    • ኦሜጋ 6 የሚሰራውም ከ ሊኖልኒክ አሲድ እና ጋማ-ሊኖልኒክ አሲድ ነው፤ የሚገኘውም በተለያዩ ዘይቶች እና ለውዝ ውስጥ ነው።
    • ኦሜጋ 9፤ በተፈጥሮ የኦሊክ አሲድ ያለባቸው ምግቦች እንደ ለውዝ እና ዘይት ውስጥ ሊገኝ ይችላል።
    • በእነዚህ ፋቲ አሲዶች መካከል ያለው የሬሾ መጠን በጣም ጠቃሚ ነው፣ በተለይ ደግሞ በኦሜጋ 3 እና በኦሜጋ 6 መካከል ያለው። ኦሜጋ 3-6-9፣ በቀን 3ቴ በሚወሰድ ዶዝ፣ ከአሳ እና ከፍላክስ ከፍተኛ የኦሜጋ 3 ዘይት ሬሾ የሚሰጥ ሲሆን፣ እና ደግሞ ከቦራዥ እና ፍላክስ ዘይት ከፍተኛ ጥራት ያለው የኦሜጋ 6ን የምናገኝ ይሆናል፣ ይኸውም ከኦሊክ አሲድ እንዲሁም ከፍላክስ ዘይት በሚገኝ ኦሜጋ 9ኝ የሚመጣጠን ይሆናል።
    • የአሳ ዘይት ለኦክሲዴሽን ተጋላጭ ነው፤ ይኸውም በምርቱ ላይ ዝቃጭ ቅንጣቶችን ያስከትላሉ። የእኛ የላቁ ዩልቲሜት ኦሜጋ ንጥረ-ነገሮች በናይትሮጂን በተሞላ አየር ክፍል ውስጥ ስለሚሞሉ ጥራቱ እና ደህንነቱ የተጠበቀ ነው።

    1 x የደንከሊያ የተሟላ የአጥንት ማጠንከሪያ ፈሳሽ

    ጥቅሞቹ፤

    የደንከሊያ የአጥንት ማጠንከሪያ ልዩ ቅይጦችን የያዘ ሲሆን እነዚህም አሚኖ አሲድ ቸላትስ ሲትራትስ  እና ማላትስ  ሲሆኑ እነዚህ ማዕድናት በሁሉም የዕድሜ ክልል ውስጥ ለሚገኙት፣ የምግብ መፈጨት ችግር ላለባቸውም በቀላሉ እንዲሰርጉ የሚረዱ ናቸው። ምንም እንኳ ካልሲየም በአጥንት ውስጥ በብዛት የሚገኝ ቢሆንም፣ ሰውነታችን ጥቅም ላይ ሊያውለው የሚችልበት መንገድ በሌሎች ቁልፍ ንጥረ-ነገሮች የሚወሰን ነው፤ ለምሳሌ ቪታሚን ዲ እና MSM (ኤም.ኤስ.ኤም) ሲሆኑ በልህቀት በተቀመረው ውህዳችን ላይ አብረው ተካትተዋል።

    o  የላቀ የካልሲየም ድብልቅ፣ ለአጥንት ጤና አስፈላጊ የሆኑ ንጥረ ነገሮች ጋር

    o  አጥንትን ለማጠንከር ወሳኝ የሆኑ ማዕድናትን እና ቪታሚኖችን የሚያቀርብ

    o  በተመጣጠነ መልኩ የአጥንት ማጠንከሪያ ንጥረ-ነገሮችን እያገኙ እንደሆኑ ማረጋገጥ ለሚፈልጉ ሰዎች ተመራጭ የሆነ

    ካልሲየም አጥንትን ለመጠገን አስፈላጊ ነው

    ካልሲየም ሴት ልጅ ደም-ከቆረጠች በኋላ ለሚደርስባት የአጥንት ማዕድን እፍግታ ማሽቆልቆልን ለመቀነስ ይረዳል። ዝቅተኛ የሆነ የአጥንት ማዕድን እፍግታ፣ ለ ኦስቲኦፖሮቲክ የአጥንት መሰንጠቅ መንስዔ ነው።

    ቪታሚን ዲ3ዚንክ እና ማግኒዚየም አጥንትን እና ጡንቻዎችን ለመጠገን አስተዋፅዖ አላቸው።

    ኮፐር፤ አገናኝ ህብረ-ህዋሳት ለመጠገን አስተዋፅዖ አለው

    ማንጋኒዝ ለአገናኝ ህብረ-ህዋሳት መፈጠር እና አጥንትን ለመጠገን አስተዋፅዖ አለው

    o MSM(ኤም. ኤስ. ኤም) - በሰውነት ውስጥ ለተለያዩ ዋና ዋና ተግባራት አስፈላጊ የሆነውን ሰልፈር ያቀርብልናል

    • 1 x ፍሎራ ኤድ

    ጥቅሞቹ፤

    ፍሎራ-ኤድ  የቅድመ እና የድህረ-ባዮቲክስ ቅይጥ ሲሆን ጤናማ የእርሽርሽሪት ስርዓት እና የተስተካከለ የንጥረ-ነገር ስርገት እና ሜታቦሊዝምን እንዲደግፍ የተቀመረ ምርት ነው። እንዲሁም ደግሞ ዩልቲሜት ፍሎራ ኤፍ.ኤክስ በተፈጥሮ የሚገኘውን ቅድመ-ባዮቲክ ግሉኮኖ ዴልታ ላክቶን (ጂ.ዲ.ኤል) የተባለ ኤጀንት የያዙ ሲሆን ይኸውም የትንሹ አንጀትን ጠቃሚ ባክቴሪያዎች የሚጠቅም እና እንደ አጠቃላይ የአንጀት ጤናን የሚያሻሽል ነው።

    • እያንዳንዶቹ የምትወስዷቸው እንክብሎች የሆድን አሲድ መቋቋም የሚችሉ እና በታችኛው የምግብ እንሽርሽሪት ክፍል ውስጥ መቀመጥ የሚችሉ ወደ 6 ቢሊዮን ጠቃሚ ማይክሮ-ኦርጋኒዝምስ ያላቸው ናቸው።
    • በልዩ ሁኔታ የተቀመሩ 3 ቅይጦች
    • ጠቃሚ የሆኑ (ህይወት ያላቸው የማይክሮ-ኦርጋኒዚም) ምንጭ
    • ጤናማ የባክቴሪያ ሁኔታን ለመፍጠር ይረዳል
    • ከ 6 ቢሊዮን በላይ ጠቃሚ ማይክሮ-ኦርጋኒዝሞችን ይሰጠናል

    1 x ዩልቲሜት ኢንዛየምስ

    ጥቅሞቹ፤

    ዩልቲሜት ኢንዛየምስ የእንሽርሽሪት ሂደትን እንዲደግፉ የተቀመሩ ናቸው። የእንሽርሽሪት ጤናን እንዲደግፉ ቢቴን HCl፣ ኦ.ኤክስ ቢሌ፣ እንዲሁም የእንሽርሽሪት ጤናን የሚደግፉ ጠቃሚ ኢንዛየሞችን ያካተቱ ናቸው። ዩልቲሜት ኢንዛየሞች ፤ ሰውነታችን ካርቦሀድሬትንፕሮቲንን እና ፋትን መሰባበር እና ንጥረ-ነገሮችን ማስረግ እንዲችል የሚረዱ ሲሆን ቆሻሻን በፍጥነት እንዲወጣ ይረዳሉ።

    • የእንሽርሽሪት ስርዓታችሁ ከምግቦቻችሁ ውስጥ ንጥረ-ነገሮች እንዲመጥ ይረዳል
    • ፕሮቲን፣ የካርቦሀይድሬት፣ እንዲሁም ፋት መሰባበር የሚያስችሉ የእንሽርሽሪት ኢንዛየሞች ልዩ ድብልቅ
    • ሀይድሮክሎሪክ አሲድን የሚጨምር ቢቴን ሀይድሮክሎራይድ የያዘ
    • ኦ.ኤክስ ቢሌ ይዘት ያለው ሲሆን ይኸውም የሀሞት ከረጢታቸው ለተወገደ ሰዎች ተመራጭ የሆነ
    • ከዕፅዋት የተዘጋጀ፣ ለአትክልት ተመጋቢዎች ሰፕልመንት የሚሆን

    ከሚከተሉት ነገሮች ነፃ የሆነ፡ ግሉተን፣ ስንዴ፣ የወተት ተዋፅዖ፣ አኩሪ አተር፣ እርሾ፣ ሰው ሰራሽ ማቆያዎች እና ማጣፈጫዎች ነፃ የሆነ።

    1 x ናይትሊ ኢሴንስ

    ዩልቲሜት ናይትሊ ኢሴንስ የተለያዩ የሰውነት ስርዓቶችን የሚደግፉ ጠቃሚ ኢንዛየሞችን የያዘ ሲሆን የልብ ጤና፣ በሽታ የመከላከል አቅማችንን እንዲሁም አጠቃላይ የሆድ እቃችንን ጤና የሚያሻሽሉ ናቸው። ዩልቲሜት ናይትሊ ኢሴንስ፤ የሆርሞን መጠንን፣ የኮሌስትሮል መጠንን፣ እንዲሁም የቆዳችንን ጤና የሚያሻሽሉ ናቸው።

    ከሚከተሉት ነገሮች ነፃ የሆነ፡ ግሉተን፣ ስንዴ፣ የወተት ተዋፅዖ፣ አኩሪ አተር፣ እርሾ፣ ሰው ሰራሽ ማቆያዎች እና ማጣፈጫዎች ነፃ የሆነ።

    የተሟላ የተለያዩ ቪታሚኖች ማዕድን  ታብሌት - በየቀኑ ከምግብ ጋር ወይም ከምግብ በኋላ 4 ታብሌት መውሰድ፣ ወይም የጤና አማካሪዎ በሚያዝዝዎ መሰረት መውሰድ::

    ዩልቲሜት ኦሜጋ 3-6-9 ፕላስ - በየቀኑ ከምግብ ጋር 3 እንክብሎችን እንድትወስዱ ይመከራል፣ ወይም የጤና አማካሪዎ በሚያዝዝዎ መሰረት መውሰድ።

    የተሟላ የአጥንት ማጠንከሪያ ፈሳሽ - በየቀኑ 31 ሚሊ(2 የሻይ ማንኪያ) መውሰድ፣ ወይም የጤና አማካሪዎ በሚያዝዝዎ መሰረት መውሰድ። ለጣዕም ከጭማቂ (ጁስ) ወይም ከውሀ ጋር ቀላቅላችሁ መውሰድ።  ከመጠቀማችሁ በፊት በደንብ መነቅነቅ ያስፈልጋል።

    ዩልቲሜት ኢንዛየምስ - በደንብ ከመመገባችሁ በፊት 1 እንክብል እንድትወስዱ ይመከራል፣ ወይም የጤና አማካሪዎ በሚያዝዝዎ መሰረት መውሰድ።

    ናይትሊ ኢሴንስ ፣ ከእያንዳንዱ ምግባችሁ በፊት 2 እንክብሎችን መውሰድ ወይም የጤና አማካሪዎ በሚያዝዝዎ መሰረት መውሰድ።

    ፍሎራ ኤድ - በየቀኑ ከምግብ ጋር 3 እንክብሎችን እንድትወስዱ ይመከራል፣ ወይም የጤና አማካሪዎ በሚያዝዝዎ መሰረት መውሰድ።

    የተሟላ የተለያዩ ቪታሚኖች ማዕድን ታብሌት -የፀሀይ ብርሃን በቀጥታ በማያገኘው መልኩ በቀዝቃዛ እና ደረቅ ቦታ ያስቀምጡት።

    ዩልቲሜት ኦሜጋ 3-6-9  - የፀሀይ ብርሃን በቀጥታ በማያገኘው መልኩ በቀዝቃዛ እና ደረቅ ቦታ ያስቀምጡት።

    የተሟላ የአጥንት ማጠንከሪያ ፈሳሽ - የፀሀይ ብርሃን በቀጥታ በማያገኘው መልኩ በቀዝቃዛ እና ደረቅ ቦታ ያስቀምጡት እና ከከፈታችሁት በኋላ በፍሪጅ ውስጥ ይቀመጥ። ምርቱ ከፍተኛ ጥራት ያለው በመሆኑ ለረዥም ጊዜ እንዲሁ ቀጥ አድርጋችሁ ካስቀመጣችሁት ሊጠጥር ይችላል። ይህን ለማስወገድ ከመጠቀማችሁ በፊት በሚገባ ነቅንቁት፣ እንዲሁም በፍሪጅ ውስጥ አጋድማችሁ ያስቀምጡት።

    ፍሎራ ኤድ እንክብሎች -የፀሀይ ብርሃን በቀጥታ በማያገኘው መልኩ በቀዝቃዛ እና ደረቅ ቦታ ያስቀምጡት።

    ዩልቲሜት ኢንዛየምስ - የፀሀይ ብርሃን በቀጥታ በማያገኘው መልኩ በቀዝቃዛ እና ደረቅ ቦታ ያስቀምጡት።

    ናይትሊ ኢሴንስ - በመደበኛ የሙቀት ልክ የፀሀይ ብርሃን በቀጥታ በማያገኘው መልኩ በቀዝቃዛ እና ደረቅ ቦታ ያስቀምጡት። ፍሪጅ ውስጥ ማስቀመጥ አያስፈልግም

    Have Questions?Ask An Expert
    The cookie settings on this website are set to 'allow all cookies' to give you the very best experience. Please click Accept Cookies to continue to use the site.
    የደንከሊያ ዩልቲሜት የእንሽርሽሪት ፓኬት (ታብሌት/ፈሳሽ)
    You have successfully subscribed!