የእንሽርሽሪት ስርዓትን የሚያጎለብት ፓኬት (ፓውደር/ፓውደር)

$306.95
  • A powerful combination of our Complete Multi-Vitamin Mineral Powder, Bone Support Powder, Ultimate Omegas 3-6-9 Plus, alongside Plant Enzymes and Flora Aid to help support the digestive system
  • Containing over 60 Plant Derived Minerals, 16 Vitamins, 12 Amino Acids, 3 Essential Fatty Acids at its base with extra enzymes and probiotics to promote healthy gut function
  • Highly absorbable forms of nutrients and necessary co-factors
  • Rich in antioxidants (vitamins A, C and E) protecting against free radical damage
Size Guide
$306.95
ገለፃ

የእንሽርሽሪት ስርዓትን የሚደግፉና እጅግ በጣም የተለያዩ ንጥረ-ነገሮች የተጨመሩበት እና የላቀ ዘመናዊ ህይወት መኖር ለሚፈልጉ ተመራጭ የሆነ። የዘመናችን ዘመናዊ የአስተራረስ ዘዴ ለም የሆነውን የአፈር ክፍል ከሚገባው በላይ ደጋግሞ የሚጠቀም በመሆኑ ምክንያት ለጤና አስፈላጊ የሆኑት፤ ጠቃሚ ቪታሚኖች፣ ማዕድናት፣ አሚኖ አሲድስ እንዲሁም ጠቃሚ ፋቲ አሲዶች ከምግቦቻችን ላይ በመጥፋት ላይ ይገኛሉ። የዚህ ፓኬት ይዘትም፤ የተሟላ የተለያዩ ቪታሚን ማዕድናት ፓውደር፣ ፕሪሚየም የኦሜጋ ዘይት ቅይጥ፣ የአጥንት ማጠንከሪያ ፖውደር የያዘ ነው። ከ90 በላይ ጠቃሚ ቪታሚኖች፣ ማዕድናት፣ አሚኖ አሲድስ፣ እና ጠቃሚ ፋቲ አሲዶች እንዲሁም በተጨማሪ የካልሲየም ይዘት አለው ለበለጠ የአጥንት ጥንካሬም ቪታሚን ዲ3 እና ማግኒዚየም  የያዘ ነው።  የደንከሊያ የእንሽርሽሪት ስርዓትን የሚደግፍ ፓኬት (ፓውደር/ፓውደር)  በአንቲኦክሲደንትስ የበለፀገ እና ሰውነታችን የዘመናዊ ህይወትን ጭንቀት እና ውጥረት መዋጋት መቋቋም እንዲችል የሚረዱ ከ 115 በላይ ፍራፍሬ እና አትክልቶች ጋር በልዩ ሁኔታ የተቀመሩ እና በተጨማሪነት እንሽርሽሪትን ከሚደግፉ ጋር አብረው የቀረቡ ናቸው።

የዚህ ፓኬት ይዘት፤

1 x የደነከሊያ የተሟሉ የተለያዩ ቪታሚን ማዕድናት ፓውደር

ጥቅሞቹ

ከፍተኛ መጠን ያለው የ ፓይቶኒውትረንት  ቅይጥ፣ ከዕፅዋትን የተቀመሙ ግብዓቶች እና ከፍተኛ አንቲኦክሲደንት ያለው ሲሆን 115 አይነት አትክልት እና ፍራፍሬን ያካተተ ነው።

ቪታሚን ቢ አይነቶችን በሙሉ የያዘ - ዕለታዊ የጉልበት መጠናችሁን ከፍ በማድረግ፣ የድካም ስሜትን እና ድካምን ይቀንሳል

ቪታሚን ቢ1፣ ቢ2፣ ቢ6 እና ቢ12 - የድካምን ስሜትን እና ድካምን በመቀነስ አስተዋፅዖ ያደርጋል

ቪታሚን ሲ - የበሽታ ተከላካይ ስርዓት ስራውን በአግባቡ እንዲሰራ ጠቃሚ የሆነ

ከፍተኛ ጥራት ያላቸው ግብዓቶች፤ የባክቴሪያ ቅይጥንም ያካተቱ ይኸውም ግብዓቶች በከፍተኛ ሁኔታ እንዲሰርጉ የሚያደርግ

ፍሪ ራዲካልስ ከሚደርስብን ጉዳት የሚከላከሉ ጠቃሚ የሆኑ አንቲ ኦክሲደንቶች  ቪታሚን ኤ፣ ሲ እና ኢ የያዙ። ፍሪ ራዲካልስ የማይሰክኑ ሞለኪውሎች  ሲሆኑ በሰውነታችን ውስጥ የሚገኙ ህዋሳትን የሚጎዱ እና የጤና ችግር የሚያስከትሉ እና ያለዕድሜ የሚያስረጁ ናቸው።

ፎሊክ አሲድ  ለቀይ የደም ህዋሳት ጤናማ ተግባር አስተዋፅዖ ያለው ነው

1 x ደንከሊያ ዩልቲሜት ኦሜጋ 3-6-9 ፕላስ

ጥቅሞቹ፤

  • ዩልቲሜት ኦሜጋስ 3-6-9 ከአሳ፣ ከፍላክስሲድ እና ከቦራዥ ዘይት የተገኙ የኦሜጋ 3፣ 6፣ እና 9 ፋቲ አሲዶች ልዩ ቅይጥ ነው። እነዚህ ጠቃሚ ፋትስ ለተለያዩ አካላዊ ተግባራት አስፈላጊ ሲሆኑ ሰውነታችን እነዚህን ፋትስ በራሱ ማመንጨት ስለማይችል የምግባችን አካል መሆን አለባቸው።
  • ኦሜጋ 3 EPA(ኤኮሳፐንታኖይክ አሲድ) እና DHA (ዶኮሳሄክሳኖይክ አሲድ) ያሉት ነው። በአብዛኛው የሚገኘው ዘይታማ አሳዎች በሆኑት ሳርዲንማክረል እና ሳልሞን ውስጥ ነው። እንዲሁም ደግሞ አሳዎች በተፈጥሯቸው ጠቃሚ ወደሆነው EPA እና DHA መለወጥ የሚችሉትን ALA (አልፋ-ሊኖልኒክ አሲድ) ያካተተ ነው፣ ነገር ግን ሰውነታችን አነስተኛ መጠን ብቻ ነው መለወጥ የሚችለው።
  • ኦሜጋ 6 የሚሰራውም ከ ሊኖልኒክ አሲድ እና ጋማ-ሊኖልኒክ አሲድ ነው፤ የሚገኘውም በተለያዩ ዘይቶች እና ለውዝ ውስጥ ነው።
  • ኦሜጋ 9፤ በተፈጥሮ የኦሊክ አሲድ ያለባቸው ምግቦች እንደ ለውዝ እና ዘይት ውስጥ ሊገኝ ይችላል።
  • በእነዚህ ፋቲ አሲዶች መካከል ያለው የሬሾ መጠን በጣም ጠቃሚ ነው፣ በተለይ ደግሞ በኦሜጋ 3 እና በኦሜጋ 6 መካከል ያለው። ኦሜጋ 3-6-9፣ በቀን 3ቴ በሚወሰድ ዶዝ፣ ከአሳ እና ከፍላክስ ከፍተኛ የኦሜጋ 3 ዘይት ሬሾ የሚሰጥ ሲሆን፣ እና ደግሞ ከቦራዥ እና ፍላክስ ዘይት ከፍተኛ ጥራት ያለው የኦሜጋ 6ን የምናገኝ ይሆናል፣ ይኸውም ከኦሊክ አሲድ እንዲሁም ከፍላክስ ዘይት በሚገኝ ኦሜጋ 9ኝ የሚመጣጠን ይሆናል።
  • የአሳ ዘይት ለኦክሲዴሽን ተጋላጭ ነው፤ ይኸውም በምርቱ ላይ ዝቃጭ ቅንጣቶችን ያስከትላሉ። የእኛ የላቁ ዩልቲሜት ኦሜጋ ንጥረ-ነገሮች በናይትሮጂን በተሞላ አየር ክፍል ውስጥ ስለሚሞሉ ጥራቱ እና ደህንነቱ የተጠበቀ ነው።

1 x የደንከሊያ የተሟላ የአጥንት ማጠንከሪያ ፓውደር

ጥቅሞቹ፤

የደንከሊያ የአጥንት ማጠንከሪያ ልዩ ቅይጦችን የያዘ ሲሆን እነዚህም አሚኖ አሲድ ቸላትስ ሲትራትስ  እና ማላትስ  ሲሆኑ እነዚህ ማዕድናት በሁሉም የዕድሜ ክልል ውስጥ ለሚገኙት፣ የምግብ መፈጨት ችግር ላለባቸውም በቀላሉ እንዲሰርጉ የሚረዱ ናቸው። ምንም እንኳ ካልሲየም በአጥንት ውስጥ በብዛት የሚገኝ ቢሆንም፣ ሰውነታችን ጥቅም ላይ ሊያውለው የሚችልበት መንገድ በሌሎች ቁልፍ ንጥረ-ነገሮች የሚወሰን ነው፤ ለምሳሌ ቪታሚን ዲ እና MSM (ኤም.ኤስ.ኤም) ሲሆኑ በልህቀት በተቀመረው ውህዳችን ላይ አብረው ተካትተዋል።

o  የላቀ የካልሲየም ድብልቅ፣ ለአጥንት ጤና አስፈላጊ የሆኑ ንጥረ ነገሮች ጋር

o  አጥንትን ለማጠንከር ወሳኝ የሆኑ ማዕድናትን እና ቪታሚኖችን የሚያቀርብ

o  በተመጣጠነ መልኩ የአጥንት ማጠንከሪያ ንጥረ-ነገሮችን እያገኙ እንደሆኑ ማረጋገጥ ለሚፈልጉ ሰዎች ተመራጭ የሆነ

ካልሲየም አጥንትን ለመጠገን አስፈላጊ ነው

ካልሲየም ሴት ልጅ ደም-ከቆረጠች በኋላ ለሚደርስባት የአጥንት ማዕድን እፍግታ ማሽቆልቆልን ለመቀነስ ይረዳል። ዝቅተኛ የሆነ የአጥንት ማዕድን እፍግታ፣ ለ ኦስቲኦፖሮቲክ የአጥንት መሰንጠቅ መንስዔ ነው።

ቪታሚን ዲ3ዚንክ እና ማግኒዚየም አጥንትን እና ጡንቻዎችን ለመጠገን አስተዋፅዖ አላቸው።

ኮፐር፤ አገናኝ ህብረ-ህዋሳት ለመጠገን አስተዋፅዖ አለው

ማንጋኒዝ ለአገናኝ ህብረ-ህዋሳት መፈጠር እና አጥንትን ለመጠገን አስተዋፅዖ አለው

o  MSM(ኤም. ኤስ. ኤም) - በሰውነት ውስጥ ለተለያዩ ዋና ዋና ተግባራት አስፈላጊ የሆነውን ሰልፈር ያቀርብልናል

1 x ፍሎራ ኤድ

ጥቅሞቹ፤

ፍሎራ-ኤድ  የቅድመ እና የድህረ-ባዮቲክስ ቅይጥ ሲሆን ጤናማ የእርሽርሽሪት ስርዓት እና የተስተካከለ የንጥረ-ነገር ስርገት እና ሜታቦሊዝምን እንዲደግፍ የተቀመረ ምርት ነው። እንዲሁም ደግሞ ዩልቲሜት ፍሎራ ኤፍ.ኤክስ በተፈጥሮ የሚገኘውን ቅድመ-ባዮቲክ ግሉኮኖ ዴልታ ላክቶን (ጂ.ዲ.ኤል) የተባለ ኤጀንት የያዙ ሲሆን ይኸውም የትንሹ አንጀትን ጠቃሚ ባክቴሪያዎች የሚጠቅም እና እንደ አጠቃላይ የአንጀት ጤናን የሚያሻሽል ነው።

  • እያንዳንዶቹ የምትወስዷቸው እንክብሎች የሆድን አሲድ መቋቋም የሚችሉ እና በታችኛው የምግብ እንሽርሽሪት ክፍል ውስጥ መቀመጥ የሚችሉ ወደ 6 ቢሊዮን ጠቃሚ ማይክሮ-ኦርጋኒዝምስ ያላቸው ናቸው።
  • በልዩ ሁኔታ የተቀመሩ 3 ቅይጦች
  • ጠቃሚ የሆኑ (ህይወት ያላቸው የማይክሮ-ኦርጋኒዚም) ምንጭ
  • ጤናማ የባክቴሪያ ሁኔታን ለመፍጠር ይረዳል
  • ከ 6 ቢሊዮን በላይ ጠቃሚ ማይክሮ-ኦርጋኒዝሞችን ይሰጠናል

1 x የዕፅዋት ኢንዛየምስ

ጥቅሞቹ

የዕፅዋት ኢንዛየሞች የእንሽርሽሪት ስርዓታችንን እና የምግብ ስርገትን ለመደገፍ የሚረዱ ሲሆን ምንጫቸው ከእንስሳት ያልሆነ፣ የእኛ ልዩ ግኝት ኢንዛየሞች ናቸው። እነዚህን የዕፅዋት ኢንዛየሞች በቀን ከ 1-3 እንክብሎች በመውሰድ፣ ሰውነታችሁ የበላችሁትን ምግብ በቀላሉ እንዲፈጭ እና ንጥረ-ነገሮችን መምጠጥ እንዲችል መርዳት ትችላላችሁ።

  • የእንሽርሽሪት ስርዓታችሁ ከምግቦቻችሁ ውስጥ ንጥረ-ነገሮች እንዲመጥ ይረዳል
  • የፕሮቲን፣ የካርቦሀይድሬት፣ እንዲሁም ፋት መሰባበር የሚያስችሉ የእንሽርሽሪት ኢንዛየሞች ልዩ ድብልቅ
  • ሀይድሮክሎሪክ አሲድን የሚጨምር ቢቴን ሀይድሮክሎራይድ የያዘ
  • ከዕፅዋት የተዘጋጀ፣ ለአትክልት ተመጋቢዎች ሰፕልመንት የሚሆን

ከሚከተሉት ነገሮች ነፃ የሆነ፡ ግሉተን፣ ስንዴ፣ የወተት ተዋፅዖ፣ አኩሪ አተር፣ እርሾ፣ ሰው ሰራሽ ማቆያዎች እና ማጣፈጫዎች ነፃ የሆነ።

የተሟላ የተለያዩ ቪታሚኖች ማዕድን ፓውደር - 1 ጎድጓዳ ማንኪያ ከ 250 ሚሊ ውሀ ወይም ጭማቂ(ጁስ) ጋር ቀላቅላችሁ ከምግብ ጋር ወይም ከምግብ በኋላ እንድትወስዱ ይመከራል፣ ወይም የጤና አማካሪዎ በሚያዝዎ መሰረት መውሰድ።

ዩልቲሜት ኦሜጋ 3-6-9 ፕላስ - በየቀኑ ከምግብ ጋር 3 እንክብሎችን እንድትወስዱ ይመከራል፣ ወይም የጤና አማካሪዎ በሚያዝዝዎ መሰረት መውሰድ።

የተሟላ የአጥንት ማጠንከሪያ ፓውደር - 1 ጎድጓዳ ማንኪያ ከ 250 ሚሊ ውሀ ወይም ጭማቂ(ጁስ) ጋር ቀላቅላችሁ ከምግብ ጋር ወይም ከምግብ በኋላ መውሰድ፣ ወይም የጤና አማካሪዎ በሚያዝዎ መሰረት መውሰድ።

የዕፅዋት ኢንዛየምስ - በሚገባ ከመመገባችሁ በፊት ከ2-3 እንክብሎችን እንድትወስዱ ይመከራል፣ ወይም የጤና አማካሪዎ በሚያዝዝዎ መሰረት መውሰድ።

ፍሎራ ኤድ - በየቀኑ ከምግብ ጋር 3 እንክብሎችን እንድትወስዱ ይመከራል፣ ወይም የጤና አማካሪዎ በሚያዝዝዎ መሰረት መውሰድ።

ሁሉም እቃ ፀሀይ በቀጥታ በማያገኘው መልኩ በቀዝቃዛ እና ደረቅ ቦታ ይቀመጥ።

ይህን ምርት በፍሪጅ ውስጥ ማስቀመጥ አያስፈልግም።

Have Questions?Ask An Expert
The cookie settings on this website are set to 'allow all cookies' to give you the very best experience. Please click Accept Cookies to continue to use the site.
የእንሽርሽሪት ስርዓትን የሚያጎለብት ፓኬት (ፓውደር/ፓውደር)
You have successfully subscribed!