ከዕፅዋት የተገኙ ማዕድናት - 30 እንክብሎች

$48.95
  • ከፍተኛ ጥራት ያላቸው ከዕፅዋት የተገኙ የአዮኒክ ማዕድናት ልዩ ድብልቅ
  • ጥራት ያለው የውሀ ማጣራት ሂደት
  • ከ70 በላይ በቀላሉ መስረግ የሚችሉ ኮሎይዳል ማዕድናት
  • ለተለያዩ አይነት ጠቃሚ ባዮሎጂካል ሪያክሽኖች እንደ ካታሊስትነት የሚያገልግሉ
  • ለአትክልት ብቻ ተመጋቢዎችም የሚሆን
እያንዳንዱ የሰውነታችን ክፍል በትክክለኛው ደረጃ ስራውን ለመከወን፣ ከምግብ የሚገኙ ማዕድናት ያስፈልጉታል። የተመጣጠነ ምግብ የሚያስፈልጉንን ማዕድናት በሙሉ የሚሰጠን ሊመስለን ይችላል፤ ነገር ግን፣ በዘመን አመጣሽ ብክለት ምክንያት፣ ገንቢ የሆኑት ክፍሎች ከምግቦቻችን ላይ ጎድለዋል። የእኛ ከዕፅዋት የተገኙ አዮኒክ ማዕድናት ከፍተኛ ጥራት ያላቸው ሲሆኑ ከጥንታዊ የዕፅዋት ክምችቶች ውስጥ የተገኙ ናቸው፣ የተፈጠሩትም ፕላኔታችን በብክለት ከመታወኳ ከሚሊዮን ዓመታት በፊት ነው፤ ስለሆነም ጥራት ያላቸው ንጥረ ነገሮችን እና ማዕድናትን ከእነ ሙሉ ይዘታቸው መስጠት ያስችላሉ።
Size Guide
መጠን *
$48.95
Add to Wish List

ገለፃ

የእኛዎቹ ከዕፅዋት የተገኙ ማዕድናት የሚገኙት ከ ዩታህ፣ አሜሪካ ከሚገኝ የ ሼል ክምችት ውስጥ ነው። እነዚህ ክምችቶች የተፈጠሩት ከሚሊዮን አመታት በፊት ሲሆን በቅድመ-ታሪክ ዘመን በደን የተሸፈኑ ነበሩ። ይህ ቅርፍተ መሬት ከዕፅዋት የተገኙ ማዕድናትን የያዘ ሲሆን ከበካይ ነገሮች ለሚሊዮን አመታት ተጠብቀው እና ተደብቀው የኖሩበት የመሬት ክፍል ነው። ይኸውም በቅድመ-ታሪክ ዘመን ከዕፅዋት እና ፍራፍሬዎች የሰረጉ ከ 77 በላይ ማዕድናት የሚገኙበት ነው። ሰውነታችን ስራውን በአግባቡ ለመከወን የማያቋርጥ የማዕድን አቅርቦት ይፈልጋል። የእኛ ከዕፅዋት የተገኙ ማዕድናት በፈሳሽ መልክ የቀረቡ ሲሆን ከቅድመ-ታሪክ እፅዋት የተገኙ ከ70 በላይ በቀላሉ የሚሟሙ፣ ከውሀ ጋር የሚዋሃዱ ኮሎይዳል ማዕድናትን የያዙ ናቸው።

ከሚከተሉት ነገሮች ነፃ የሆነ፤ግሉተን፣ ከስንዴ፣ ከአኩሪ አተር፣ ከእርሾ፣ ከሰው ሰራሽ ማቆያ እና ማጣፈጫዎች ነፃ የሆነ።

በየቀኑ 31 ሚሊ (2 የሻይ ማንኪያ) መውሰድ፣ ወይም የጤና አማካሪዎ በሚያዝዝዎ መሰረት መውሰድ። ለጣዕም፤ ከጭማቂ(ጁስ) ወይም ውሀ ጋር መቀላቀል ትችላላችሁ።

በቀጥታ የፀሀይ ብርሃን በማያገኘው መልኩ በቀዝቃዛ እና በደረቅ ቦታ ያስቀምጡት። አንዴ ከተከፈተ በኋላ ማቀዝቀዣ(ፍሪጅ) ውስጥ ያስቀምጡት።


Have Questions?Ask An Expert
The cookie settings on this website are set to 'allow all cookies' to give you the very best experience. Please click Accept Cookies to continue to use the site.
ከዕፅዋት የተገኙ ማዕድናት - 30 እንክብሎች
You have successfully subscribed!