ገለፃ
ቪዥንኤድ ፕላስ የ ፍሪ ራዲካልን ጉዳት ለመቀነስ በሚረዳ መልኩ ከቪታሚን እና ማዕድናት ጋር አብሮ የተቀመረ ኃይለኛ አንቲኦክሲደንት ነው።
ፍሪ ራዲካልስ በሰውነታችን ውስጥ ያለማቋረጥ የሚመረቱ የማይሰክኑ አቶሞች ሲሆኑ፣ በተለይ ደግሞ በጭንቀት ወቅት ወይም ለአየር ብክለት፣ ለጨረራ ወይም ለዩልትራቫዮሌት ብርሀን ስንጋለጥ በብዛት የሚመረቱ ናቸው። ፍሪ ራዲካልስ ለበሽታዎች ሁሉ ምክንያት እንደሆኑ ይታመናል እንዲሁም ያለዕድሜ እንድናረጅ ከፍተኛ አስተዋፅዖ አላቸው። የህዋስ መዳከም መንስዔ በመሆን፣ እንደ ካንሰር እና በሌሎችም በሽታዎች እንድንጠቃ ያደርጉናል።
አንቲ-ኦክሲደንቶች የ ነፃ-ራዲካሎችን ተፅዕኖ ለመቋቋም የሚያስችሉ ናቸው። በጣም ጠቃሚ ከሆኑት ውስጥ ጥቂቶቹ፤ ቤታ-ካሮቲን፣ ቪታሚን ሲ፣ ቪታሚን ኢ፣ ዚንክ እና ሰሊኒየም ይጠቀሳሉ።፡
የቪዥንኤድ ፕላስ ልዩ ቀመር ጠንካራ የአንቲኦክሲደንት ባህሪያት ያሉት ሲሆን እነዚህም፤ ቢሊቤሪ፣ ኩዊርሰቲን፣ የአረንጓዴ ቅጠል ጭማቂ፣ ቪታሚን ሲ/ኤ እና ኢ፣ ከማዕድናቱ ጋር አንድላይ፣ ዚንክ እና ሰሊኒየምን ያካተተ ነው።
ቪታሚን ሲ ያለው አስተዋፅዖ፤
- ለጤናማ የ ኮላጅን አፈጣጠር፤ የደም-ትቦዎች፣ አጥንቶች፣ ልምአፅሞች፣ ድድ፣ ቆዳ እና ጥርስ በጤናማ ሁኔታ ስራቸውን እንዲተገብሩ፤
- ጉልበት ለሚያመነጭ ጤናማ ሜታቦሊዝም
- ለጤናማ የስርዓተ-ነርቭ ተግባር
- ለጤናማ የስነ-አዕምሯዊ ተግባር
- ለጤናማ የበሽታ-ተከላካይ ስርዓት፣ እንዲሁም ደግሞ በከባድ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ወቅት እና በኋላ ለጤናማ የእንቅስቃሴ ተግባር።
- ህዋሶችን ከ ኦክሲዴቲቭ ውጥረት ለመከላከል
- የድካም ስሜትን እና ድካምን ለመቀነስ
- ቪታሚን ኢ ሲቀንስ በተወሰነ መልኩ ለማስቀጠል
- የ አይረን የስርገት መጠንን ለመጨመር
ቪታሚን ኢ
- በፋት የሚሟሟ ቪታሚን ሲሆን ግንባር ቀደም አንቲኦክሲደንት የሆነ ጠቃሚ ንጥረ-ነገር ነው.
- እንዲሁም ደግሞ ተፈጥሯዊው ቪታሚን ኢ (ዲ-አልፋ ቶኮፌሮል) ከሰው-ሰራሹ አንፃር ሲታይ በ1.3 የበለጠ ባዮአቬሌብል መሆኑን ጥናቶች አሳይተዋል።
የዚንክ ያለው አስተዋፅዖ
- ፀጉርን፣ ቆዳን እና ጥፍርን ለመጠገን
- ለካርቦሀይድሬት ሜታቦሊዝም
- ለግንዛቤ ተግባር
- የመካንነት ችግርን ለመቅረፍ
- ለቪታሚን ኤ ሜታቦሊዝም
- ለደም ውስጥ የቴስቴስትሮን መጠን
- ለአይን ጥራት
- በሽታን ለመከላከል
- ጤናማ አጥንቶችን ለመጠገን
- ህዋሶችን ከኦክሲዴቲቭ ውጥረት ለመጠበቅ
ሰለኒየም ያለው አስተዋፅዖ፤
- ለጤናማ “ስፐርማቶጀነሲስ”
- የፀጉርን ጤና ለመጠበቅ
- የጥፍርን ጤና ለመጠበቅ
- የበሽታ ተከላካይ ስርዓት በአግባቡ ስራውን እንዲከውን
- ለጤናማ የታይሮይድ ተግባር
- ህዋሶችን ከኦክሲዴቲቭ ውጥረት ለመጠበቅ
ቪታሚን ኤ ያለው አስተዋፅዖ፤ ለጤናማ የ አይረን ሜታቦሊዝም
- የአፍንጫ ቀዳዳ የህብረ ህዋስ ሽፋንን ለመጠገን
- ቆዳን ለመጠገን
- የአይን ዕይታን ለማሻሻል
- ለጤናማ የበሽታ ተከላካይ ስርዓት
- የህዋሳትን ተግባር ለማካሄድ
ይህ ቀመር ከያዘው ውስጥ
- ታውሪን - በሰውነት ውስጥ ሊፈጠር የማይጭል ጠቃሚ አሚኖ አሲድ
- ካሮቲኖይድስ - በዕፅዋት፣ በአትክልት እና ፍራፍሬዎች ውስጥ ደማቅ ቢጫ፣ ቀይ እና አረንጓዴ ቀለማትን የሚፈጥር ውህድ
- ኡፍሬሺያ ስትሪክታ (ብሩህ አይን) - በባህላዊ መልኩ ለአይን ህክምና ጥቅም ላይ ሲውል የነበረ በአውሮፓ የሚበቅል ዕፅ
- ቢልቤሪ ቤሪ- በሰሜናዊ አውሮፓ፣ በሰሜን አሜሪካ እና በሰሜናዊ ኤዥያ ውስጥ የሚገኝ ባለ አበባ ቆጥቋጦ። ፖሊፌኖሊስ የሆኑት፣ የ አንቶሳይኒነስ ዋና ምንጭ ነው።
- ኩዊርሴቲን የዕፅዋት የቀለም ምንጭ (ፍላቮኖይድ) ነው። በተለያዩ ዕፅዋት እና ምግቦች ውስጥ የሚገኝ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥም ቀይ ወይን፣ ሽንኩርት፣ አረንጓዴ ሻይ፣ ፖም፣ ቤሪ፣ ጂንኮ ቢሎባ፣ John's wort, American elder, እንዲሁም በሌሎችም ይገኛል። የ በክዊት ሻይ ከፍተኛ የኩዊርሴቲን መጠን አለው። ሰዎች ኩዊርሴቲን እንደ መድሃኒትነት ይጠቀሙበታል። ኩዌርሴቲን የአንቲኦክሲዳንት እና አንቲ-ኢንፍላማቶሪ ውጤት ስላለው የሰውነት መቆጣትን ለመቀነስ፣ የካንሰር ህዋሳትን ለመግደል፣ የደም ውስጥ የስኳር መጠንን ለመቆጣጠር፣ እንዲሁም የልብ በሽታን ለመከላከል ይረዳል።
- የአረንጓዴ ሻይ ጭማቂ - ኢፒጋሎካተቺን 3 ጋላቴ (EGCG) የሚባል ካተቺን የያዘ ነው። ካተቺኖች የህዋሳትን ጉዳት የሚከላከሉ እና ሌሎች ጥቅሞች ያላቸው የተፈጥሮ አንቲኦክሲደንት ናቸው።
ከሚከተሉት ነገሮች ነፃ የሆነ፤ ከግሉተን፣ ከስንዴ፣ከወተት ተዋፅዖ፣ ከአኩሪ-አተር፣ ከእርሾ፣ ከሰው ሰራሽ ማቆያ እና ማጣፈጫዎች ነፃ የሆነ።