ቪታሚን ዲ3 10,000 IU (250µg) 150 እንክብሎች

$53.95
የአጥንትን እና የጥርስን ጤና ይጠብቃሉ

የጡንቻ ተግባርን ያግዛሉ

በሽታ የመከላከል አቅምን ያጎለብታሉ

የካልሲየም የስርገት መጠንን ያፋጥናሉ

    የላቁ የቪታሚን ዲ3 ንጥረነገሮችን በውስጣቸው ቪታሚን ኬ1 እና ኬ2 እንዲይዙ ተደርገው ዲዛይን የተደረጉ ሲሆን የቪታሚን ዲ ዋና ተግባር በደማችን ውስጥ በቂ የካልሲየም መጠን መኖሩን ማረጋገጥ ነው። ቪታሚን ኬ በአጥንታችን ውስጥ የተከማቸውን የካልሲየም መጠን የሚያመጣጥን እንዲሁም እንደ ደም ቧንቧ ባሉት ስስ ህብረህዋሳት ውስጥ የተከማቸውን የሚቀንስ ነው።
Size Guide
$53.95
Add to Wish List

ገለፃ

የደንከሊያ ቪታሚን ዲ3 10,000 IU (250µg) እንክብሎች ቪታሚን ዲ ን ከ ቪታሚን ኬ1 እና ኬ2 ጋር የያዙ እና ይበልጥ ለሰውንት ተስማሚ በሆነው ዲ3 መልኩ በላቀ ሁኔታ የተቀመሩ እንክብሎች ናቸው። የተስተካከል ጤናን የሚደግፉ ሲሆን፣ “ከፀሀይ ስለሚገኝ ቪታሚን” ጥቅብ በብዛት እና በተጠናገረ መልኩ ተገልጿል፣ በተለይ ደግሞ በሽታን ለመከላከል ያለው አስተዋፅዖ ጠቃሚ ነው።

በዓለማችን ላይ ከ ቢሊዮን ሰዎች በላይ አነስተኛ የቪታሚን ዲ ያላቸው ሲሆን ቪታሚን ዲ  በ ፋት የሚሟሟ እና የካልሲየም የስርገት መጠንን የሚጨምር ሲሆን ይኸውም ጤናማ አጥንት እና ጥርስ እንዲኖረን የሚረዳን ነው። የደንከሊያ የቪታሚን ዲ3 በከፍተኛ ሁኔታ መስረግ የሚችል ቪታሚን ዲ ከመሆኑ ባሻገር የአመጋገብ ዘያችሁን ከመቀየር ባሻገር፣ በቀዝቃዛዎቹ የዊንተር ወራት የቪታሚን ዲ ሰፕልመንትን መውሰድ የተሻለ ነገር ነው።

እና የካልሲየም የስርገት መጠንን የሚጨምር ሲሆን ይኸውም ጤናማ አጥንት እና ጥርስ እንዲኖረን የሚረዳን ነው። የደንከሊያ የቪታሚን ዲ3 በከፍተኛ ሁኔታ መስረግ የሚችል ቪታሚን ዲ ከመሆኑ ባሻገር የአመጋገብ ዘያችሁን ከመቀየር ባሻገር፣ በቀዝቃዛዎቹ የዊንተር ወራት የቪታሚን ዲ ሰፕልመንትን መውሰድ የተሻለ ነገር ነው።

ቪታሚን ዲ ያለው አስተዋፅዖ፤

  • ለጤናማ የበሽታ ተከላካይ ስርዓት
  • አጥንትን እና ጥርስን በጤናማ ሁኔታ ለመጠገን
  • ለጤናማ የካልሲየም እና የፎስፈረስ ስርገት
  • በደም ውስጥ የካልሲየም መጠን ጤናማ እንዲሆን አስተዋፅዖ በማድረግ

  • በደም ውስጥ የካልሲየም መጠን ጤናማ እንዲሆን አስተዋፅዖ በማድረግ

ቪታሚን ኬ ያለው አስተዋፅዖ፤

  • ለጤናማ የደም መርጋት
  • ጤናማ አጥንትን ለመጠገን 

ቪታሚን ዲ እና ኬ በቡድን ነው የሚሰሩት

ወደ ካልሲየም ሜታቦሊዝም ከመጣን፣ ቪታሚን ዲ እና ኬ በጋራ ነው የሚሰሩት። ሁለቱም ጠቃሚ ሚና አላቸው።


የቪታሚን ዲ ሚና

የቪታሚን ዲ ዋና ተግባር ከሆኑት አንዱ በደም ውስጥ በቂ የሆነ የካልሲየም መጠን እንዲኖር ማመጣጠን ነው።

ቪታሚን ዲ ይህን የሚያደርግበት ሁለት መንገዶች አሉ።

  • የካልሲየም የስርገት መጠንን መጨመር፤ ቪታሚን ዲ ከምንመገባቸው ምግቦች ውስጥ የምናገኘውን ካልሲየም በይበልጥ እንዲሰርግ ያደርጋል።
  • ከአጥንት ካልሲየምን መውሰድ፤ በቂ የሆነ የካልሲየም መጠን የማትመገቡ ከሆነ፣ የሰውነታችን ዋና የካልሲየም ምንጭ ከሆነው ከአጥንታችን በመውሰድ የደምን መጠን ያመጣጥናል።

በደም ውስጥ በቂ የካልሲየም ይዘት መኖሩ አስፈላጊ ነው። ምንም እንኳ ካልሲየም ይበልጥ የሚታወቀው ከአጥንት ጤና ጋር በተያያዘ ቢሆንም፣ ለተለያዩ የሰውነታችን ተግባራት በጣም አስፈላጊ ነው።

በቂ ያልሆነ የካልሲየም መጠን ካልወሰዳችሁ፣ ለሰውነታችሁ ሌላ አማራጭ ስላልሰጣችሁት ከአጥንታችሁ ለመውሰድ ይገደዳል፤ ይኸውም በጊዜ በሂደት ለአጥንት መሳሳት ብሎም ለ ኦስቲኦፖሮሲስ ይዳርጋችኋል።

የቪታሚን ኬ ሚና

ከላይ እንደተገለፀው፣ ቪታሚን ዲ በደም ውስጥ ያለው የካልሲየም መጠን የሰውነታችሁን ፍላጎት ለማሟላት በቂ መሆኑን ያረጋግጣል።

ይሁን እንጂ፣ ቪታሚን ዲ በሰውነታችሁ ውስጥ ያለውን የካልሲየም መዳረሻ አይቆጣጠርም። እዚህ ጋር ነው የ ቪታሚን ኬ ተግባር የሚያስፈልገው።

ቪታሚን ኬ ቢያንስ በሁለት መንገድ በሰውነታችሁ ውስጥ የሚገኘውን የካልሲየም መጠን ያመጣጥናል።

  • የአጥንትን ካልሲፊኬሽን ይጨምራል፤ ቪታሚን ኬ በአጥንት እና በጥርስ ውስጥ የካልሲየም ክምችትን የሚጨምር ኦስቲኦካልሲን የተባለ ፕሮቲን ያነቃቃል።
  • የስስ ህብረህዋሳትን ካልሲፊኬሽን ይቀንሳል፤ ቪታሚን ኬ እንደ ኩላሊት እና የደም ቧንቧ በመሳሰሉት ስስ  ህብረህዋሳት ውስጥ እንዳይከማች የሚከላከል ማትሪክስ ጂ.ኤል.ኤ ፕሮቲንን ያነቃቃል።


ከሚከተሉት ነገሮች ነፃ የሆነ፤ ግሉተን፣ ስንዴ፣ የወተት ተዋፅዖ፣ አኩሪ-አተር፣ እርሾ፣ ከሰው ሰራሽ ማቆያ እና ማጣፈጫዎች ነፃ የሆነ።

በየቀኑ ከምግብ በፊት 2 እንክብሎችን መውሰድ፣ ወይም የጤና አማካሪዎ በሚያዝዝዎት መሰረት መውሰድ።

በቀጥታ ፀሀይ በማያገኘው መልኩ በቀዝቃዛ እና በደረቅ ቦታ ያስቀምጡት። ማቀዝቀዣ (ፍሪጅ) ውስጥ ማስቀመጥ አያስፈልግም።

Have Questions?Ask An Expert
The cookie settings on this website are set to 'allow all cookies' to give you the very best experience. Please click Accept Cookies to continue to use the site.
ቪታሚን ዲ3 10,000 IU (250µg) 150 እንክብሎች
You have successfully subscribed!