ቤተሰባችንን አትክልትና ፍራፍሬ እንዲመገቡ የምናደርግባቸው 10 መንገዶች - ሰናአይት
የምንወዳቸው ሰዎች በቀን ቢያንስ አምስት ፍራፍሬዎችን እና አትክልቶችን በትንሹ እንዲመገቡ ለማድረግ መሞከር ብዙውን ጊዜ አስቸጋሪ ነው ፡፡ ነገርግን በማያውቁት መልኩ እነዚህን ጤና ሰጪ ምግቦች ወደ ምግባቸው ውስጥ ቀላቅለን እንዴት መስጠት እንደምንችል ማውቅ ብልሃት ነው።
1. ቁርስ ላይ ጁስ(ስሙዚ)
ልጆቹን(ሚልክ ሼክ) ነው በማለት ፡የበረዶ እንክብሎች (አይስ ኪዩቦችን )፣ እርጎ እና ትኩስ ፍራፍሬዎችን ቅላቅሎ በመፍጨት በተጨማሪም ብርታት የሚሰጡ የፕሮቲን ዱቄቶችን ወይም ተልባን በማከል መስጠት ይቻላል፡ ልጆቹ አይስ ክሬምን የሚወዱ ከሆነ ደግሞ በፍራፍሬዎች ምትክ በረዶ የሰራ ፍራፍሬ በመጠቀም ተመሳሳይ የሆነ ለስላሳና ጠቃሚ ንጥረ ነገር ይለው ምግብ ያገኛሉ።
2. በተፈጥሮው የደረቀ ፍሬ
በተፈትሮ የደረቀ ፍሬ ጥቅም አለው ሰላጣ ውስጥም ሊጨመር ይችላል። በመጋገሪያ ውስጥ ወይም በእርጥበት ማስወገጃ (ዲሀይድሬተር) ውስጥ በጣም በዝቅተኛ የሙቀት መጠን ማድረቅ ይችላል ፡፡ የደረቁ ፍራፍሬዎችን በልጆችዎ ወይም በቤተሰብ አባል ምሳ ዕቃ ውስጥ ወይም እንደመክሰስ ሊጠቀሙ ይችላሉ።
3. ፍራፍሬዎችን እና አትክልቶችን ወደ ሳንድዊቾች ይጨምሩ
ሳንድዊችዎችን ለማዘጋጀት ከግሉተን ነፃ ዳቦን ይጠቀሙ ወይም ከአፍሪካ ቀንድ የሚመጣ የጤፍ ቂጣ ቁርስራሽ ሙከራ ያድርጉ ፡ ሳንድዊቹን በቀጭን የተከተፈ አፕል ፣ ሙዝ ወይም እንጆሪ አድርገው በለውዝ ቅቤ (ይቅርታ ፣ የኦቾሎኒ ቅቤ አይፈቀድም) አድርገው ይሞክሩት ፡፡
በዶሮ ስጋ(ተርኪ) ወይም በአይብ ሳንድዊቾች ውስጥ የተከተፈ ቲማቲም ፣ ዱባ(ኪውከምበር) ፣ የማይቃጥል ቃርያ፣ ሰላጣ ፣ የተከተፈ ካሮት ወይም ሌላ ማንኛውንም አትክልት ይጨምሩ ፡ዘይት-አልባ በሆነ ማዮኔዝ ቀላቀለውን ቤተሰቦን ለመመገብ ይሞክሩ ፡፡
4. በእራት ሰዓት የሰላጣ
የእራት ጊዜን አስደሳችና ፈጠራ የተሞላበት የሰላጣ አሰራር ለቤተሰቦ ያስተዋውቁ መላው ቤተሰብ እንዲሳተፉ ያድርጉ ለምሳሌ ለጆችን ፍራፍሬውን በፈለጉት ቅርጾች እና መጠኖች እንዲቆርጡ ያድርጉ፡፡ አትክልቶችን ፣ ከአይብ (ቺዝ)፣ ከተርኪ(ከዶሮ) ወይም ከበሬ ሥጋ ጋር ቀላቅለው ያቅርቡት። ቤተሰቦ በጭራሽ ሌላ ቦታ ሂደው መመገብ አይፈልጉም ፡፡እንደሚታወቀው የአንድ ሬስቶራንት ቁልፍ አቀራረቡ ነው።
5. ፍራፍሬዎችን እና አትክልቶችን መጠጣት
በጠርሙስ ጆግ ውስጥ የተለያዩ የተፈጩ ጭማቂዎችን በማቀዝቀዣ ውስጥ ያስቀምጡና ቤተሰብዎ ጥሩ ስሜት በማይሰማቸው ግዜ እንዲጠጡ ያበረታቷቸው ፡፡ ያስታውሱ በቀዝቃዛነት የተጨመቁ ጭማቂዎች ከተሰሩ ብዙም ሳይቆይ ኦክሳይድ መሆን ይጀምራሉ ፣ ስለሆነም በየቀኑ ትኩስ መሆኑን ያአረጋግጡ ፡
«ኮክቴል ሰዓት»በጁስ ብርጭቆዎ ላይ የኮክቴል ጃንጥላዎችን እና ለአይን የሚማርኩ ትኩስ ፍራፍሬዎችን በመጨመር በዙሪያው ተቀምጣችው ለመወይየት የሚያስደስት መጠጥ የሆናል። ይህም ከእራት በፊት ሊሆን ይችላል።
6. ጣፋጭ
ቤተሰቦ ይህንን ጣፋጭ ይወዱታል፡፡
• ትንሽ የቀዘቀዘ እርጎ ወይም የቀዘቀዘ የፍራፍሬ ድብልቅ (እንደ ሙዝ እና ማንጎ ያሉ)
• የተፈጨ አቮካዶ ወይም በድብል ክሬም የተሞላ
• በብዙ ትኩስ ወይም በቀዘቀዙ የእንጆሪ ፍሬዎች የተሸፈነ
7. የፍራፍሬ እና የአትክልት መክሰስ
• የተከተፈ አፕል በለውዝ ቅቤ (የኦቾሎኒ ቅቤ አይደለም) ወይም አይብ(ቺዝ) ተጨምሮ
• የተከተፈ አይብ(ቺዝ) ከወይን ፍሬዎች ወይም አናናስ ጋር
• ተቆርጠው ጥሬውን የሚበሉ አትክልቶች በቤት ውስጥ በተቀመመ አዋዜ ተናክተው የሚበሉ
• በአቮካዶ ወይም በአይብ ተሞልተው ዘቢብ የተነሰነሰባቸው የሴላሪ እንጨቶች
8. አዲስ ነገር ይሞክሩ
አዲስ እና ያልተለመዱ ፍራፍሬዎችን እና አትክልቶችን ቤተሰብዎን ለማስተዋወቅ ይሞክሩ ፡፡ እርስዎ ከማወቅዎ በፊት ወሬው እየተዛመተ መላው ሰፈር እነሱን ይሞክራቸዋል ፡፡ የዛሬዎቹ ሱፐር ማርኬቶች ከዓለም ዙሪያ አስገራሚ ልዩ ልዩ ፍራፍሬዎችን እና አትክልቶችን ያከማቹ ስለሆኑም ይሞክሯቸው ፡፡
9. የአጥንት ሾርባ ወይም በዋናነት የአትክልት ሾርባ
በዋናነት አትክልቶች የሆኑትን ሾርባ ወይንም የአጥንት ሾርባ ያብስሉ ፡፡ ለእነዚያ ቀዝቃዛ የክረምት ምሽቶች ተመራጭ ነው።
10. አትክልት የመብላት ቀን
በዚህ ቀን የትኛውን አትክልቶች መመገብ እንደሚፈልጉ እያንዳንዱ የቤተሰብ አባል ተራ ይኖራቸውል።ነገር ግን በሌላ የቤተሰብ አባላት የተመረጡትን ሁሉንም አትክልቶች የማይሞክሩ ከሆነ ተራውን ለሚቀጥለው ተራውን ያጣሉ ማለት ነው፡፡