አስተውሎ መመገብ ለተሻለ ጤና-

አስተውሎ መመገብ አስተዋይነትን እንደማለት ነው። በምንመገብበት ወቅት የምንበላውን ማወቅ በሰውነታችን በቀላሉ የሚቃጠለውን የምግብ ምጠን የመረዳት ችሎታ ነው ፡፡ አስተውሎ መብላት ሆድን ለመሙላት እና መበላት ሰላለበት ለሚበላው ሁሉ ጠቃሚ ነው ፡፡ እኛ የምንምገበውን እንመስላለን ያለ ምግብ መኖር አንችልም ነገር ግን ሰውነታችንን ባልረባ ምግብ እንሞላለን በውስጡም ምን እንዳለ ማውቀ አንፈለግም - በዚህ ሰአት ነው አስተውሎ መመገብ የሚያስፈለገው ፡፡

እንዴት መጀመር እንዳለብን

ምግባችንን ሰንገዛ በአቅማችን እና የተመጣጠነ ንጥረነገር ያለው መሆኑንና መረዳት አእለብን፣ ሰናዘጋጀውም ወይም ስንመገበው ለጤንነታችን ተስማሚ፡መሆኑን በመገንዘብ ደስታና እርካታን ይሰጠናል።ስንመገበ ራሳችንን ትኩረት ከሚከፋፍሉ ነገሮች ውይም እይታ አርቀን በተረጋጋ መንፈስ መሆን አለበት፡ ስናዘጋጅ እና ስንመገብ ከቤተሰብ አባል ወይም ከጓዋደኛ ጋር ብናደርገው ደስታን ሊሰጠን ይችላል፡፡

እስኪ ፓስታ በቲማቲም/ እና በበሶብላ ፣ በዛ ባለ ቺዝ ከሰላጣ ጋር ብናቀርበው እና ቁጭ ብለን በስሃናችን ላይ ያለውን ለእህይታ ማራኪ የከለር አይነቶች በሹካችን ጠቅለለን ወደ አፋችህን ስንመገብ ጣህእሙን እያጣጣምን በቀሰታ እያኘከን ሰንውጥ ያለውን እርካታ ሰናስብ ምን ያህል ያስደሰታል፡፡

የአስተውሎ መብላት የሚሰጡት ውጠቶች

ማንኛውንም ምግብ፡ አስተውሎ የመብላት ልምድ በሚሰጠው ደስታ እና ጣዕም ከፍተኛ እርካታን እናገኛለን፡ እንዲሁም ምግብን በቀስታ ስናኝክ የምንጎርሰውን የምግብ መጠን ስንቀንስም እናስተውላለን ፡በተጨማሪም የምግብ አፈጫጨቱንም ስርዓት በጥሩ ሁኔታም ይቀይራል፡፡ አስተውለሁ የሚመገቡ ሰዎች አስተያየት ሲሰጡ አስተውለው በመመገባቸው በከፍተኛ ሁኔታ ክብደት መቀነስ መቻላቸውና በቶሎ ሊጠግቡ እንደቻሉ ነገርግን ከዚበፊት በስውነታቸው ላይ የሚያመጣውን ችግር ካለማስተዋል በጭፍን ይመገቡ እንደነበር ይናገራሉ። አስተውሎ የመመገብ ልምድ ወደ አስደሳች የምግብ ማብሰል ልማድ እና ጥሩ የቤተሰብ ትስስርም ሊፈጥር ይችላል፡ እንደዚሁም አብስሎ የመብላት ልማድን ለህፃናት ማስተማር ምን ይህል እርካታ ያለው አስደሳች ተግባር እና ለህይወት አስፈላጊ መሆኑን እንዲሁም መብላት ለምኖር ብቻ እንዳልሆነ እንዲገነዘቡ ያደርጋል።

The cookie settings on this website are set to 'allow all cookies' to give you the very best experience. Please click Accept Cookies to continue to use the site.
You have successfully subscribed!